www.maledatimes.com የአሥራ ሁለት አምባሳደሮች በተለያዩ አገራት አምባሳደርነትን ሊያገለግሉ ተመደቡ !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የአሥራ ሁለት አምባሳደሮች በተለያዩ አገራት አምባሳደርነትን ሊያገለግሉ ተመደቡ !!

By   /   August 17, 2017  /   Comments Off on የአሥራ ሁለት አምባሳደሮች በተለያዩ አገራት አምባሳደርነትን ሊያገለግሉ ተመደቡ !!

    Print       Email
0 0
Read Time:45 Second

ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ሐምሌ 19 ቀን 2009 ዓ.ም. የሰጡት የአሥራ ሁለት አምባሳደሮች ሹመት ምደባ ይፋ ሆነ:: የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ጽሕፈት ቤት በፌስቡክ ገጹ ይፋ እንዳደረገው፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ አቶ ሥዩም መስፍንን ተክተው የቻይና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተመድበዋል:: አቶ ካሳ ተክለ ብርሃንም አቶ ግርማ ብሩን ተክተው የአሜሪካ ባለሙሉ ባለሥልጣን አምባሳደር ሆነዋል::

በተመሳሳይ የቀድሞ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትር ወ/ሮ አስቴር ማሞ የካናዳ፣ የቀድሞው የትምህርት ሚኒስትር ሽፈራው ተክለ ማርያም (ዶ/ር) የደቡብ አፍሪካ፣ እንዲሁም የቀድሞ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የስዊዲን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተመድበዋል::

ከዚህ በተጨማሪ አምባሳደር ተበጀ በርሄ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ አቶ መታሰቢያ ታደሰ የኳታር፣ የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ የኢንዶኔዥያ፣ ወ/ሮ ሉሊት ዘውዴ የሩዋንዳ፣ የሥነ ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ዓሊ ሱሌይማን የፈረንሣይ፣ እንዲሁም አቶ ሙሉጌታ ዘውዴ የሱዳን ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሆነው ተመድበዋል::

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልዩ ረዳት የነበሩት አቶ እውነቱ ብላታ በብራሰልስ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር መሆናቸው ታውቋል::

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar