www.maledatimes.com የግንቦት ሰባት ፓርቲ ስብሰባ ላይ የህብር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋን የመቅረጸ ድምጽ እና ካሜራ ይዞ ገብቶ ከስፍራው ገብቶ እንዳይዘግብ ከለከሉት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የግንቦት ሰባት ፓርቲ ስብሰባ ላይ የህብር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋን የመቅረጸ ድምጽ እና ካሜራ ይዞ ገብቶ ከስፍራው ገብቶ እንዳይዘግብ ከለከሉት

By   /   October 26, 2017  /   Comments Off on የግንቦት ሰባት ፓርቲ ስብሰባ ላይ የህብር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋን የመቅረጸ ድምጽ እና ካሜራ ይዞ ገብቶ ከስፍራው ገብቶ እንዳይዘግብ ከለከሉት

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 1 Second

በላስቬጋስ ይከናወን የነበረውን የግንቦት ሰባት የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ላይ ደጋፊዎቹን እና ሌሎች ነጻነት ናፋቂ አባላትን ገንዘብ ማሰባሰብ ላይ የሚገኘው የግንቦት ሰባት የገንዘብ ቡድን የነጻ ጋዜጠኞች የአመራር አካል እና የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ የሆነውን ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ ከስፍራው ሆኖ እንዳይዘግብ ከአመራር አካላቶች በተሰጠው ትእዛዝ መሆኑን ለማለዳ ታይምስ የደረሰው ዘገባ ያመለክታል።

ጋዜጠኛው ከስብሰባ አዘጋጆች ጋር የነበረውን የመረጃ ውይይት ሃሳቡን ምንጸባርቅ እንዲችል ብቻ በማድረግ እና ማንኛውንም ሪፖርት ለመስራት በሁለት በኩል ተከፍለው ለመፍቀድ እና ላለመፍቀድ የተወያዩ ሲሆን በዚህ ውሳኔ ላይ ስምምነት ባለመምጣቱ ጋዜጠኛው ስብሰባውን ረግጦ ለመውጣት በመሞከሩ እንደገና ተመልሶ እንዲገባ ካደረጉ በኋላ ፣ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ መድረኩ ከገባ በኋላ በአንድ የግንቦት ሰባት አባል ማናቸውንም የቴክኖሎጂ መሳሪያ ተጠቅሞ መቅረጽ እንደማይችል እና ይህንን የሚያደርግ እንደሆነ ከመድረክ እንደሚያባርረው አስፈራርቶታል።

ይህንን ከሆነ በኋላ ጋዜጠኛው የሚቀርጸውን ሁሉ አቋርጦ ስብሰባውን የተከታተእ ሲሆን ክልከላውን ከፈጸመው ግለሰብ በወረቀት ብቻ ማስታወሻ እንዲይዝ ሃሳብ መሰንዘሩን ፣ህዝብን ማስቆጣቱን እና የጋዜጠኝነትን ስነ ምግባር ለሚያውቁት ሁሉ የንቀት መግለጫ አድርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋን ከመቅረጫ ድምጹን  ይዞ በአዳአራሽ እንዳይገባ የተከለከለ መሆኑን በፌስቡክ ገጻችን ላይ ያሳወቀ መሆኑን እና በግንቦት ሰባት ላይ በነበረው ስብሰባ ላይ የመረጃ ዶክመንቶችን ይዞ መግባት እንደማይችል መግለጻቸውን ግን አልሸሸገም ፤ ይህም ሆኖ በስብሰባው ላይ ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችለውን መግቢ የመገናኛ ብዙሃን መሳሪያዎቹን ጥሎ ሲገባ ብቻ መሆኑን ለማወቅ ችለናል ። ለተደረገልን መስተካከል ሃብታሙ አሰፋን እያመሰገንን በማናቸውም ሁኔታዎች የመረጃ ማእከሎችን ማፈን መቻል ከአፋኝ እና ጨቋኝ ስርአት ተለይተው የማይቻሉ ናቸው ።

በእለቱ ይከናወን የነበረው ይሄው ስብሰባ ላይ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚገኝ የነበረ ሲሆን በዚህ ስብሰባ ላይ ጋዜጠኛው ስብሰብውን ምንም አይነት መረጃ ማስተላለፍ እንዳይችል አደርገውታል፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ባሳለፍንነው ሳምንት የህብር ሬዲዮ ጋዜጠኛ አቶ ካሳዬ መርሻ  የተሰኘ ግንቦት ሰባት አባል የሆነ ፣ሆኖም ግን በአስመራ ስለተከሰተው ነገር አንዳችም ነገሮችን የማያቅ በመሆኑ እና የህዝብ ግንኙነት ተብሎ በመሰየሙ ምክንያት የህብር ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ላቀረበለት ጠንካራ ጥያቄ እና የመልስ ውይይት አቶ ካሳዬ መርሻ ከአውሮጳ የሚሰጠው መልስ በማጣቱ እና በዝረራ በመውደቁ መሆኑን ከግንቦት ሰባት የወጣው ድብቅ መረጃ ያመለክታል ።

ግንቦት ሰባት አማራዎች በድርጅቱ ውስጥ ይመራሉ የሚለውን ነጸብራቅ በማህበረሰብ ለመዝራት ሲል ይህንን ግለሰብ እንደ መሳሪያ እንደተጠቀመበት እና ህብር ሬዲዮ በአለም አቀፍ ተደማጭነት ማግኘቱን ተከትሎ ማናቸውንም ትግሎች ያደናቅፍብኛል ብሎ ያልጠበቀው ግንቦት ሰባት ድምጹን እንዲሰጥ መፍቀዱ ከመጥፎ አዝቅት ውስጥ እንዲወድቁ ዳርጓቸዋል ሲል ዘጋቢያችን መረጃውን አጣርቶ እና መርምሮ ዘግቧል ። ከወያኔ በማይተናነስ ጨካኝነት የተሞላ ፓርቲ በግንቦት ሰባት እና በሌሎች ተቃዋሚዎች ላይ ማየታችን የሃገራአችን የወደፊትን ራእይ የሚያቀⶽ ከመሆኑም ባሻገር ፣በግንባር ቀደም ሃገርን ሊመሩ የማይችሉ ፖለቲከኞች የመጀመሪያ ምእራፋቸውን በጨቋኝነት እያሳዩን መሆኑን የሚገልጽ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን የሰጡን የስብሰባው ታዳሚዎች ለማለዳ ገልጸዋል።

በወቅቱ የተሰበሰበው ገንዘብ እና የጨረታ ሽያጭ ገቢ ሳይገለጽ የድርጅቱ ስብሰባ መበተኑ ተገልጧል።

ነጻ ሚዲያን መፍጠር የማይችሉ ማናቸውም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከማንኛውም ማህበረሰብ ጋር በነጻነት መስራት አይችሉም !! የዛሬው መልእክታችን ነው

ማለዳ ታይምስ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar