www.maledatimes.com ሳምንታዊ ዳሰሳ ከዳላስ ቴክሳስ ስፖርት ሜዳ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ሳምንታዊ ዳሰሳ ከዳላስ ቴክሳስ ስፖርት ሜዳ

By   /   July 16, 2018  /   Comments Off on ሳምንታዊ ዳሰሳ ከዳላስ ቴክሳስ ስፖርት ሜዳ

    Print       Email
0 0
Read Time:9 Minute, 51 Second
ቅድሚያ  ትዝብታችንን በፌደሬሽኑ ደካማ አጀማመር የጠቀስናቸው ጥቃቅን ህጸጾች እንደተመለከታችሁ እርግጠኞች ነን ፣አሁንም ደግመን በምግብ ቤቶች እና እንዲሁም ቀሪውን የፌደሬሽኑን ሂደቶች እንደገና ደግመን በተለያዩ ጉዳዮች ላይም እንቃኛለን ሌሎችንም ትዝብቶች እንዳሣለ።
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በየአመቱ አስተያየት ስንሰጣቸው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ዝምታን መምረጣቸው ግልጽ ቢሆንም እኛ ግን ያለ መሰልቸት ያየናቸውን እና የታዘብናቸውን ከመናገር እና ከመግለጽ አንቆጠብም ፣ይህም ከግንዛቤ ይገባልን ዘንድ እየታሰበ ያለምንም ቅራኔ ትክክለኛውን ነገር ለመናገር አሁንም እንጥራለን። በቅድሚያ ስለ ቀድሞው የፌደሬሽኑ ፕረዚደንት ስለነበረው እና አሁንም የፌደሬሽኑ ህልውና በእሱ ብቻ ጫና ያለው የሚመስለው እና የግንቦት ሰባትፓርቲ ዋነኛ የፌደሬሽኑ ሰባኪ የሆነው አቶ ጌታቸው ፣ስልጣኑን ካስረከበበት ጊዜ ጀምሮ አሁንም የዚሁ የፌደሬሽኑ ዋና መሪ በመሆን ሚናውን ሲጫወት፣ የወቅቱ ፕረኢዳንት አቶ አብይ በጣም ምስኪን እና መልካም ሰው ከመሆኑ በላይ ዝቅ ብሎ መስራትን እና ማስተዳደርን ከመውደዱ የተነሳ የእርሱን ቦታ ተክቶ እንደ ዋና ሃላፊ የሚሰራው ይሄው የቀድሞው መሪ አቶ ጌታቸው ሲሆን ፣ብዙሃኑ እጅህን ከፌደሬሽኑ ላይ አንሳ ቢሉትም አልሰማም ማለቱ ግርምትን ይፈጥራል፣ስለዚህ በቅድሚያ የምናስታውሰው ነገር ቢኖር ከፌደሬሽኑ ላይ እጅህ አንሳ ነው።
በሌላመልኩ የበጋ ወራት ላይ የሚከናወነው ይሄው የባህል እስፖርት ማእከል ከየትኛውም ለየት የሚያደርገው ፣ስሙ ሲሆን ስራው እና ምግባሩ ግን የትየለሌ ነው ፣እንደምሳሌ ያህል የሰሜን አሜሪካ የስፖርት እና ባህል በሚል የሚጠራው ይሄው ማእከል ስሙን እንኳን ንጥር ባለ መልኩ ብንመለከተው እና የሚያቀርበው ስፖርት አንድ የእግርኳስ ጨዋታን ብቻ ሲሆን ከዚያም ባሻገር ለተጨዋቾቹ ምንም አይነት የትራንስፖርትም ሆነ የሆቴል የማይችል ከመሆኑም በላይ ፣ ተጨዋቾቹ ታጋሾች እና ለጨዋታ ፍላጎት በማለት ከኪሳቸው ወጭ በማውጣት አለበለዚያም ከየስቴቱ ያሉ ማህበረሰባቶች ከኪሳቸው እያዋጡላቸው በመዘውወር ጨዋታቸውን ሲያካሂዱ ፣ ፌደሬሽኑ ደግሞ እነርሱ(ተጨዋጮቹ) በለፉበት እና በደከሙበት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከማህበረሰቡ ኪስ ዝቆ ይሄዳል።
ይህም ብቻ ሳያንሰው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርት በሚለው የትኛውንም ባህላዊ እሴቶቻችንን በስፖርት ፕሮግራሙ ላይ ሲቀርብ አይተንም ሰምተንም አናውቅም ፣እንዲያውም በየ አመቱ እጅ እጅ የሚሉ ድምጻውያንን እና ዳንሰኞችን በፋንትሽ በቀለ በኩል እንዲቀርቡ በመደረጉ ምንኛ የኪነጥበብን እድገት ወደ ቁልቁል እንዳራመዱት መገመት አያዳግትም ። በዚህም የተነሳ ዳግም ፋንትሽን ማየት የማይፈልጉ ብዙሃን ኢትዮጵያያኖች መቼ ነው ጡረታ የምትወጣው እያሉ መዘበታቸውን አላቆሙም ፣ ለዚህም ከካንሳስ ሙዙሪ፣ አትላንታ፣ ዳላስ፣ ካናዳ እና ሳንዲያጎ የመጡ እንግዶች የጠየቅናቸው ሲመልሱ ተመሳሳይ ሃሳብ እንደሰነዘሩ ለመግለጽ እንወዳለን። ስለዚህ ከፌደሬሽኑ ጋር አብሮ ማርጀት የለም እና በወጣት ሃይል መተካካት ከእናንተ ይጀመር፣ ፖለቲከኞችን ስልጣናችሁን ልቀቁ እያላችሁ ፣ከማሰልቸትችሁ በፊት እናንተ የስልጣን ወንበርን የመልቀቅ ልምድ ይኑራችሁ እና ሌሎች ወጣት ሰራተኞች ይተኩበት፣ እስከ ዛሬም ለሰራችሁት ስራ የሰላሳ አምስት አመታቱን ወጭ እና ገቢ በትክክለኛው መሰረት ኦዲት ብታስደርጉት እና ዶክመንቶቹን ለህዝብ እይታ ብታቀርቡት መልካም ነው ፣ሆኖም ግን የማን ኪስ እንደሚበረበር እና ማን ዘብጥያ እንደሚወርድ መገመት አያዳግትም እና እንተወው።

በተለይም በዚህ በሁለት ሺህ አስራ ስምንት የተደረገውን የፌደሬሽኑን ቅሌት መዳሰስ ከተጀመረ በጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋን ለመደብደብ መነሳት ነው ፣ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ማለት በበሳል ጽሁፎቹ የሚታወቅ ድንቅ እና የተከበረ የእረጅም ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ጋዜጠኛ ፣ይህ ጋዜጠኛ የጻፋቸው ነገሮች እውነታቸው የሚፈለቀቁት በትክክለኛው ቦታ እና ጊዜ መሰረቱን በጠበቁት ሁኔታዎች ነው ፣በሬ ወለደ ስራ አይመቸውም ፣ሰውን ያከብራል ይጫወታል፣ ለእውነት ይሞታል፣ ኢሳት የተሰኘውን ድርጅት ካቋቋሙት ጥቂት ሰዎች ውስጥ የመጀመሪያው ሲሆን በመካከል በአመራር ደረጃ ባስቀመጧቸው የሆላንድ ቀን ጅቦች ውስጥ ተጠልፈው እንዲወድቁ ከተደረጉት ጋዜጠኞች መካከል ፣ ይህ ጋዜጠኛ እና ጋዜጠኛ ከፋለ ማሞ የሚታወሱ ናቸው ፣ክንፉ አሰፋም ያለምንም ማመንታት ከሁለት አመታት በላይ የኢሳት ቴሌቪዥን ስቱዲዮን በጊዜአዊነት በእርሱ ቤት እንዲመራ እና እንዲጠናከር ካደረገበት ጊዜ በሁዋላ ፣ከጀርባቸው የፖለቲካ አላማ ይዘው የመጡ ጋዜጠኞች ፣ከምርጫ ዘጠና ሰባት በሁዋላ የአስራ ሰባት ወራት እስራታቸውን ጨርሰው ወደኬንያ አምርተው ከዚያም ሆላንድ ካቀኑበት ጊዜ ጀምሮ የግምቦት ሰባት አላማን እና ምግባርን ለማስፈጸም በሚያደርጉት ትጉህ አላማ ፣እና አስጨራሽ እልህ ፣ የውሽት ፕሮፖጋናዳ በመንፋት የሚታወቁት እነዚሁ የሚዲያ ሰዎች መስራቹን እና በቀድሞው የኢሳት የህዝብ ግንኑነት ሃላፊ ክንፉ አሰፋ እንዲሁም ሌሎች ጋዘጠኞችን ድርጅቱ በማይወስነው እናስነ ምግባር በጎደላቸ ግለሰቦች የውሸት የፈጠራ ወሬ ድርጅቱን እንዲለቁ አስደረገው ዛሬ የግንቦት ሰባት መፈንጫ አድርገውታል። 
ታዲያ ይህ ሰው እውነተኛን መንገድ በተመረኮዘ ሁኔታ በበሳል ብእሩ ስለሚተቻቸው እነርሱም የሚያጠቁበት መንገድ ባለመኖራቸው በሃይል እና በጉልበት በመምጣት ማወዛገብ መጀመራቸውን ስናይ ትልቁን ዳቦ ሊጥ ሆነ እንድንል አስቻለን ። በዚህም ወቅት ጋዜጠኛን የክብር እንግዳ አድርጎ የስራ ባልደረባዎቹ ከሆኑት ውስጥ ትልቅ ጋዜጠኛን ለመደብደብ መነሳት የውርደት መጀመሪያ ሳይሆን የውርደት መጨረሻ መሆኑን ብትገነዘቡት ጥሩ ነበር ። የዚህ ሰው ለመደብደብ ዋነኛ ምክንያት የሆነው የሚዲያ አባል እንደመሆኑ መጠን በተለያዩ ቦታዎች በመገኘት ሊያደርጋቸው የሚችሉትን ቃለ መጠይቆችንም ሆነ በበአሉ ሂደት ላይ የሚደረጉትን ክስተቶች በማጤን ለዝግጅት ፕሮግራሙ መዳመቅ እና መሳካትም ሆነ ጉድለቶችን በማጤን ማቅረብ ለሚችለው የመረጃ ድጋፍ ይሆነው ዘንድ ፣ሪፖርቶችን እንዲሰራ ይረዳዋል ታዲያ ይህ ከሆነ ዘንዳ ፣በፌደሬሽኑ አመራር ነኝ የቦርድም አባል ነኝ ያለ አንድ ግለሰብ ፣ከሜዳው ውስጥ ገፍትሮ ሊያስወታው ሲሞክር ለምን ትገፈትረኛለህ ፣ከሜዳው ብትወጣ ይሻላል ብትለኝ ይቀለኛል በሚለው ሃሳብ አንተ ማነህ ከፈለክ ከሜዳውም ሆነ ከማንኛውም ቦታ አባርርሃለሁ በማለት ወደ ከፍተኛ ጸብ እንዲበረታ ዳርጎታል። ከመጠነኛ መከራከር እና ዱላ ቀረሽ የሆነ ንግግር ከተደረገ በሁዋላ የማንነት ጥያቄ ሲነሳ እና ከፌደሬሽኑ አባሎች ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ ማን እንደሆነ ከተረዳ በሁዋላ እባካችሁ ተሳስቼ ነው ይቅርታ ይደረግልኝ ማለቱ ቢታወቅም ፣ ማንኛውም ሰው በሰበአዊ መብቱም ሆነ በሰውነቱ መከበር ሲገባው ፣እኔ አውቅልሃለሁ፣እኔ ከአንተ እበልጣለሁ ብሎ ሰውን ለማዋረድ እና ለማጎሳቆል መታሰብም የለበትም ይህ ከሆነ በድጋሚ በዚህ ፌደሬሽን ውስጥ ብዙ አይነት ውስብስብ ችግሮች ሊገጥሙት እንደሚችሉ ይገመታል። ስለዚህ የዚህ የፌደሬሽን ሂደት እንዲህ አይነት ድክመቶችን ይዞ ጉዞውን ከጀመረ የውድቀቱ ፍጽሜ መጭው ጊዜ ቅርብ ሊሆን ይችላል፣የውደት ጊዜውን ላለማፋጠን ከላይ የተጠቀሱትን ጥቂት ሃሳቦችን እና የሙሰኝነትን እና ዘረፋን ፣ለሰዎች ክብር እና የሙያ ስነ ምግባርን ፣የሙያ አጋርን ማክበር እና ሌሎችንም ጥቃቅን ስህተቶችን በጉልህ በማየት ይህ የህዝብ ፌደሬሽን የሆነን ትልቅ ድርጅት የግለሰብ ከማድረግ በመቆጠብ ፤ እና የአንድ ቤተሰብ አባላቶች በሁለት እና በሶስት የአመራርነት ቦታ ላይ ተቀምጦ ፌደሬሽኑን ለመበዝበዝ መነሳት መቆም ይገባዋል እንላለን ሊታሰብበትም ይገባል። ሳምንታዊየአብይ የፍቅር ሳምንት የተባለው ለካ የለበጥ የሰዎችን ልብ ለማንጠልጠል ነው ጃል።
በሳምንታዊው ቆይታችን ውስጥ ስለታዘብናቸው የፌደሬሽኑ ነገሮች ብዙ ለማለት በወደድን ጠንካራ የሚባሉ አንዳችም ነገር የላቸውም ሆኖም ግን እንዲጠነክሩ ስንል ድክመቶቻቸውን ነቅሰን እንናገራለን ። በዚህ አመት ለተደረገው ጨዋታ የክብር እንግዳ ሆኜ ልቅረብ በማለት በእራሱ አንደበት በግልጽ ደብዳቤ ለፌደሬሽኑ ያሳወቀው የአሁን የለውጥ መሪ የሆነው ዶክተር አብይ አህመድ ፣ለፌደሬሽኑ ደብዳቤ ማቅረቡ አነጋጋሪ የሆነ ጉዳይ ነበር ታዲያ ምላሹ ግን በፌደሬሽኑ ሙሰኞች እንዳይሳካ የተደረገበትን ሁኔታ ስንሰማው ፣አንገታችንን እንድናሸማቅቅ አድርጎናል ፣ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ ፌደሬሽን መቼ ይሆን የሚጠራው በማለትም ትዝብታችንን መጫር ግዴታችን እንደሆነ ሲገባን ፣ወደ አደባባይ ማውጣቱን መረጥን። የዚህ ትልቅ መሪ ጥያቄ የተቀለበሰው በሁለት የፌደሬሽኑ አመራሮች ሲሆን እነዚህም ሰዎች ከአቶ አባይ ጸሃይ እና ከሌላ አንድ የህወሃት ባለ ሃብት በጥሬ ገንዘብ በየግላቸው 100.000 ዶላር በመቀበላቸው ነው የሚለውን በሰማን ወቅት እና የእነዚህን ሰዎች ለማጣራት ወደ ሳንፍራንሲስኮ የሚገኘው የፌደሬሽኑ አካላቶች ስንደው ማናቸውም ፣ መልስ ለመስጠት ፍላጎት እንደሌላቸው ተገልጦአል። ስለዚህ ፌደሬሽኑ በገንዘብ ሃይል የሚመአ ከሆነ ከዚህም በፊት የነበረባቸው ችግር የሼክ አላህሙዲ ደጋፊዎች ጋርም ይሄው እንደሆነ በግልጽ የተጻፈ ሲሆን ከፖለቲካዊ አጀንዳ ጋር እንዲያያዝ ተደርጎ ፣ለሚዲያ ፍጆታ እንዲቀርብ ሆኖአል፣ይህስ ለምን ሆነ የዶክተር አብይን ከሚፈልገው ህዝብ ጋር እንዳይገናኝ በግል ጥቅሞቻችሁ አማካይነት ለምን ማስቀረት አስፈለገ? እንደዚያስ ከሆነ ለምንስ አልባሌ የሆነ ምላሽ ለህብረተሰቡም ሆነ ለዶክተር አብይ መስጠት አስፈለገ የሚሉት ምላሾች ቢቀርብበት ጥሩ ነበር ።
በትክክለኛው መድረክ ለአዶከተር አብይም ሆነ ለመላው ማህበረሰብ የይቅርታ ደብዳቤአችሁን አቅርባችሁ እንደገና መልካም ግንኙነታችሁን ብታጠነክሩ ይሻላል፣ እንደከዚህ ቀደሙ አቶ ጌታቸው የደም ገንዘብ እንዳለው ፣ዛሬም እናንተ የደም ገንዘብ ተቀብታችሁ እየዞራችሁ የህዝብ ነን ብላችሁ ማጭበርበሩን አቁሙ። በሌላ አቅጣጫ ደግሞ በዳላስ እና አካባቢዋ ስለነበሩት የምግብ ቤቶች ሂደት ያየናቸውን ለመመስከር ገጻችንን ሰፋ አድርገን ከፍተናል ፣ የደስታ ምግብ ቤት የደረስነው የዝግጅቱ ቀን ገና ከመከፈቱ ሁለት ሶስት ቀን ቀደም ብሎ ነበር፣ በዚያን ቀናቶቹስም ሆነ ከዚህ ቀደም ብሎ ዳላስን ለመጎብኘት በተጓዝንበት ጊዜ ይህንን ቤት ለማየት የሚያስችለን ጊዜ ገጥሞናል፣ ከቀድሞ ባለቤቶቹ ህልፈተ ህይወት በኋላ ያለው አስተዳደር የተለየ ቢሆንም ምግባቸው ከቀድሞ ይሻላል ማለት ባይቻልም፣ ጥሩ ነው ብለን አስተያየት ሰጥተን ነበር፣ ሆኖም ቀድሞ የነበረውን የምግብ ዝርዝር በመለወጥ እና የዋጋ ተመን ከ60 በመቶ በላይ በመጫን የተመጋቢውን ኪስ ለማሟጠጥ ከተነሱት ምግብ ቤቶች ውስጥ ቀዳሚው ስፍራ የያዘ ሲሆን፣ ወደ እዚህ ምግብ ቤት፣ ጎራ ባልንበት ወቅት እንደ አጋጣሚ እነ ሲስተር ዘቢደር፣ መቅደስ ተስፋዬ ፣ቴዎድሮስ ተሾመ እና ዮኒ ቬጋስ በጋራ በአንድ ተሽከርካሪ መኪና ውስጥ ሆነው እኛ ደግሞ በሌላ ተሳፍረን እኩል ከመኪና ማቆሚያው ውስጥ ደረስን ፣ይህንን አጋጣሚ ተጠቅመን መወያየት የሚገባን ጉዳይ ስለነበር ከቴዎድሮስ ተሾመ ጋር በመነጋገር እነርሱ ሊገቡበት ከነበርው ሲቲ ካፌ አስቀርተናቸው ወደ ደስታ እንድናመራ ተወሰነ ፣በዚህን ወቅት ነበር ያልጠበቅነው የዋጋ መናር እና የምግብ ለውጥ መኖሩን የሰማነው። ከሰባት በላይ የምግብ ዝርዝር እንደሌለ እና የፈለግናቸው ምግቦችም በአዲስ የምግብ ዝርዝር መቀየሩን አስተናጋጇ ገለጠችልን ፣እኛም ያለውን እንመገብ በሚል ተስማማን እና አዘዝን ከታዘዙት መካከል ፣ቋንጣ ፍርፍር፣ ጥብስ ፣ ክትፎ ፣በጥቂቱ እንደሆኑ አስታወሳለሁ፣ ሁሉም ነገር እህል እህልም አይልም ፤ ይህም ብቻም አይደለም ጨውም አልተጨመረበትም ፣
ፍርፍሩ ገባ ወጣ ተደርጎ ከመሰርቱም በላይ እሳት አልመታውም እና ጣእሙን ስታዩት ወንደላጤ በቤቱ ውስጥ ከደስታ ምግብ ቤት በላይ ክሽን ያለች ፍርፍር እንደሚሰራ መመስከር እችላለሁ፣ ለዚህም ምግብ የዋጋው መናር ሳያንሰን ፣ የምግቡን አለመጣፈጥ ለነገርናት አስተያየት ተቀባይ እና እንዲሁም ባለቤት ለተባለችው ሴት ፣(ስሟን መጥቀስ ስለምይገባኝ ነው) ምንም አይነት ንግግርም ሳያደርጉ በመመናጨቅ መሄዳቸው ከሚገባው በላይየሚያናድድ ቢሆንም፣ የሃበሻ ምግብ ቤቶች በእራሳቸው ላይ የሚያደርጉት ዘረፋ እና ግዴለሽነት ቢስተካከል ጥሩ ቢሆን ፣ ፌደሬሽኖችም የአዘጋጅ አገሮችን ሲመርጡ ምግቤቶቻቸውንም ሄደው በመጎብኘት ቅናሽ ዋጋ እንዲሸጡ መዋዋል ሲገባቸው ጣራ የነካ ዋጋ ሲደረግባቸው ምንኛ እርካታ እንደሚሰጣቸው ባናውቅም ፣እንዲህ አይነት ገቢ ለአንድ ማህበረሰብ በሰፊው ማምጣት ቀላል አይደለም እና ምናልባትም ለጎብኝዎቹ ከባድ እንደሚሆን ቢታሰብበት እና የዋጋውን ንረት ፣በክክለኛው የዋጋ መጠን ቢደረግ ጥሩ ነው። ሌላው ደግሞ የእናት ጓዳ ምግብ ቤት ሲሆን ከምግብም ሆነ ከአስተናጋጅ የራቀ ባዶ ቤት ነው ፣ አስተናጋጆቹ በጥሪም አይደለም በልመናም አያስተናግዱም፣ ከመለመኑም በላይ ደግሞ ንጽህና የሚባል የላቸውም ፣ ከባዱ ነገር እና ዋነኛው ይሄ ነው ፣ንጽህና ወደ ሌለው ምግብ ቤት ጎራ ብሎ ጸጉሯን እያከከች መጥታ ማእድ ካቀረበች በሁዋላ ምን አይነት የምግብ ፍላጎት ያለው ሰው መጥቶ ሊመገብ እንደሚችል መገመት አያዳግትም፣ ለዚህም መነሻ ነጥብ ሁለት ነገር ልግለጽ ፣ከአንድ ደንበኛ የቀረበ ቡና ነበር ፣በዚህን ወቅት ላይ እኔ በቡና ማሽኑ በተገተረበት ቀጥታ ተቀምጬ የሚከናወነውን በአይኔ መቃኘት ጀምሬአለሁ።
የሰው ብዛት ጢም ብሎአል፣ የማውቃቸው ታዋቂ ሰዎች ፣ፖለቲከኞች ፣ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ አስተያየት ሰጭዎች ከፊት ለፊቴ ተደርድረዋል ፣ እኔም ማንነቴን ላለማሳወቅ አብዛኞቹን ሰላምታም አልቸርኳቸውም ፣ምክንያቱም በአይን ማየት ለጋዜጠኛ ስራም ነውና ። በዚህን ጊዜ አንደኛዋ አስተናጋጅ አፍንጫዋን በጣቶቿ እየጎረጎረች በመምጣት ቡና ላዘዘው ሰው የቡና ማጥለያውን አንስታ የተጨመቀውን ቡና ካራገፈች በሁዋላ ፣እንደገና አፍንጫዋን በደፈጠጠችበት እጆቿ መልሳ መጭመቂያ ወንፊቱን ጠራረገችበት ፣ በዚህን ወቅት ትክክል እንዳልሆነች ለመገሰጽ ሞከርኩኝ ሆኖም እርሷ የዋዛ አይደለችም እና ክርክር ገጠመችኝ ፣ ለማንኛውም አስተያየትሽን ተቀበይ ለሚያይ ሰውም አይደለም ለተጠቃሚውም ጤና አይደለም ብዬ ትቼአት ወጣሁ፣ በሌላ ቆይታ እንደገና ወደዚሁ ቤት አመራን ፣ያቸው ልጅ አስተናጋጅ ሆና ተመድባለች። ከእሷ ውጭ ሌላ ሰው አያስተናግድም፣ የሳምንት ድካም አለ ፣እንግዶች በሙሉ ሃገር ለቀው ወጥተዋል፣ ሆኖም የምግብ ዝርዝር አልተቀየረም ፣ዋጋው እንደናረ ነው ፣ ምግብ አዘዝን ፣ምግቡም ከጥብሱ ውጭ ሁሉም የምግብ ዘር አይመስልም፣ ምግቡም በቀረፋ እና ጥቅቁር አዝሙድ ቅመም ያበደ ይመስላል ፣ከቀመሙ ውጭ የጥብሱም ጣእም አይታወቅም፣ በዚህን ወቅት አስተያየት ሰጠተናት ልንሄድ ስንል እራሷን እያከከች ለሌላ ሰው ምግብ ማቅረቧን አስተዋልን ፣በዙሪያዋ ያለን ሰዎች በሙሉ ጋዜጠኞችም እንደሆንም አላወቀችም ትዝብታችንን ድጋሚ ማፈንዳት አልፈለግን ፣የንጽህና ጉድለት የሚመጣው ከአስተዳደሩ ካለው ጥብቅ የሆነ የንጽህና አመለካከት ስለሆነ ፣ባለቤቶቹም የተዝረከረኩ ናቸው ብለን ወሰንን፣ ባይሆኑማ ኖሮ ጉድጉዋድ ውስጥ የተቀበረ ቦታ ላይስ ማን ንግድ ይጀምራል፣በለን መልሰናል።
ሌላው ድሬዳዋ ነው ድሬድዋ በባለቤትየዋ የእንኳን ደህናመጣችሁ ጨዋታ ተደስተህ ትወጣለህ ፣ደስ ይልሃል ትዝናናለህ፣ የምግብ አቅርቦት ላይ ግን ከፍተኛ ጊዜ ይወስዳል፣ ከመግባትህ በፊት ማዘዝ ደግሞ ከባድ ነው ያዘዝከው ፣ምግብ ላላዘዝከው ሰው ሊቀርብለት ይችላል፣ ፣የዚህ ቤት ችግር አስተናጋጆቿ የምግቡን ዝርዝር በብቃት አያውቁትም፣ አንዷ ከአውስትን ቴክሳስ ነው ለዚሁ በአል መትታ ስራ የጀመረችው ፣ሌላዋም ከእዚያው ዳላስ በቅርብ ጊዜ ስራውን እንደጀመረች እና ምግቡንም እንደማታውቀው ገለጠችልን ግን ፣በቃ የታዘዘውን ምግብ መጠበቁ ከሁለት ሰአታት በላይ ይፈጅ ነበር ፣ይህ አይነቱ እርማት ቢታረም ጥሩ ነበር፣ ከዚያም ባሻገር ፣በድንኳን ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ምግብ ቤቶች ፣ጥብስ በዳቦ እስከ 40 ዶላር መሸጣቸው አስገራሚ ከመሆኑም በላይ የራበው ሰው ሳይወድ በግዱ እንዲበላ ተደርጓል።
ለዚህም ከስዊዘርላንድ የመጣው ጋዜጠኛ እያደር አዲስ እንደአጋጣሚ ሆኖ የእዚህ እድል ተጠቃሚ ነበር ፣ ለአንድ ምግብ 40 ዶላር ማውጣት ምን የሚሉት ዘረፋ ይሆን፣?
ማጠቃለያ
እነዚህን አስተያየቶች የምንሰጠው ከክፋት አንጻር አይደለም ፣ምናልባትም መጥፎ አመለካከት ያላችሁ ሰዎች በመጥፎ ተርጉማችሁት የሰዎችን ሃሳብ ወደ ገደል ልትከቱት ትችሉ ይሆናል፣ እኛ ግን እንዲታረሙ ብለን ነው ይህንን አይነት አስተያየት የምንሰጠው ፣ በዚህም መሰረት እኛ ባየነው መሰረት እንደ እናት ጓዳ አይነቶቹን ቤት ለማዘጋት ቀላል እንደሆነ የተረዳንበት መነግድ አለ ይሄውም በአጠቃላይ ንጽህና የሚባለው እገር ፈጽሞ ከውስጣቸው ያልበቀለ ነው ፣ታዲያ ለከተማቸው የኢንስፔክሽን ሴክተር ምን እንደተፈጸመ ብንጠቁም ምን ሊፈጠር እንደሚችል ማንም አያዳግተውም፣ ስለዚህ መጠፋፋት አይጠቅመንም ፣መተራረም ግን የሁላችንም ድርሻ ቢሆን ካሰብንበት የመልካም ደረጃ ልንደርስ እንችላለን፤
ስለዚህ ሁላችሁንም በወቅቱ ለነበራቸሁ የፌደሬሽኑ እንግዶች፣ የድላስ ቴክሳስ ነዋሪዎችም ሆናችሁ የክብር እንግዶች እንኳን በሰላም አገናኝቶ በሰላም ወደ ሃገራችን መለሰን ስንል፣ ለሚቀጥለው አመት ለሚከናወነው እግር ኳስ ጨዋታ ፌደሬሽኑ ሚድዌስ ማድረግ እንዳለበት ፣ መጠየቅም ብቻም ሳይሆን ግዴታም እንዳለበት እዚህ ላይ በግልጽ እናስቀምጣለን፣ በየአመቱ በሙስና በተሞላበት መንገድ በተደጋጋሚ ዲሲ አትላንታ ፣እና ሌሎች ስቴቶኦች ተደርገዋል፣ አሁን ደግሞ ቀጣዮቹ ፣ምንም ያልተደረገባቸው ፣ምንሶታ እና ኦሃዮ አሉ፣ እነርሱ የማይችሉ ከሆነ ደግሞ ችካጎ ይችላል፣ስለዚህ እነዚህ አገሮች ምንም አድርገው አያውቁም ብቃት አላቸው ፣የሰው ሃይል አላቸው ሆኖም ግን ለፌደሬሽኑ አመራሮች የሚሰጡት የሙስና ገንዘብ የላቸውም ፣ችካጎ ካዘጋጀ 10 አመት ሆኖታል አሁንም በድጋሚ ማዘጋጀት ይችላል ፣ይህ በደጋሚ ሊታሰብበት ይገባል። የፌደሬሽኑ አመራሮች ከፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ይውጡ የሚለውን አስተያየታችንን ስንሰጥ ፌደሬሽኑንም ከግንቦት ሰባት ፣ኢሳት እና አባይ ሚዲያ እጅ እንዲላቀቅ አሁም ጥሪ እናቀርባለን። በሌላም በኩል ከዲሲ እየመጡ ባንዲራ እንነግዳለን እያሉ የሚመጡትን የዲሲ ግብረ ሃይልን ከአሁን በኋላ ድንኳን እንዳይሰጣቸው ማእቀብ ቢጣል ፣ይህም የሚሆበት ምክንያት እነርሱ ለሰላም ሳይሆን የሚመጡት ለመደባደብ ስለሆነ ፣በዚህ አመት በዳላስ ያደረጉት ድብደባ ምስክርነት ሊቀርበባቸው የሚችል መሆኑ ከግንዛቤ ውስጥ እንዲገባ በአክብሮት እንገልጻለን።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar