www.maledatimes.com የሽብር ወንጀልና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎችን በመክሰስና በማሰፈረድ የሚታወቁት አቃቤ ሕግ ብርሀኑ ወንድማገኝ ተሰናበቱ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የሽብር ወንጀልና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎችን በመክሰስና በማሰፈረድ የሚታወቁት አቃቤ ሕግ ብርሀኑ ወንድማገኝ ተሰናበቱ

By   /   July 21, 2018  /   Comments Off on የሽብር ወንጀልና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎችን በመክሰስና በማሰፈረድ የሚታወቁት አቃቤ ሕግ ብርሀኑ ወንድማገኝ ተሰናበቱ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 14 Second
አቃቤ ሕግ ብርሀኑ ወንድማገኝ

አቃቤ ሕግ ብርሀኑ ወንድማገኝ

ዋዜማ ራዲዮ- የፌደራሉ ዋና ዓቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ለዓመታት በርካቶችን ባልተጨበጠ የሽብር ወንጀልና ተያያዥ ከፍተኛ ወንጀሎችን በመክሰስና በማሰፈረድ የሚታወቁትን ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝን ከኃላፊነት በማሰናበት በቦታቸው አቶ ፍቃዱ ፀጋን መሾሙን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዋና ዓቃቤ ህጉ አቶ ብርሃኑ ፀጋዬ አቶ ብርሃኑ ሐምሌ 12፣ 2010 ዓ.ም የመስሪያ ቤታቸውን የለውጥ ሂደት (ሪፎርም) በተመለከተ የተለያዩ ርምጃዎችን ለስራተኞቹ ያስተዋወቁ ሲሆን በአቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ ሲመራ የነበረውን ጭምሮ የበርካታ ዳይሬከቶሬት ኃላፊዎችን በማንሳት በአዲስ እንደተኩ የውስጥ ምንጮች ለዋዜማ አረጋግጠዋል፡፡
አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ ለዓመታት የሽብርና የተደራጁ ድንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን የዚሁ የፌደራሉ መንግሰት ዋና ዐቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ቁልፍ ሰዎች አንዱ እነደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡

በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችንና አባላቶቻቸውን እንዲሁም የመብት አቀንቃኞችን፣ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪዎችንና የተለያዩ ግለሰቦችን የመንግሰት አቃቤ በመሆን በተለያየ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች በሽብርና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ክስ በመመስረትና በማሰፈረድ ይታወቃሉ፡፡

እንዲሁም በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በበጎ የማይንሳው አቶ ብርሃኑ ወንድምአገኝ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር የሚገኙ ተከሳሾችን የፍርድ ሁደት በማጓተትና በእስር የሚገኙ ታራሚዎች የመብት ጥሰት እዲፈጸምባቸው ተደጋጋሚ ምክንያት ይሆኑ እንደነበርም ወቀሳ ሲሰማባቸው ይሰማል፡፡
ዋና ዓቃቤ ህግ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ በጻፉት የሹመት ደብዳቤ አቶ ፍቃዱ ጸጋ የተባሉ ነባር የህግ ባለሙያ አቶ ብርሃኑ ወንድምአገኝን እንዲተኩ ማድረጋቸውንና አቶ ተመስገን ላጲሶን በምክትል ዳይሬከተር መሾማቸውን የዋዜማ ምንጮች ገልጸዋል፡፡
ሌሎች በርካታ ሀላፊዎችም በአዳዲስ የተተኩ ሲሆን ለሹም ሽር ምክንያት የሆነው የቀደሙት ሀላፊዎች የፖለቲካ ፓርቲ አባላት የነበሩ በመሆናቸው ጭምር እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ስር የሚቀጠሩ ዓቃብያነ ህጎች ከዚህ በኋላ ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባልነት ነጻ መሆን እንዳለባቸው የሚያስገድድ ድንጋጌ የያዘ መመሪያ መውጣቱ ታውቋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar