www.maledatimes.com ፍቃዱና ባለ ካባ (ከመድረክ ተዋናይ ማንያዘዋል እንደሻው) - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ፍቃዱና ባለ ካባ (ከመድረክ ተዋናይ ማንያዘዋል እንደሻው)

By   /   August 3, 2018  /   Comments Off on ፍቃዱና ባለ ካባ (ከመድረክ ተዋናይ ማንያዘዋል እንደሻው)

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 21 Second

ስለ ጽሁፉ ማለዳ ታይምስ ሚዲያ ግሩፕ ምስጋናን ያቀርባል

ዳግማዊ ምኒሊክ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪ እያለሁ በአራት ኪሎ ስመላለስ ነበር ፍቃዱን አየው የነበረው፡፡ ዘናጭ አኪያሄዱ፣ የሚያውቁት ሰዎች “”ቻርሊ!” እያሉ ሲጠሩትና በቄንጥ ሰላምታ እየሰጣቸው ሲያልፍ የህልም ያህል ትውስ ይለኛል – ፓርላማ አካባቢ፡፡ እናም ስገምት (ወይስ በኋላ ራሱ ነግሮኝ ይሆን?) ታዋቂውን የፊልም ጥበበኛ ቻርሊ ቻፕሊንን እያስመሰለ ሲጫወት ሳይሆን አይቀርም ይሄን ስም ያገኘው፡፡ በ67 የመንግስቱ ለማ “ባለካባና ባለዳባ” በተፈሪ ብዙአየሁ አዘጋጅነት በሀገር ፍቅር ቴአትር ሲታይ፣ ወንድሜ ስዩም ተፈራም ይጫወትበት ነበርና ጋብዞኝ ሳየው (ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት ቴአትር ሳይሆን አይቀርም) ፍቃዱና ሱራፌል ጋሻው ባሬስታና አስተናጋጅ ሆነው ይጫወቱ ነበር (በነገራችን ላይ ነቢይ መኮንንም በዚህ ድራማ ውስጥ ተውኗል)፡፡
አንድ ጊዜ ፍቃዱ ሲያጫውተኝ፣ ተፈሪ ብዟየሁ ለሚጫወተው ገጸ-ባህሪ ሁለት ሳንድዊች ይቀርብና አንዱን በልቶ አንደኛውን ስለሚተወው ፍቃዱና ሱራፌል ቴአትሩ ሲያልቅ ሊበሉት ያቅዳሉ (እንግዲህ ገና ስራ ያልያዙ ወጣቶች በመሆናቸው መጓጓታቸው አያስገርምም)፡፡ ታዲያ በትዕይንቱ መጨረሻ መብራቱ ጠፍቶ ሲበራ ሳንድዊቹ የለም፣ እናም ይሄ ግራ የሚያጋባ ጉዳይ በየሳምንቱ ይደጋገማል፡፡ አንድ ቀን ግን በዛው ሰዓት ላይ መብራት ሲበራ አንድ ልጅ ተወርውሮ ባሬስታው የሚቆምበት ባንኮኒ ጀርባ ይደበቃል፣ ሳንድዊቹንም ይዟል፡፡ “ሌባው” ታወቀ! ዋናውን ገጸ-ባህሪ ገዝሙን በልጅነቱ ይጫወት የነበረ ትንሽ ልጅ ሲሆን፣ መብራት መጥፋቱን ጠብቆ ይገባና፣ ከመብራቱ በፊት ሳንድዊቹን ሞጭልፎ ይወጣ ነበር (አሁን ታዋቂ ሰው ሆኗል፣ ስሙን እንዝለለው)፡፡ መብራት እስከሚጠፋ ድረስ ልጁ መውጣት ስለማይችል፣ ሁለተኛ እንዳይለመደው ከሱራፌል ጋር እንዴት አርገው “ትምርት እንደሰጡት” ፍቄ ሲያወራልኝ በሳቅ ነበር የፈረስኩት፡፡ በጣም ከማደንቃቸው ጥቂት ጨዋታ አዋቂዎች መሀል አንዱ ፍቄ ነበር!Image may contain: 1 person, standing
ዋና ገጸ-ባህሪ ይዞ መጫወት የጀመረውና ችሎታውን ያስመሰከረው በአያልነህ ሙላቱ ተጽፎ በአባተ መኩሪያ የተዘጋጀው “እሳት ሲነድ” ሲሆን፣ ትንሽ ቀደም ብሎ ከሱራፌል ጋሻው፣ ሥዩም ተፈራ፣ አላዛር ሳሙኤል፣ ወለላ አሰፋ፣ ፍቅርተ ጌታሁን፣ ተሾመ አንዳርጋቸው፣ ፋንቱ ማንዶዬና ከሌሎችም ተዋንያን ጋር በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቴአትር ቤት (ዛሬ አ.አ. ቴአትርና ባህል አዳረሽ) በተፈሪ ብዟየሁ አማካኘነት ቋሚ ተቀጣሪ ሆኖ ነበር፡፡
አስራ ምናምን ዓመታት ስንዘል 83 ላይ እንደርሳለን፣ እናም አባተ መኩሪያ ከስራ አስኪያጅነት ሲነሳ፣ የተፈጠረው ሁኔታ ስላልተመቸው ፍቃዱ በገዛ ፍቃዱ ስራውን ለቆ ወጣ፡፡ ሥራ አስኪያጅ እንደሆንኩ የባህል ሚኒስቴርን ም/ሚኒስትር ጠይቄ በብሄራዊ ቴአትር እንደተቀጠረ የ”ባለካባና ባለዳባ”ን ልምምድ ጀመርን፡፡ በተዋንያን ምደባ (casting) ከተቸገርኩባቸው ጊዜያት አንዱ ይሄ መሆን አለበት፡፡ በንባብ ላይ እያለን ፍቃዱ ለሁለቱም ዋና ገጸ-ባህሪያት ግሩም ሆኖ ይስማማል፡፡ `ገዝሙ` የተባለው ገጸ-ባህሪ መንግስቱ ለማ ከራሳቸው ባህሪ ተነስተው የጻፉት ረጋ ያለ፣ በቁሳቁስ የማይደለልና ለማተቡ የሚሞት፣ “እንደወይራ ሽመል የማይጎብጥ የማይለመጥ” ግትር ሲሆን በተቃራኒው `ተጫኔ` አድርባይ፣ ወሽካታና ለጥቅሙ ሲል ማንንም የሚሸጥ ሞላጫ ነው፡፡ የትኛውን እንዲጫወት እንደምፈልግ ፍቃዱ ሲጠይቀኝ፣ ለሁለቱም ግጥም ብሎ ስለሚስማማ ለመወሰን እንደተቸገርኩ ስነግረው “እንግዲህ ምን ልሁንልህ ማኔ፣ መቼም ለሁለት አልሰነጠቅ!?” ብሎ ያሳቀኝን አስታውሰዋለሁ፡፡
ፍቃዱ በጣም የሚያደንቀው ተዋናይ ወጋየሁ ንጋቱ ነበር፣ እናም ወጋየሁ ሲለየን የነበረውን ክፍት ቦታ ሞልቶ፣ ነገስታትን ብቻ ሳይሆን ሌሎችን በርካታ ገጸ-ባህሪያት ሲጨወት፣ እውነተኛው “የመድረኩ ንጉስ” ሆኖ ዘልቋል! በጸጋዬ ገ/መድህን “የከርሞ ሰው” ውስጥ `ሞገስ`ን ሆኖ ሲጫወት ባየሁት ጊዜ “በአንድ ገጸ-ባህሪ ነፍስ ውስጥ፣ የዚህን ያህል ጠልቆ መግባት ይቻላል ወይ?” ብዬ እንድጠይቅ አስገድዶኛል፡፡
ከፍቄ ጋር ገና ብዙ የመስራት ህልም ነበረኝ፣ ግና አልሆነምና ምን ይደረጋል!?
የጊዜ ጉዳይ ነውንጂ ሁላችንም ወደዛው ነንና፣ እስክንገናኝ እረፍትህን የሰላም ያድርግልህ ፍቄ!

Image may contain: 2 people, selfie and closeup
Image may contain: one or more people and people standing
Image may contain: 2 people, people smiling, people on stage and people standingአባተ መኩሪያና ፀጋዬ ገ/መድህን ….ቴዎድሮስ ቴያትር ..ማዘጋጃ ቤት
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar