www.maledatimes.com ዓቃቤ ሕግ በቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ዓቃቤ ሕግ በቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠው

By   /   August 23, 2018  /   Comments Off on ዓቃቤ ሕግ በቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዳይሬክተር ላይ ክስ መሥርቶ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጠው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 9 Second

Source The Ethiopian Reporter
የቀድሞ የኢንሳ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ተወልደ
ታምሩ ጽጌ
ዓቃቤ ሕግ በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ በሚገኙት የቀድሞ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ላይ፣ ክስ እንዲያቀርብና ውጤቱንም እንዲገልጽ ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ትዕዛዙን የሰጠው፣ የፌዴራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን በተጠርጣሪ አቶ ቢኒያም ተወልደና አቶ ሰላም ይሁን አደፍርስ ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናቆ፣ ለዓቃቤ ሕግ እንዲያስረክብ ተሰጥቶ የነበረውን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለመፈጸሙ ምክንያት ነው፡፡

ፍርድ ቤቱ ከፖሊስ የምርመራ መዝገቡ ለዓቃቤ ሕግ አለመሰጠቱንና የተጻፈ ደብዳቤም እንደሌለ ገልጿል፡፡ ድርጊቱ ተገቢ አለመሆኑንና ለወደፊቱም መደገም እንደሌለበት መርማሪ ቡድኑን በችሎት አስጠንቅቋል፡፡ መርማሪ ቡድኑ በተፈቀደለት አሥራ አንድ ቀናት ውስጥ ምንም ሳይሠራ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቁ ተገቢ አለመሆኑን ጠቁሞ፣ የምርመራ መዝገቡን ለዓቃቤ ሕግ አሳልፎ እንዲሰጥ በችሎት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

አቶ ቢኒያም በጠበቃቸው አማካይነት ባቀረቡት ክርክር እንደተናገሩት፣ ከተያዙበት ጊዜ አንስቶ በፍርድ ቤት የቀረበባቸው የተጠረጠሩት ወንጀል ሥልጣንን ያላግባብ መገልገልና ሀብት ማከማቸት ነው፡፡ ይኼንን ለማጣራት ደግሞ ለመርማሪ ፖሊስ ከበቂ በላይ ጊዜ ስለተሰጠው ምርመራውን ማጠናቀቁን ፍርድ ቤቱ ተገንዝቦ፣ ለዓቃቤ ሕግ እንዲያስረክብ ትዕዛዝ የሰጠ ቢሆንም ትዕዛዙን አለማክበሩን አስረድተዋል፡፡

በመሆኑም ለመርማሪ ቡድኑ የተሰጠው ጊዜ ከበቂ በላይ ስለሆነና የሚቀረው ሥራ የኦዲት ሪፖርት በመሆኑ፣ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

አቶ ሰላም ይሁንም ለፍርድ ቤቱ እንደገለጹት፣ ከተያዙ ጀምሮ ቃል አልሰጡም፡፡ ይኼ የሚያሳየው ምንም ዓይነት ወንጀል እንደሌለባቸውና ወንጀልም እንዳልተፈጸመ ስለሆነ፣ ነፃ ሆነው የመገመት መብታቸው ተከብሮ በነፃ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡

መርማሪ ቡድኑ ደግሞ የዋስትና  መብት ጥያቄውን ተቃውሞ ተከራክሯል፡፡ ፍርድ ቤቱም የዋስትና ጥያቄውን በማለፍ፣ ከላይ የተጠቀሰውን ትዕዛዝ ለዓቃቤ ሕግና ለመርማሪ ፖሊስ ሰጥቷል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar