www.maledatimes.com የአንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍ ሰገድ ይልማ 6ተኛ የሆነው እና “የፓለቲካ አሽሙር” የተሰኘው መፅሐፍ ይመረቃል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የአንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍ ሰገድ ይልማ 6ተኛ የሆነው እና “የፓለቲካ አሽሙር” የተሰኘው መፅሐፍ ይመረቃል።

By   /   November 24, 2018  /   Comments Off on የአንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍ ሰገድ ይልማ 6ተኛ የሆነው እና “የፓለቲካ አሽሙር” የተሰኘው መፅሐፍ ይመረቃል።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 36 Second

የአንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ አጥናፍ ሰገድ ይልማ 6ተኛ የሆነው እና
“የፓለቲካ አሽሙር” የተሰኘው
መፅሐፍ ቅዳሜ ህዳር 15ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ በ8ሰዓት ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከፍ ብሎ በሚገኘው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መፃሕፍት እና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ(ወመዘክር) አዳራሽ ይመረቃል።
አጥናፍ ሰገድ ይልማ ከ 1952 -1972 ድረስ ባሉት ዓመታት በማስታወቂያ ሚኒስቴር ውስጥ ከ ጀማሪ ዘጋቢነት እስከ ዋና አዘጋጅነትየሠሩ ሲሆን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅም ነበሩ።
ከ 1972 ዓ.ም በሁዋላም በተለያዩ መንግሥታዊ ተቋማት በሐላፊነት አገልግለዋል።
– ጋሽ አጥናፍሰገድ ከአንጋፋ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ባቋቋሙት ልሣነ ሕዝብ ጋዜጣ እና መፅሔት ከፀሐፊነት እስከ አዘጋጅነት ሠርተዋል።
በጦብያ መፅሔት ላይም አባ ገምባው በተሰኘ የብዕር ሥም በርካታ ፅሁፎችን አስነብበዋል።
ጋሽ አጥናፍ መፅሐፍ ፅፈው አሣትመው ለንባብ ያበቁት ከ 70ኛ ዓመታቸው በሁዋላ ነበር።
በጋዜጦች እና መፅሔቶች ላይ በብዕር ሥም የሚፅፉትን የሚያነቡ ወዳጆቻቸው መፅሐፍ እንዲፅፉ ቢመክሯቸውም ጋሽ አጥናፍሰገድ ግን አልተቀበሏቸውም። ምክንያታቸውም ከታላላቅ የሐገራችን ደራሲዎች እኩል እንዴት ደራሲ ተብዬ እጠራለሁ የሚል ከአክብሮት የመነጨ ፍርሐት ነበር።
በ 1989 ዓመተ ምህረት ያለ ክስ ያለ ፍርድ ታስረው በመጨረሻም በስህተት ነው ተብለው ነፃ በተለቀቁበት የ1 ዓመት ከ4ወር የእሰር ጊዜያት እንደሳቸው በእስር ላይ ሆኖ ላገኙት ለጀግናው አሊ በርኬ ቃለመጠይቅ አድርገው እና ታሪኩን ፅፈው ከእስር ሲፈቱ በጦብያ መፅሔት ላይ በ5 ተከታታይ ክፍል ለንባብ እንዲበቃ በማድረግ የጀግናውን ታሪክ ለሕዝብ አስተዋውቀዋል።
በነዛ የእስር ጊዜያት ውሥጥም “የበደል ካሳ” የተሰኘ ልብ ወለድ መፅሐፍም ፅፈዋል።

ጋሽ አጥናፍ ሰገድ የጋዜጠኝነት እና የፅሁፍ ሥራን መሥራት ከጀመሩ ከ 50ዓመታት በሁዋላ ፣ ዕድሜያቸው 70 ካለፈ በሁዋላ ለመጀመሪያ ጊዜ “የበደል ካሳ ” የተሰኘ መፅሐፋቸውን ደራሲ አጥናፍ ሰገድ ይልማ ብለው ለሕትመት አበቁ።
ከዚህ መፅሐፍ በሁዋላ
-የአቤቶ ኢያሱ አነሳስ እና አወዳደቅ
-የእንስሳት ዓመፅ እና ድርድር
– የሕይወቴ ሚስጥር (ግለ ታሪክ)
-ሐገር የፈታ ሽፍታ
የተሰኙ መፅሐፍትን ለንባብ አብቅተዋል።

አሁን 82 ዓመት የደፈኑት አንጋፋው ጋዜጠኛ እና ደራሲ በቅርቡ ለአንባቢያን ለማድረስ ያዘጋጇቸው
-የታሪክ ውርስ እና ቅርስ (ራስ አበበ አረጋይ)
-የሉዓላዊነት እና የመንግሥት ጥያቄ በኢትዮጵያ
የተሰኙ መፅሐፎችም አሏቸው።

ለመፅሐፍ ወዳጆች በሙሉ
አንጋፋ ደራሲያን በአፃፃፍ ስልቱ እና በሚያስተለልፈው መልዕክት ድንቅ በማለት የአድናቆት አስተያየታቸውን የቸሩት ከወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ጋር የሚናበበው “የፖለቲካ አሽሙር” መፅሐፍ የምርቃት ሥነሥርዓት ላይ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችሁዋል።

ቅዳሜ ህዳር 15 ከቀኑ በ8ሰዓት ወመዘክር አዳራሽ እንገናኝ። by Azeb worku

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar