www.maledatimes.com በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ለደረሰው አደጋ ለተጎጂ አካላት እና ቤተሰቦቻቸው አለም አቀፍ የህግ ጥብቅና ለመስጠት ጠበቃ ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ ገለፁ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ለደረሰው አደጋ ለተጎጂ አካላት እና ቤተሰቦቻቸው አለም አቀፍ የህግ ጥብቅና ለመስጠት ጠበቃ ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ ገለፁ!

By   /   March 13, 2019  /   Comments Off on በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ለደረሰው አደጋ ለተጎጂ አካላት እና ቤተሰቦቻቸው አለም አቀፍ የህግ ጥብቅና ለመስጠት ጠበቃ ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ ገለፁ!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 51 Second


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302

ፍሬድማን ሩቢን እና የህግ ባለሙያው ሼክስፒር የህግ ቢሮ

ሲያትል፡ አሜሪካ።

ማርች 13 ቀን፣ 2019 ዓ.ም

ከቦይንግ አውሮፕላን ካምፓኒ በጥቂት ርቀት ላይ የሚገኘው፤ ፍሬድማን ሩቢን የህግ ቢሮ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ህይወታቸው ያጡትን ቤተሰቦች የሚታደግ መሆኑን አሳወቀ። ፍሬድማን ሩቢን የህግ ቢሮ – በተለይ በኢትዮጵያ፣ አፍሪቃ የሚገኙ ዜጎች ፍትህ እንዲያገኙ ለማድረግ፤ ከኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያው ሼክስፒር ፈይሳ ጋር ተስማምተዋል።

 የመስሪያ ቤቱ መግለጫ እንዳሳወቀው ከሆነ፤ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 በደረሰው አደጋ፤ የተሰማውን ጥልቅ ህዘን ገልጾ፤ ቦይንግ ካምፓኒ አስፈላጊውን ክፍያ እንዲያደርግ፤ ከተጎጂ ቤተሰቦች ጋር አብሮ የሚሰራ መሆኑን ነው – መግለጫው ያብራራው።

ፍሬድማን ሩቢን የህግ መስሪያ ቤት፤ ቦይንግ 737 Max ከሚሰራበት  ሬንተን ከተማ፣ ዋሺንግተን ክፍለ ግዛት – በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል። ከዚህ በፊት በኢንዶኔዥያ ለደረሰው የቦይንግ 737 Max፤ የጉዳት ሰለባዎች የህግ ጠበቃ ሆነን ሰርተናል። እንደ ህግ ቢሮው መግለጫ ከሆነ፤ ለደረሱት አደጋዎች አንደኛው መንስኤው የቦይንግ ስራ ጉድለት ሲሆን፤ “እኛ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች አስፈላጊው የጉዳት ካሳ እንዲከፈላቸው እናስደርጋለን” ብሏል መግለጫው።

ከዚህ በመቀጠል ፍሬድማን ሩቢን የህግ መስሪያ ቤት፤ የሰጠውን ማብራሪያ ቀጥሎ አቅርበናል።

በርግጥ ምን እንደተፈጠረ እውነቱን መፈለግ ያስፈልጋል?

ሁሉም የአውሮፕላን አደጋዎች ከደረሱ በኋላ፤ ምንግዜም ቢሆን ምርመራ ይደረጋል። በአንዛኛው ግን ይህ ምርመራ የሚካሄደው በአየር መንገዱና በአውሮፕላን ፋብሪካው ተወካዮች፤ ወይም የሁለትዮሽ ስምምነት ነው። ይህን ሁኔታ… አንዳንዶች “የዶሮ ቤትን ለመጠበቅ ቀበሮን ዘበኛ ማድረግ እንደማለት ነው።” ይላሉ። ብዙውን ግዜ አደጋው የደረሰባቸው ቤተሰቦች፤ በምርመራው ሂደት ላይ ተሳታፊ አይሆኑም። የአቪዬሽን ጠበቃ በመቅጠርና ህጋዊ ውል በመፈጸም ማንኛውም ቤተሰብ የምርመራውን ውጤት በቅርብ የማወቅ እድል ያገኛሉ። ህጋዊ ውክልና ካገኘን ደግሞ፤ አስፈላጊ የሆኑ ጥያቄዎችን እናቀርባለን። በጥያቄያችንም መሰረት…አየር መንገዱም ሆነ የቦይንግ ካምፓኒ መልስ የመስጠት ግዴታ ይኖርባቸዋል። ይህ ብቻም አይደለም። የራሳችንን የምርመራ ልዑካን ቡድን አባላት፤ የአውሮፕላኑ አደጋ የደረሰበት ቦታ ድረስ እንልካለን። በፍንዳታው የደረሰውን አደጋ እና የጥገና መዝገቡን እናጠናለን፤ እናም ከፍንዳታው በስተጀርባ ምን እንደተፈጠረ እውነትን እንፈልጋለን።

ይህ በሌላ ቤተሰብ ላይ፤ በጭራሽ ሊደርስ የማይገባው ነው!

በዚህ አመት በቦይንግ 737 ማክስ ላይ ተመሳሳት ሲደርስ፤ ይህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ላይ የደረሰው አደጋ ሁለተኛው መሆኑ ነው። የመጀመሪያው አደጋ በ Lion Air ላይ ሲደርስ፤ የችግሩ መንስኤ የቦይንግ 737 ማክስ መሆኑን አየር መንገዱ ገና አላወቀም ነበር። የአውሮፕላኑን የበረራ ፍሰት ለመቆጣጠር የሚያግዘው የበረራ ሰነድ (flight manual) ሊኖራቸው እንደሚገባ ለLion አየር መንገድ ስላልተነገራቸው፤ ተመሳሳይ የሆነው አደጋ በኢንዶኔዥያ ደረሰ። ሆኖም በ Lion አየር መንገድ ላይ አደጋው ከደረሰ በኋላ፤ ለሁሉም አየር መንገዶች የበረራ ማኑዋል መስጠት እንዳለበት የፌዴራል አቪዬሽን አስተዳደር ትዕዛዝ ሰጥቶታል። በ Lion አየር መንገድ ላይ አደጋ ከደረሰ በኋላ፤ ይህ አዲስ የበረራ ማኑዋል ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ተሰጥቶ ሊሆን ይችል ይሆናል። ይህ ብቻ ግን በቂ አይደለም። ከዚህ አደጋ በኋላ፤ ተመሳሳይ የሆነ አደጋ እንዳይደርስ እና ለውጥ መደረጉን እርግጠኛ መሆን ያስፈልጋል።

ይህ አይነቱ አደጋ እንዳይደገም ወይም በሌላ ቤተሰብ ላይ እንዳይደርስ መሆን አለበት።

ሃላፊነትንም መውሰድ ያስፈልጋል!

ማንኛውም በረራ ምቹ መሆኑ ቀርቶ አደጋ ካጋጠመው አየር መንገዱ፤ ወይም የአውሮፕላኑ ማምረቻ ካምፓኒ በጋራ ወይም በተናጠል ሃላፊነት ሊወስዱ ይገባቸዋል። አንዳንድ ግዜ አየር መንገዶች ወይም የአውሮፕላን አምራቾች የነሱን ጥፋት በሌላ ሰው ላይ ማላከክ ይፈልጋሉ። እውነቱን በማጋለጥ ይህን እናስቆማለን። ይህ አይነቱን ምግባር የምናስቆመው፤ አየር መንገዱ ወይም የአውሮፕላን አምራቹ ለፈጸሙት ጉዳት እና ለጠፋው ህይወት፤ ለቤተሰቦች አስፈላጊውን የካሳ ክፍያ እንዲፈጽሙ በማድረግ ነው። ከዚያ በኋላ በርካሽ እና በአቋራጭ መንገድ ማምለጥ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል። አየር መንገዱ ወይም አውሮፕላን አምራቹ ሃላፊነት የማይወስዱ ከሆነ ግን፤ በህግ ሃላፊነት እንዲወስዱ እናደርጋቸዋለን።

ፍሬድማን ሩቢን የህግ ቢሮ መግለጫውን ሲያጠቃልል፤ “ቤተሰብዎን በዚህ አደጋ አጥተው ከሆነ፤ ልባዊ ሃዘናችንን እንገልጻለን።” በማለት በዚህ አደጋ ህይወታቸው ላለፉት ሰዎች ሙሉ ክብር የሚሰጥ መሆኑን አሳውቋል።

ተያይዞ የደረሰን ዘገባ እንደሚያመለክተው ከሆነ፤ ፍሬድማን ሩቢን የህግ ቢሮ ከኢትዮጵያዊው የህግ ባለሙያ ሼክስፒር ፈይሳ ጋር በመሆን የተጎጂ ቤተሰቦች ፍትህ እንዲያገኙ አብረው ለመስራት ተስማምተዋል፤ ጉዳዩንም በቅርበት በመከታተል ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል። በቅርቡም ወደ ኢትዮጵያ እና ናይሮቢ በማምራት አደጋው ከደረሰባቸው ቤተሰቦች ጋር ተገናኝተው ለመነጋገር ተስፋ ያላቸው መሆኑን- የህግ ሙያተኛ የሆኑት ሼክስፒር ፈይሳ ገልጸውልናል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar