www.maledatimes.com ርእሰ አንቀጽ የትግራይን ህዝብ ባላሰበው መንገድ ቅጽበታዊ ውንብድና ላይ መውሰድ እና ማሳሰብ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  AFRICA  >  Current Article

ርእሰ አንቀጽ የትግራይን ህዝብ ባላሰበው መንገድ ቅጽበታዊ ውንብድና ላይ መውሰድ እና ማሳሰብ

By   /   June 15, 2019  /   Comments Off on ርእሰ አንቀጽ የትግራይን ህዝብ ባላሰበው መንገድ ቅጽበታዊ ውንብድና ላይ መውሰድ እና ማሳሰብ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 0 Second

ባሳለፍነው ሳምንት የትግራይ ክልል መስተዳድር ፕረዚደንት የሆኑት አቶ ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ለመገናኛ ብዙሃኖች እንዳሳሰቡት ከሆነ በብዙዎች አእምሮ ውስጥ ጥልቅ እሳቤ እንዲገባ አድርገዋል።

ይኸውም የህወሃት አስተዳደር ወሰ ስልጣን ከመምጣቱ በፊት የሰራውን የቤት ስራ በሃገሪቱ ላይ በፋ የዘረኝነት እና የሃገር መገነጣጠል ሃሳብ ከፈጸሙ በኋላ እንደገና በድጋሜ በስልጣን ዘመናቸው ከሃያ ስምንት አመታት ቆይታ በኋላ የትግራይ ህዝብ ለመገንጠል ጥያቄ ለማንሳት እየተገደደ ነው ብሎ ሃሳብን በጨረፍታ ለማቅረብ መሞከር ምን ያህል በስልጣን ላይ የነበሩት አመራሮች የስልጣን ጥማት እና የህዝብን በመከፋፈል ስሜት ውስጥ ቅራኔዎችን መውደዳቸውን የሚያሳይ መሆኑን ማወቅ ይቻላል።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በዘረኝነት የተራመደ በየትኛውም የዘር ግንድ ባይኖርም ነገር ግን ላለፉት ሃያ ስምንት አመታት የተመራንበር አስተዳደር የህብረተሰብን በዘረኝነት አረንቋ ውስጥ ከቶ ብዙዎችን በዘር ግንዳቸው እንዲያስቡ አቅጣጫ ያስቀየረበት ሁኔታ እንደነበር ማንም አይረሳውም ይህም ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ህዝብ ለብቻው በትግራይ ህዝብ ላይ ጥቃት እየፈጸ መ ነው የሚለው አሉባልታ በማንኛውም ማህበረሰብ ተቀባይነት ባይኖትረውም ህዝቡ በፍቅር ፣በአንድነት በመተሳሰብ እና በስጋዊ ዝምድናው እና በጋብቻው ተባብሮ የሚኖር አንድ ህዝብ መሆኑን ማስተዋል የተሳናቸው የስልጣን ጥመኞች ድምጽ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል።

በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ማንም ማህበረሰብ ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ያልተዛመደ ፣ያልተጋባ ወይንም ያልተዋለደ የለም ስለዚህ ምንም ይሁን ምን የኔ ዘር ከአንተ ዘር ይበልጣል ተባብሎ የዘርን ብልጫ ለማሳየት እና አንዱን ከአንዱ ማሳነ የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜት ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶች አጀንዳ በመሆኑ ምክንያት ህወሃትም ሆነ ኦነግ ላለፉት አርባ እና ሃምሳ አመታት ሲሰሩበት ቆይተዋል ፣ ያልተፈጠሩ ልዩነቶችን ፈጥረው በልዩነቶች ህዝቦችን እንዲያምኑ አድርገዋቸዋል ፣ ብዙ ንጹሃን ዜጎች እንዲጠፉ ምክንያት ሆነዋል፣ ከተጠያቂነት ባያድናቸውም ፣ ለስልጣን ጥማታቸው ጠቅሟአቸው ሊሆን ይችላል ይህ ግን ሃገርን አያድንም ህዝብን መከፋፈል ከአሁን በኋላ ለማንም አይጠቅምም እራስን ከሌሎች አስበልጦ በማየት ለእኔ ማህበረሰብ ትልቅ ትኩረት ይሰጠኝ ብሎ ማሰብ ማንንም ከማንም በተለያየ ደረጃ ሊያስተያይ አችልም። ይልቁንም ትግራይ ብትገነጠል ተጠቃሚው ማን ነው የሚለውን እውነተኛ ማንነቱን የሚገልጸው ህዝብ ወሳኙ እርሱው የትግራይ ህዝብ ሊሆን ይችላል የሚለው ነገር ሊታሰብ ይችላል ብሎ ማሰብ የማይታሰብ ነው ። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ትግራይ የሚያስብ እንጂ ስለ አመራሮች የሚያስብ ማህበረሰብ አለመሆኑን ሊሰመርበት ይገባል። የትግራይ ህዝብ ምጣኔ ሃብቱም ይሁን ሃገራዊ በጀቱ ከኢትዮጵያ ህዝብ የተሰጠ አመታዊ በጀት እንጂ ከትግራይ ህዝብ ብቻ የተቀነሰ የገቢ ምንጭ የለውም ፣ የትግራይ ህዝብ በግብርና እርሻው ውስጥ ምንም አይነት የሚያራምደው የግብርና ግብአት የለውም ፣ ከደቡብ አቅጣጫም ቢሆን ያለበትን ሁኔታም ሆነ በሰሜን አቅጣጫ ያለበትን መልከአ ምድር መገንዘብ እና ለወደፊቱ ሊኖረው የሚገባውን ሃገራዊ ጠቀሜታም ሆነ አስተዳደራዊ መዋቅር ማስላት እና መገንዘብ ይኖርበታል። ምናልባት ህዝብን በረሃብ ፣በችጋር ፣ እና በድንቁርና ፣ በቁሙ መቅጣት የሚፈልግ ባለስልጣን ህዝቡን ገንጥሎ መውሰድ ይችላል ነገር ግን ፍጻሜው በቁሙ ሞትን በእራሱ ህዝብ እያቃረበ የሚመጣ መንግስት መሆኑን ልብ ሊሉ ይገባል!!

በህዝብ ላይ የሚደረገውን ቅዽጽበታዊ ውንብድና ከዚህ በፊት እንደወሰዳችሁት ለትግል መሳሪያ የተጠቀማችሁበት አይነት መሳሪያ ስለማይሆን ዛሬውኑ ከውሳኔ መድረስ ያለበት የኢትዮፕያ ህዝብ መሆኑን ማለዳ መረጃ ማእከል ያስገነዝባል!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar