www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መግለጫ ወጣ !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መግለጫ ወጣ !!

By   /   April 22, 2020  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበር በሰሜን አሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ መግለጫ ወጣ !!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 12 Second

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስኪያጅን አስመልክቶ ዘሃበሻ በዘገበው ዘገባ ላይ በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማህበር ለአየር መንገዱ ሃሳብን በነጻነት መግለጽን አስመልክቶ የዋና ስራ አስኪያጁ ክስ ውድቅ እንዲያደርገው እና ዋና ስራ አስኪያጁ የመጡበት መንገድ እስከ መጨረሻው የማያስኬዳቸው መሆኑን አክሎ ገልጿል ። በአየር መንገዱ አመራር እና አየር መንገዱ የህዝብን ንብረት በግል በመጠቀም ያደረጉት የሙስና ወንጀል ቀላል የሚባል እንዳልሆነ ሁላችንም የምንረዳው ነው ።

ለዚህም ከተለያዩ አካላት በአየር መንግዱ እንዝላል አሰራር ላይ ያቀረቡልንን መረጃዎች ከማውጣታችን በፊት እና በአለም አቀፍ የበረራ ድርጅቶች ውስጥ ያላቸውን መሪ ተዋናይነት የሚያስናክለውን ይህንን ወንጀላቸውን ከመግለስ የተቆጠበው የዘሃበሻ ሚዲያ ፣ በማለዳ ታይምስ እጅ ውስጥ የሚገኙ መረጃዎች እንዳሉ ሳንገልጽ አናልፍም ። በተለይም በአቶ ሳሙኤል የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ በጀርመን እና በጀርመኑ የኢትዮጵያ አየር መን ገድ እንዲሁም በአቶ ስዩም መስፍን እና ሌሎች ባለስልታናት የተሰራው ድብቅ ወንጀል የሁላችንንም ጆሮ የሰጠ ነው ።

ይህም ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ በመስሪያቤት ውስጥ ይደርስ የነበረውን ወሲባዊ ጥቃት፣ ሙስና እና መድልዎም አስመልክቶ ሰራተኞቹ ያደረሱን መረጃዎች ጥቂቶቹ ናቸው ።

የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ስኮላር እንሰጣለን በማለት ከአዲስ አበባ ወደ ጀርመን እንዲሄዱ በማድረግ ከፍተኛ ገንዘብ የሰሩባቸው እና የጀርመን ኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሳᎂል የዚሁ እጣ የደረሳቸው እና በዚሁ ስራ ከአቶ ስዩም መስፍን ፣ ወዩ ሮባ  እና የአየር መንገዱ አመራር ጋር በጋራ በመሆን ከፍተኛ ምዝበራ ያደረጉ ግለሰቦች ነበሩ ።

የተለያዩ ባለሃብቶችን እንዲባረሩ እና በምትኩ እነዚህ ሰዎች በሃገሪቱ ላይ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ስራ እንዲሰሩ ከተደረጉት ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው ። ሌሎቹንም ስም ዝርዝር በቀጣይ ሪፖርት ማለዳ ታይምስ ይዞ ይቀርባል ።

በአየር መንገዱ ቅዋሜ ያላችሁ ሆነ በሙስና ከስራችሁ የተባረራችሁ የጾታችሁ ጥቃት የተፈጸመባችሁ ሌሎች ሰራተኞችን ጨምሮ  ማናችሁም ኢትዮጵያውያኖች ያላችሁን መረጃ edito@maledatimes.com  መላክ ትችላላችሁ !!

No photo description available.

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar