www.maledatimes.com የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከ90 በመቶ በላይ ህዝብ አስቸኳይ የሆነ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ሲል አሳወቀ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከ90 በመቶ በላይ ህዝብ አስቸኳይ የሆነ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ሲል አሳወቀ።

By   /   June 1, 2021  /   Comments Off on የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ከ90 በመቶ በላይ ህዝብ አስቸኳይ የሆነ የምግብ እርዳታ ይፈልጋል ሲል አሳወቀ።

    Print       Email
0 0
Read Time:35 Second

#Tigray

የተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) በመጋቢት ወር በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ እና ደቡብ ዞኖች ስርጭት ከጀመረ ጀምሮ ለአንድ ሚሊዮን ሰዎች የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ መስጠቱን ገልጿል።

በጥቅምት ወር ላይ በተነሳው ግጭት ሳቢያ በአጠቃላይ 5.2 ሚሊዮን ህዝብ (91 % የትግራይ ህዝብ ማለት ነው) አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልገው WFP አሳውቋል።

ለአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ምላሽ የ203 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

የWFP ቃል አቃባይ ቶምሶን ፒሪ ፥ “በክልሉ ረሃብ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዳይሸጋገር ያሳስበናል” ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ እስከ 2021 መጨረሻ በረሃብ ምክንያት የሰዎች ሕይወት እንዳይጠፋ እና የተጀመረውን የምግብ ድጋፍ አጠናክሮ ለማድረስ የተጠየቀው ገንዘብ በአስቸኳይ ሊቀርብ እንደሚገባ WFP አሳስቧል።

የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሪፖርት : www.wfp.org/news/wfp-reaches-over-1-million-people-emergency-food-assistance-tigray

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar