www.maledatimes.com በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 – ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 – ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

By   /   June 4, 2021  /   Comments Off on በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 – ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

    Print       Email
0 0
Read Time:40 Second

በአማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 – ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

ቢሮ ይህን የገለፀው ዛሬ የ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተናን አስመልክቶ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።

መግለጫዉን የሰጡት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኀላፊ ሙላው አበበ ሲሆኑ የ2013 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሰኔ 25/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎቻቸው ፈተናዉን የሚወስዱበትን ቀን እንዲያሳውቁ ምክትል ኀላፊው አሳስበዋል።

በትምህርት ወደኋላ የቀሩ ተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት እንዲሰጣቸው፤ ተማሪዎች የፈተናውን ቀን አውቀው ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ነው አቶ ሙላው የገለጹት።

ፈተናው በሚሰጥበት ቀንም ኾነ የፈተናው የጥያቄ ወረቀት የማጓጓዝ ሂደቱ ሰላማዊ እንዲኾን በየዘርፉ የሚገኙ የጸጥታ አካላት ኀላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በአማራ ክልል ከ500 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች የ8ኛ ክፍል ፈተናን የሚሰጡ ሲኾን 420 ሺህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ መታወቁን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar