www.maledatimes.com በሱዳን ደርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት የ36 ሰዎች ህይወት አለፈ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በሱዳን ደርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት የ36 ሰዎች ህይወት አለፈ።

By   /   June 7, 2021  /   Comments Off on በሱዳን ደርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ የጎሳ ግጭት የ36 ሰዎች ህይወት አለፈ።

    Print       Email
0 0
Read Time:31 Second

በሱዳን ደቡባዊ ዳርፉር ግዛት በተቀሰቀሰ ግጭት የ36 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 32 ሰዎች መቁሰላቸውንም ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።

ግጭቱ የተከሰተው በደቡባዊ ደርፉር በሚኖሩ ፌላታ እና ቴይሻ በተሰኙ ሁለት ጎሳዎች መካከል በተፈጠረ የመሬት ይገባኛል ግጭት እንደሆነ ዘገባው ጠቁሟል።

በሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት እና በአካባቢው በሚንቀሳቀሱ አማጺ ሀይሎች መካከል የተለያዩ ስምምነቶች ቢደረጉም በአካባቢው ጎሳን መሰረት ያደረጉ ገጭቶች በተደጋጋሚ እየተከሰቱ እንደሆነ ተገልጽል።

የአፍሪካ ህብረት የጋራ ሰላም አስከባሪ ሀይል ካሳለፍነው ጥር ጀምሮ በመውጣቱ የሱዳን ብሔራዊ ጦር አካባቢው ቢቆጣጠርም ግጭቶቹ ሊቆሙ አልቻሉም።

በዳርፉር እ.ኤ.አ 2003 በተከሰተ የጎሳ ግጭት 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ህዝብ የተፈናቀለ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጀምሮ ደግሞ ግጭቶቹ በድጋሚ በማገርሸት ላይ እንደሚገኙ ዘገባው ጠቁሟል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar