www.maledatimes.com በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት የቨርሞንት ክፍለ ሃገር ሴኔተር ፓትሪክ ሌሂ በትግራይ ጉዳይ መግለጫ አውጥተዋል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት የቨርሞንት ክፍለ ሃገር ሴኔተር ፓትሪክ ሌሂ በትግራይ ጉዳይ መግለጫ አውጥተዋል።

By   /   June 7, 2021  /   Comments Off on በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት የቨርሞንት ክፍለ ሃገር ሴኔተር ፓትሪክ ሌሂ በትግራይ ጉዳይ መግለጫ አውጥተዋል።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 18 Second

#Tigray

መግለጫው ሲጀምር “በ1984 እአአ በኢትዮጵያ በተራዘመ ድርቅ ሳቢያ በስፋት በተከሰተው የምግብ እጥረትና በመንግሥት አድላዊ ፖሊሲዎች የተነሳ የደረሰውን ከባድ ረሃብ በዚያም ምክንያት ብዙዎቹ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሰውነታቸው በረሃብ ያለቀ ፤ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የተሰደዱበትን የሚዘገንን ቸነፈር በደንብ አስታውሰዋለሁ”

ቆይቶ ዝናብ መጣል ጀመረ። ስደተኞቹም ወደቀያቸው ተመለሱ። ይሁን እንጂ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሃገሪቱ በየጊዜው ግጭት እና የበቂ ምግብ ዕጦት ተለይቷት አያውቅም ሲሉም የዩናይትድ ስቴትሱ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል አክለዋል።

ዛሬ የትግራይ ህዝብ ዘግናኝ በሆነ ደረጃ ጭካኔ የተመላበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥቃት እየተፈጸመበት ነው ያሉት ሴኔተር ሌሂ ህዝቡ በአጣዳፊነት የሚያስፈልገው የምግብ እርዳታ እንዳይደርሰው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች እንዲሁም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች እየከለከሉ ናቸው” ብለዋል።

“የአሜሪካ እና ሌሎችም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ግጭቱን አቁመው ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የወሰዱት አንዳችም ትርጉም ያለው እርምጃ የለም” ሲሉ አክለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን ወንጀሎች የፈጸሙትን ተጠያቂ እንዲያደርግ የሲቪሎችን ደህንነት እንዲጠብቅ የሰብዓዊ ረድዔት ተደራሽነትን እንዲያረጋግጥ የአሜሪካ መንግሥት ጥሪ አቅርቦለታል በማለት አክለው የኤርትራም መንግሥት በገባው ቃል መሰረት ወታደሮቹ ወደግዛቱ መመለስ ነበረበት ብለዋል።

“ትግራይ ውስጥ የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ በግዴታ ከቀዬ ማፈናቀል፣ ወሲባዊ ጥቃቶች እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በውሃ አቅርቦት ስፍራዎችና በሆስፒታሎችና በመሰል የጤና ማዕከሎች ላይ የሚደርሰውን ውድመት የአሜሪካ መንግሥት አውግዟል።

በአሁኑ ጊዜ ትግራይ ውስጥ የሚታየው አሳዛኝ ዕውነታ የረሃብ፣ በሰብዓዊ ፍጡር ላይ የሚፈጸም ወንጀሎች እና የዘር ማጥፋት አድራጎት ነው ሲሉ የቀጠሉት ሴኒተር ፓትሪክ ሌሂ ይህ እየደረሰ ያለውም በአንድ ምክንያት ነው፤ እሱም የአዲስ አበባና የአስመራ መንግሥታት በመመሳጠራቸው ነው። በሪፖርቶች መሰረት ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ከዳርፉር የባሰ ሊሆን ይችላል ሲሉ አክለዋል።
አስከትለው ትግራይ ውስጥ የሚፈጸመው የግፍ አድራጎት እንዲገታ፥ የምግብ እና ሌላም እርዳታ ተደራሽነት እንዳይከለከል ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ እና የጭካኔ አድራጎት ሰለባ የሆኑት ዜጎች ፍትህ እንዲያገኙ እጠይቃለሁ ብለዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar