www.maledatimes.com maleda times - MALEDA TIMES - Page 252
Loading...
You are here:  Home  >  Articles by maleda times  -  Page 252
Latest

ይድረስ ለምሁሩ ወዳጄ (በድጋሚ የቀረበ)

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ይድረስ ለምሁሩ ወዳጄ (በድጋሚ የቀረበ)

    ይድረስ የኑሮ ውድነት ላነተበህ፣ ኢትዮጽያዊ ጨዋነት ከሰውነት ተራ ላወጣህ ምሁሩ ወዳጄ!… ያቺ ከልደታባዕታ የማታደርስህን ገቢ ለመሸሸህ ከግማሽ እድሜህ በላይ ቆርሰህ እስከፒ.ኤ.ቺ.ዲ ዲግሪ ድረስ ተማርክ፤ለፋህ፣ ደከምክ፡፡ እነሆ ተምረህ ስታበቃ የደመወዝህ ስኬል እንደአሮጌ የባቡር ፉርጎ እየተጎተተ 6 ሺ ብር ላይቆመ፡፡ ከዚህ ላይ መንግስት 35 በመቶ ታክስ ሲያነሳለት፣የጡረታ ፣የአባይ ግድብ መዋጮ ሲቀነጫጨብለት..ከዚያም ከዚህም የቃረምካቸው የቅሌት መዝገቦች(ብድሮች) ሲወራረዱ…ጠላትህ ክው ይበል ክው የሚያደርግፍራንክ ይዘህ ወደሚስትና ልጆችህ ትነጉዳለህ፡፡ አማኝ ነህና ለዚህም ተመስገን ትላለህ…“ተመስገን፤ ይህንንምአታሳጣኝ!..ይህንንም ያጡ ብዙዎች አሉና አንተ በቸርነትህ ጎብኛቸው… አስባቸው!” እያልክ ነግቶ በመሸ ቁጥርለብቻህ ታጉተመትማለህ፡፡.. ጮሌዎቹ ባልንጀሮችህ “መንገዱን እወቅበት!” እያሉ ጠዋት ማታ ይጎተጉቱሃል፡፡ እነሱን እያቸው!…መንግስትንደመወዝ ጨምርልኝ ከማለት ይልቅ “ይህ ልማታዊ መንግስታችን ባዶ ካዝና ነው የተረከበው፤ የገቢያችን ማነስድህነታችን የፈጠረው ችግር ነው!…ችግሩ በልማታዊ መንግስታችን ጥረት ይፈታል!…”በማለት በየመለኪያቤቶች ጭምር ዲስኩራቸውን እየነፉ፤ ግን ቀብረር…ሞልቀቅ ያለ ኑሮአቸውን ያጣጥማሉ፡፡ ከየት አምጥተውይመስልሃል ወዳጄ?!…ዕድሜ ለልማታዊ መንግስታችን!.. የአንተን ኪስ በጥሩ ደመወዝ መሙላት ቢያቅተውም፤የሁነኛ ወጃጆቹን ቀዳዳ በርሜል ለመሙላት ግን ላቡን መዝራት አልተሳነውም፡፡ ለአንተና ለመሰሎችህ ግንበየቴሌቪዥኑ መስኮት፣ በየስብሰባ አዳራሹ ቋቅ እስኪልህ ድረስ “ዋንኛው ጠላታችን ኪራይ ሰብሳቢነት ነው!”ሲል ዲስኩሩን ይግታቹሃል፡፡ አንተም ምስኪኑ…አንዳንዴ የሰማህው ሁሉ እውነት እየመሰለህ ይህንኑበየሄድክበት እንደበቀቀን ስትደግም ትውላለህ፤ “ዋንኛው ጠላታችን ኪራይ ሰብሳቢነት ነው!…ኪራይ ሰብሳቢነትየሥርዓቱ አደጋ ነውና በተባበረ ክንድ እናጥፋው!…..ተረረረም..ተረረም…” ያ አብሮ አደግህ ዶ/ር እንቶኔ 6 ሺ ብር የማትሞላ ወርሃዊ ደመወዝ ይዞ ግራውንድ ፕላስ ዋን ቤት ሰርቷል፡፡ልጆቹን ለንደን ፣ አሜሪካ ልኮ ዶላር እየመነዘረ ያስተምራል፡፡ ያኛው (ስሙን ቄስ ይጥራውና!)… ከካድሬውበላይ ካድሬ ነኝ የሚለው….፤ መሽቶ በነጋ ቁጥር በፓርቲው እየማለና እየተገዘተ ራሱን ወደንዑስ ከበርቴ መደብከፍ ካደረገ ሰንብቷል፡፡ አንተ ግን በፈሪሃ እግዚአብሄር ተሞልተህ… ባዶ ኪስህን…ባዶ ሆድህን…ባዶ ቤትህንይዘህ ትናውዛለህ፡፡ ለልጆችህ ወርሃዊ ክፍያ አጥተህ ስንቱን ስትቧጥጥ እንደምትኖር የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻነው፡፡…ደግሞ ይህቺ ባዶነትህ ውስጥ የተሰካች ኩራትህ አናትህ ላይ ወጥታ ስትጨፍር ወግ ነውና ኮራ..ጀነንትላለህ፡፡ ሰው እናድርግህ! ያሉህን “ልማታዊዋን” እየሸሸህ…እየሸሸህ፤ እነሆ በማትሸሸው ድህነት ማጥ ውስጥቦክተህ….ሐሩር እንደመታው ቄጤማ ከነቤተሰብህ ጠውልገህ ትኖራለህ፡፡ ደሃ ነህ!…ገና ጠግበህ መብላትየምትመኝ ነህ!…እናም በስርቆት ከደረጁት ጋር ተሰልፈህ ዛሬም ባልበላ አንጀትህ “ዋንኛው ጠላታችን ኪራይሰብሳቢነት ነው!” እያልክ ትዘምራለህ፡፡ ሌላው መንገድ ያንተ አይደለምና ምን ምርጫ አለህ? ንጹህነትህንየሚጠየፉ ሌቦችን ከማጀብ ውጪስ ምን ተስፋ አለህ?…ግን ይህ ጽዱ ኢትዮጽያዊ ንጽህናህ!…ደግነትህ!…ጨዋነትህ! የት ድረስ ያዘልቅህ ይሆን?…እንጃ?!….አንድዬ ይታደግህ አቦ!… ፍ.አ (ነሐሴ 2005)

Read More →
Latest

ስብሰባው (በድጋሚ የቀረበ)

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ስብሰባው (በድጋሚ የቀረበ)

ሞልቶ ከተረፉን ስብሰባዎች መካከል በአንዱ ውስጥ ነበርኩ፡፡ ስብሰባው ስለመንግስት የዕድገትናትራንስፎርሜሸን ዕቅድ እና የክልሎች እንቅስቃሴ የሚወራበት ነበር፡፡ያው እንደደንቡ የተመረጡት ሹም ከአንድሰዓት በላይ ጊዜ ወስደው ጥናት ያሉትን አቀረቡ፡፡አወያዩ አቅራቢውን የጎንዮሽ በማየት እያደነቁ “ዌል! እጅግበሳል ትንታኔ የተንጸባረቀበት ጹሑፍ ነው፡፡እሳቸው ያሉትን መልሼ አልደግመውም፡፡ግን መታለፍ የሌለባቸውዋና ዋና ነጥቦችን ላንሳ” አሉንና ንግግራቸውን እየጎተቱ ልክ እንደበቀቀን ሰውየው ያሉትን ምንም ሳያስቀሩመልሰው ደገሙልን፡፡ደግመውልን ሲያበቁ መድረኩ ለአስተያየትና ጥያቄ ክፍት መሆኑን አበሰሩ፡፡ጥቂት እጆችአየር ላይ ታዩ፡፡ሰብሳቢው ብርጭቆ የሚያህል መነጽራቸውን ግራና ቀን ሲያንከራትቱ ቆዩና “አንተ በቀኝ በኩልያለኸው..አዎ!..ቀይ ከረባት ያሰርከው ” ብለው መነጋገሪውን አሻገሩ፡፡ተመራጩ ተናጋሪ ቀጠለ፡፡ “በቅድሚያ ክቡር አቶ እገሌ ላቀረቡልን ፕረዘንቴሽን ያለኝን ልባዊ አድናቆት ልገልጽ እወዳለሁ፡፡በእውነቱፕረዘንቴሽኑ በአሁኑ ወቅት በተለይ በክልሎች ያለውን ችግር አንድ በአንድ ነቅሶ ያሳየ በመሆኑ በዚህ ረገድየምጨምረው ብዙም ነገር አይኖረኝም፡፡ክቡር አቶ እገሌ እንዳሉት ለዚህች ሳታጣ ላጣች አገራችን መደህየትተጠያቂዎቹ ጸረ ልማት ኃይሎች መሆናቸውን የተናገሩት በትልቁ ሊሰመርበት ይገባል…. ” ሌላኛው ቀጠለ፡፡“እኔም እንደወንድሜ ክቡር አቶ እገሌ ላቀረቡልን ጥናታዊ ጹሑፍ ያለኝን ክብር ሳልገልጽአላልፍም፡፡ጹሑፋ ብዙ ያላወኩትን ነገር ያሳወቀኝ ነው፡፡ከዚህ በኃላ የማቀርበው አንድ ሁለት ጥያቄዎችይኖሩኛል፡፡ይኸውም የአገራችንን ዕድገትና ልማት የሚያደናቅፉ ሓይሎች እስከመቼ ነው የምንታገሳቸው?ይህስብሰባ አንድ ቁርጥ ያለ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ለመጠየቅ ነው፡፡አመሰግናለሁ፡፡” ሌላኛውም ማይክሮፎኑን አስጠግተው ለመናገር ጉሮሮአቸውን ጠራረጉ፡፡“እ..እ..እ..እ….ክቡር ሰብሳቢለሰጡኝ ዕድል አመሰግናለሁ፡፡በእውነቱ በእንዲህ ዓይነት ትልቅ አገራዊ ፋይዳ ባለው ስብሰባ ላይ በመገኘቴየተሰማኝን ደስታ በዚህ አጋጣሚ ልገልጽ እወዳለሁ፡፡ጥናት ያቀረቡትም እጅግ ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ጥናቱ መሬትላይ ያሉ ችግሮቻችን በሚገባ የዳሰሰ ነው፡፡አገራችን ለዘመናት የተጎዳችው እንዲህ ዓይነት ችግሮቻችን በሚገባየሚዳስሱ ጥናቶች ባለመኖራቸው ነው፡፡እናም ስብሰባውን አዘጋጆች የምጠይቀው ይህ ጠቃሚ ጥናትለሚመለከታቸው ስቴክሆልደሮች ሁሉ ተባዝቶ እንዲሰጥ መደረግ እንዳለበት ለማሳሰብ ነው፡፡አመሰግናለሁ፡፡” ሌሎችም ሶስት ተናጋሪዎች በተመሳሳይ መንገድ አድናቆታቸውን ገለጹ፡፡የስብሰባው ተካፋዮችም ንግግሮችን ሁሉሳይታክቱ በጭብጨባ ከማድመቅ አልቦዘኑም፡፡ እነሆ የሻይ ዕረፍት ሆነ፡፡ ምሳ ሰዓትም ደርሶ መብልና መጠጡተወራረደ፡፡ በስብሰባው ማሳረጊያ ላይ የአቋም መግለጫ ወጣ፡፡ተጨበጨበ፡፡የውሎ አበል ለተሰብሳቢውበነፍስወከፍ ታድሎ የዕለቱ  መርሃግብር ተጠናቀቀ፡፡ ምሽትም ላይ ኢቴቪ በዕድገትና በትራንስፎርሜሽኑ ዕቅድና ትግበራ ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን አውደጥናት በሸራተንሆቴል ሲካሄድ መዋሉን አበሰረ፡፡ “በስብሰባው ላይ የተገኙት ክቡር አቶ እገሌ ባቀረቡት ጥናታዊ ጹሑፍየአገሪትዋን ልማትና ዕድገት በአስተማማኝ መልኩ ለማስቀጠል ጸረ ሰላም ኃይሎችን መታገል እንደሚገባበአጽንኦት ተናግረዋል፡፡ተሰብሳቢዎችም ዕቅዱን ለማሳካት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ቃል መግባታቸውየሪፖርተራችን ዘገባ ያሳያል” አለ፡፡ እነሆ ወራት ተቆጠሩ፡፡ክቡር ሚኒስትሩም የመ/ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማሲያቀርቡ ያን ዓውደጥናት አልዘነጉትም፡፡ ከተለያዩ ክልሎችና ሴክተር መ/ቤቶች ለተውጣጡ ከፍተኛ አመራሮችየአንድ ቀን አውደጥናት መሰጠቱን፤ በዕለቱም በቀረበው ጥናት መሰረት በልማት ረገድ ክልሎች ያለባቸውችግሮች መቀረፋቸውን ለፓርላማው ተናገሩ፡፡ዓውደጥናቱን ጨምሮ ለዚህ ዓመት ከተያዘው በጀት 30 ሚሊየንብር ጥቅም ላይ መዋሉንና የበጀት አፈጻጸማቸው ከዓመት ዓመት መሻሻል እያሳየ መምጣቱን አከሉ፡፡የፓርላማአባላቱም ስለሪፖርታቸው አጨበጨቡ፣አደነቁ፡፡ኢቴቪም የሚኒስቴሩ ሥራ አበረታች መሆኑን ፓርላማውመናገሩን ምሽት ላይ ነገረን፤እኛም የተደነቀውን፣የተጨበጨበለትን….አይተን፣ሰምተን እንደቅዱስ ቃሉ ይሁንብለን ዝም አልን፡፡

Read More →
Latest

Israeli president condemns rejection of Ethiopian-born MP as blood donor

By   /  December 16, 2013  /  AFRICA, Ethiopia  /  Comments Off on Israeli president condemns rejection of Ethiopian-born MP as blood donor

Parliamentary session is called after ‘special’ blood of Ethiopian-born MP is rejected by emergency services Harriet Sherwood theguardian.com,  Shimon Peres says all citizens are equal and should be able to donate blood. Photograph: Hector Guerrero/AFP/Getty Images Israel‘s president, Shimon Peres, has criticised the refusal of the country’s emergency medical services to accept a blood donation from an […]

Read More →
Latest

ብዙም ያልተነገረ ታሪክ ===== ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ብዙም ያልተነገረ ታሪክ ===== ወሰን ሰገድ ገብረኪዳን

ይህ የወርሃ ታህሣሥ ብዙም ያልተነገረ ትውስታ ነው፡፡ በዘመናዊው ኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ሁሌም የሚታወስ ወር ነው፡- ታህሣሥ፡፡ “የታህሣስ ግርግር” ይሰኛል፡፡ መንግስቱ ንዋይና ግርማሜ ንዋይ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱበትና በአፄው ሥርዓት ላይ መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ያደረጉት በታህሣሥ ወር የመጀመሪያ ሳምንት፡- ከታህሣስ 5- 7 ቀን 1953 ነው መፈንቅለ መንግስት ሙከራው የተቃጣው፡፡ ከዛሬ 53 ዓመት በፊት መሆኑ ነው፡- የእነመንግስቱ ንዋይ […]

Read More →
Latest

Mandela’s widow wept river of tears as the peace icon laid to rest in Qunu. (By Getahune Bekele- Qunu village, South Africa.)

By   /  December 16, 2013  /  AFRICA, Ethiopia  /  Comments Off on Mandela’s widow wept river of tears as the peace icon laid to rest in Qunu. (By Getahune Bekele- Qunu village, South Africa.)

The Horn Times Newsletter-Sunday 15 December 2013 “Do not stand at my grave and weep; I am not there. I do not sleep. I am a thousand winds that blow. I am the diamond glints on snow. I am the sunlight on ripened grain, I am the gentle autumn rain. Do not stand at my […]

Read More →
Latest

ይድረስ ለኢትዮጵያውያን የአገር ተቆርቋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on ይድረስ ለኢትዮጵያውያን የአገር ተቆርቋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች

ታሕሳስ 7 ቀን 2006 á‹“.ም. ከግንቦት ሰባት ዲሞክራቲክ የተላከ መግለጫ ኤርትራ የሚፈፀም ወንጀል1 ይድረስ ለኢትዮጵያውያን የአገር ተቆርቋሪዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዋናውን ገጽ እዚህ ያንብቡት የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት ሲጣስ የትም ይሁን የት፣ በማንም ይሁን በማን ሊወገዝ፣ ፈጻሚው ሊጠየቅ ይገባዋል። ኢትዮጵያውያን በተለይም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የህግ ባለሙያዎችም ሁኔታውን አጣርተው ለወገኖቻችን ሰቆቃ ጥብቅና ሊቆሙ ይገባል። የኢትዮጵያውያን መከራ አገርቤት […]

Read More →
Latest

የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ለውጥ ከላዕላይ መዋቅር ይመነጫል እንጂ ለአንድ ሀ/ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ አይደለም! በዲ/ን ሐብታሙ ዘዲማው ጊዮርጊስ

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ለውጥ ከላዕላይ መዋቅር ይመነጫል እንጂ ለአንድ ሀ/ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ቢሮ አይደለም! በዲ/ን ሐብታሙ ዘዲማው ጊዮርጊስ

  ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የወቅታዊ ሁኔታውን እየተከታተላችሁ ለምትልኩልን የማለዳ ታይምስ የብእር ታዳሚዎች በሙሉ ምስጋናችን በአንባብያኖቻችን ስም ከፍ ያለ ነው ! የማኅበረ ቅዱሳን ሩጫ ሀገረ ስብከት የመቆጣጠር ስልት እንጂ ዘረፈ ብዙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር ለመፍታት አያገለግልም። ማኅበረ ካህናቱ ከማኅበረ ቅዱሳን አፈናና ስለላ ለመዳን መታገል ያለባቸው ዛሬ ነው! ማኅበረ ቅዱሳን ራሱ ተቋማዊ ለውጥ የሚያስፈልገው ድርጅት ነው! […]

Read More →
Latest

የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው ገብሬሉ ተስፋዬ ከ ኖርዌ

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on የኢትዮጲያ ሰላም በአንድነታችን ላይ ነው ገብሬሉ ተስፋዬ ከ ኖርዌ

የሚያኮራ የሚያስደስት ኢትዮጲያዊ አንድነት ሰሞኑን በተደረጉት የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎች ላይ አይተናል :: በሳውዲ አረቢያ እየተሰቃዩ ላሉት እህትና ወንድምቻችን ሀይማኖትና ዘርን ሳንለይ ያሳየነው የአንድነትና የቁጣ መንፈስ በጣም የሚያስደስት ነው :: ይሄ ያሳየነው አንድነት እና ቆራጥነት መቀጠል ሊኖርበት ይገባል :: ካልሆነ ግን የችግራችንን ሥር መንቀል አስችጋሪ ነው :: ሳውዲ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጲያዊያን ሲገደሉ፣ሲደበደቡ እና ሲደፈሩ በኢትዮጲያዊነታችው መሆኑን […]

Read More →
Latest

የማለዳ ወግ … ስደተኛው ዘፋኝ በሳውዲ በርሃ …(ነቢዩ ሲራክ)

By   /  December 16, 2013  /  Ethiopia  /  Comments Off on የማለዳ ወግ … ስደተኛው ዘፋኝ በሳውዲ በርሃ …(ነቢዩ ሲራክ)

   የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ ፣ እጓዛለሁ … እንደጨው ተበትነናልና ስፍር ቁጥር የሌላቸው ወገኖቸን በየሔድኩበት ከተማ ፣ እግር በጣለኝ የሳውዲ የቀለጡ በርሃዎች ወንድም እህቶቸን አገኛለሁ ። ላፍታም ቢሆን ጊዜ ሰጥቸ እየኑሩት ስላለው ኑሮ ፣ እየገፉት ስላለው ክፉም ደግ ተሞክሮ እጠይቃቸዋለሁ አንድም ሳይደብቁ የሆድ የሆዳቸውን ያጫውቱኛል …    እለተ ቅዳሜ በማለዳው ያቀናሁት በያንቦና በጅዳ […]

Read More →
Latest

Ethiopia’s War on Homosexuals

By   /  December 16, 2013  /  AFRICA  /  Comments Off on Ethiopia’s War on Homosexuals

By Katie J.M. Baker /  In many countries, it’s getting better for the LGBT community. In Ethiopia, it’s getting worse.  Tadej Znidarcic/Redux In a bleak little apartment on the outskirts of Addis Ababa, nearly a dozen men in their 20s take turns trying on a pair of black skinny jeans and watching Project Runwayepisodes downloaded off YouTube. There’s no […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar