www.maledatimes.com
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  -  Page 148
Latest

ደሴ በሰላማዊ ሰልፍ ተናወጠች

By   /  April 6, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on ደሴ በሰላማዊ ሰልፍ ተናወጠች

አትንኩኝ ፣ባዩ እና ካልነካችሁኝ አልደርስባችሁም የሚለው እልኸኛው የደሴ ከተማ ህዝብ ከቤቱ ውልቅ ብሎ ወደ አደባባይ በመውጣት ብሶቱን አሰምቶአል ።በደሴው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከአስር ሺ በላይ የሚሆን ህዝብ ፍርሃትን ሰብሮ የደሴ ጎዳናዎች ላይ ወጥቷል። ህዝቡ አሁንም ወደ ሰላማዊ ሰርፉ በመጉረፍ እየተቀላቀለ ነው። መብቱን እና ነጻነትን በማወቅ ጥያቀዎቹን ለማሰማት የአንድነት ፓርቲ ጥሪን ተከትሎ አደባባይ የወጣው ህዝብ በመፈክር […]

Read More →
Latest

የእንግሊዝ ኩባንያዎች ቅሬታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበ

By   /  April 5, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on የእንግሊዝ ኩባንያዎች ቅሬታ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀረበ

ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የተሰማሩ የእንግሊዝ ኩባንያዎች በርካታ ችግሮች እያጋጠማቸው ነው በማለት የእንግሊዝ ኤምባሲ ቅሬታውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አቀረበ፡፡ እንግሊዝ ኤምባሲ ሰሞኑን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በኩባንያዎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር በመዘርዘር በደብዳቤ አሳውቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሥልጣናትና ከእንግሊዝ ኩባንያዎች ተወካዮች ጋር ተነጋግረዋል፡፡ ‹‹ጠቅላይ […]

Read More →
Latest

በ250 ሚሊዮን ዶላር ለሚገነባው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አምስት አማካሪ ኩባንያዎች ቀረቡ

By   /  April 5, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on በ250 ሚሊዮን ዶላር ለሚገነባው የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ አምስት አማካሪ ኩባንያዎች ቀረቡ

ዋና ዜና  ተጻፈ በ  ቃለየሱስ በቀለ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት በ250 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለማስገንባት ላቀደው የቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ተርሚናል የማስፋፊያ ፕሮጀክት ለማማከር፣ አምስት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የጨረታ ሰነድ ገዝተዋል፡፡  የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ተርሚናል ማስፋፊያ ግንባታ ሥራ የሚቆጣጠር፣ ከአዲስ አበባ ውጪ ለመገንባት ያሰበውን ግዙፍ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ፕሮጀክት የሚያጠና […]

Read More →
Latest

መናገርና መፃፍ ወንጀል የሆነባት ሃገራችን

By   /  April 4, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on መናገርና መፃፍ ወንጀል የሆነባት ሃገራችን

በናትናኤል ካብትይመር ከኦስሎ ኖርዌይ “ በኢትዮጲያ የጋዜጠኝነት ሞያ በአግባቡ የተተገብረው እንዲሁም  በነፃነት መፃፍና መተንተን የሚቻለው ስለ አውሮፓ እግር ኳስበተለይም ስለ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ነዳጅ ጨመረ ፖለቲካ ነው ፣ ነዳጅ ቀነሰም ፖለቲካ ነው ፣ ኑሮተወደደ ፖለቲካ ነው ፣ ታክሲ ጠፋ ፖለቲካ ነው ፣ ምርጫ ደረሰ ፖለቲካ ነው ፣ ሁሉ ነገር ፖለቲካ […]

Read More →
Latest

የኛና የነሱ ኢትዮጲያ

By   /  April 4, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on የኛና የነሱ ኢትዮጲያ

እኛ የምናውቃት ኢትዮጲያ ከግማሽ በላይ ህዝቧ በመብራትና በውሃ እጦት የሚሰቃይባት ፣ በስልክና በኔትወርክ ችግር የሚማረርባት ፣  በመልካም አስተዳደር እጦት አሳሩን የሚበላባት፣  አብዛኛው ህዝቧ የዛሬን እንጂ የነገን ማቀድ የማይችልባት ፣ የተለያዩ ተንታኞችና አለማቀፍ ድርጅቶች “ችግር አለ” ብለው የሚያስጠነቅቋት ፣ ለዲሞክራሲ ፈር ቀዳጅ መሆን የሚገባው የፖለቲካስርዓት የሚያስፈራና ደም ደም የሚሸትባት ፣ ብዙ ዜናና ትንታኔ ስለ አንዲት የመንግስት ፕሮጀክት ለአመታት የሚነገርባት ፣ ከአንዲት ፕሮጀክት ብዙ ሚሊዮን ብር በሙስና ተዘርፎ ጥቂቶችየሚከብሩባት ፣ መንግስት ተብየው ሃገርና ህዝብ ከማስተዳደር ይልቅ ስልጣኑን ለማደላደል ተግቶ የሚሰራባት ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿን በየአመቱ በስደት የምታጣ ፣ ለቁጥር በሚታክቱአሰቃቂ የመኪና አደጋዎች በየቀኑ ዜጎቿ የሚረግፉባት ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿ በህክምና እጥረት በሞት የምትነጠቅ ፣ ችግሮቿ ለቁጥር የሚታክቱ ነገር ግን ኩሩ ታሪክ ያላት ጥቂት ሆዳሞችበፈጠሩት ችግር አንገቷን የደፋች ሃገር ናት። እነሱ ግን ልክ እንደማናውቃት ሌላ ሃገር ኢኮኖሚዋ አለምን ባስገረመ መልኩ ለተከታታይ ብዙ አመታት የተመነደገባት ፣  የአለማችን መዓት ሃገራት የሚቀኑባትና ልምድ የሚቀስሙባትናት ይሉናል። ለመሆኑ ይህች እነሱ የሚሏት ሃገር የት ነው ያለችው? ለምን ይሆን ስለገዛ ሃገራችን ከአመት አመት ልክ እንደማናውቃት በሞኝ ውሸት የሚሰብኩን? ሃገራችን ችግር ላይ መሆንዋን ችግርዋም ከግዜ ወደ ግዜ እየተወሳሰበ ለመፍታት ወደሚያስቸግር ሂደት ውስጥ እየገባ መሄዱን የተለያዩ ምሁራን ፣ ፖለቲከኞች ፣ ተንታኞች እንዲሁምአለማቀፍ ድርጅቶች ሲወተውቱ በአንፃሩ ደግሞ መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠው አካል የዝሆን ጆሮ ይስጠኝ እያለ ነው። ሁላችንም የምናውቀው አንድ እውነት ከጥቂት ሆዳሞች በስተቀርኢትዮጲያዊ ሆኖ ሃገር እንድታድግለት የህዝቡም ኑሮ እንዲሻሻልለት የማይፈልግ የለም። ነገር ግን መንግስት ተብየው የሃገራችንን ችግር ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ የባሰ እያወሳሰበውና ጭርሱንምእየሸፋፈነ ወደ መፍትሄ አልባነት እየገፋው ይገኛል። የችግሩንም መኖር የሚጠቁሙ ዜጎችና አለማቀፍ አካላት እንደመንግስት ተቀራርቦ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ እንደሃገር ጠላት እየፈረጀ ይገኛል። ሃገራችን ለዘመናት ለተጫናት ችግር የህወሃት መንግስት በጉልበት መመካት መፍትሄ ሳይሆን ሌላ ችግር ፈጣሪ መሆን ነው። ይህንንም መንግስት ተብየው በሚገባ ያውቀዋል። ነገር ግንሃገር ወዳድነት ወደጎን ተብሎ በራስ ወዳድነትና አድር ባይነት ውድ ሃገራችን ኢትዮጲያ ወደ አጓጉል ሁኔታ ውስጥ እየተገፋች ነው። ጥቂት ራስ ወዳዶችና በግለኝነት የተዋጡ ተራ ብልጣ ብልጦችለሃገር እድገት ከመጣር ይልቅ አንዲት ነገር እየተቀባበሉና ቅርፅ እየቀያየሩ ትንታኔ በመስራት የማናቃት ኢትዮጲያ በመፍጠር ህዝባችንን የህልም ዳቦ እየበላህ ኑር እያሉት ነው። የሃገራችን ህዝብ ከመቼውም ግዜ በበለጠ የለት ተለት ኑሮው እጅግ አስቸጋሪ እስኪሆን ድረስ በዘርፈ ብዙ ችግሮች ተይዟል። በመንግስት ቴሌቪዥን የሚያይዋት ኢትዮጲያ የት እንዳለችአያውቁም። ደስተኝነት ከአብዛኛው ህዝባችን ርቋል። የሃገራችን ህዝብ  በመንግስት ሚዲያ የሚነገረው የህልም የኢኮኖሚ ትሩፋት የት እንዳለ አያውቅም። በዋና ከተማ እየኖረ የሚጠጣው ያጣንህዝብ ፣ በዋና ከተማ እየኖረ ለወራት በመብራት እጦት ሳቢያ በሻማ ለሚኖር ህዝብ ፣ በትራንስፖርት እጦት እየተሰቃየ ለሚኖር ህዝብ ፣ በመኪና አደጋ ፍራቻ በሰቀቀን ውሎ ለሚገባ ህዝብ በጥቂትሆድ አደር ብልጣ ብልጦች ስለ ሃገር ኢኮኖሚ መመንደግ ፣ ስለ ከተማ ውበትና ስለትራንስፖርት መትረፍረፍ ይነገራዋል። ሃገራችን ችግር ላይ ነች። ይህን ማለት ችግር መፍጠር አይደለም። መንግስት ነኝ ብሎ የተቀመጠው አካል የተሞላው በራስ ወዳዶች ፣ ብልጣ ብልጦችና የህዝብ ብሶት በማይሰማቸውሆዳም ግለሰቦች ነው። ይህንን የሃገራችንን ችግር ከነችግር ፈጣሪዎቹ ማስወገድ የማንኛውም ሃገር ወዳድ ዜጋ ሃላፊነትና ግዴታ ነው። ሃገራችን ጭርሱን የማይፈታና ወደውሃላ የማይመለስ አደጋውስጥ ከገባች በውሃላ ጣት መጠቋቆሙ ከክፉ ፀፀት ውጪ የሚፈይደው ነገር አይኖርም። እኛም ሆነ እነሱ የምናወራው ስለ አንድ ሃገር ነው። ስለ ኢትዮጲያ። ኢትዮጲያን ከችግር የማውጣትግዴታ ያለብን ደግሞ እኛው ኢትዮጲያውያን ነን። አዎ ኢትዮጲያችን ከመቼውም ግዜ በላይ ችግር ላይ ነች።   natnaelkab@gmail.com  

Read More →
Latest

‪‎አውቀን_እንታረም‬

By   /  April 4, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on ‪‎አውቀን_እንታረም‬

“ትንቢት ከነገር ይቀድማል” ይላሉ፡- አበው፡፡ እውነት ነው፡፡ አባባሉ እውነትነት ያለው መሆኑ በተለያየ ዘመን፣ ሁኔታ እና አጋጣሚ ታይቷልና፡፡ አንደንድ ሰዎች በዘመናቸው ከደረሱበትና ከደረሰባቸው ሁኔታ በመነሳት በግል ሕይወታቸው፣ በማህበረሰባቸው፣ ብሎም በሀገራቸው …ወዘተ ላይ ሊመጣ ይችላል የሚሉትን መልካምም ሆነ ክፉ ነገር አስቀድመው “ይተነብያሉ”፡፡ እንዲህ ያሉ ሰዎች በነገሮች ላይ ካለቸው ዕይታ ተነስተው በቃልም ሆነ በፅሁፍ ሥጋታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ያሰጋቸው ነገር […]

Read More →
Latest

የአዲስ አበባ መስተዳድር እጅ ሰጠ። አንድነት መልስ ለመስጠት እየተወያየ ነው።

By   /  April 4, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on የአዲስ አበባ መስተዳድር እጅ ሰጠ። አንድነት መልስ ለመስጠት እየተወያየ ነው።

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ መጋቢት 28/2006 ለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ የእውቅና ደብዳቤ ለመስጠት ህጋዊ መስመሩን ለመከተል ተስኖት የቆየው የአዲስ አበባ መስተዳድር ዛሬ ማለዳ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ መጋቢት 28 በሌሎች መርሐ ግብሮች የተያዘ በመሆኑ ተለዋጭ ቀንና ቦታ እንድታቀርቡ ይሁን ብሏል፡ ፡የፓርቲው አመራሮች ለተጻፈላቸው ደብዳቤ ምላሽ ለመስጠት በአሁኑ ሰዓት በውይይት ላይ ይገኛሉ፡፡

Read More →
Latest

” የእሪታ ቀን ” ሰልፉ ለሚያዚያ 5 2006 ተላልፏል። አንድነት ፓርቲ

By   /  April 4, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on ” የእሪታ ቀን ” ሰልፉ ለሚያዚያ 5 2006 ተላልፏል። አንድነት ፓርቲ

ህግ እያስከበርን የማስከበር ሃላፊነታችንን እንወጣለን፡!!! ለመጋቢት 28/2006 ተይዞ የነበረው ‹‹የእሪታ ቀን›በሚል መሪ ቃል ሊደረግ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ በዕለቱ የተለያዩ ፕሮግራሞች በከተማው የሚደረግ በመሆናቸው ቀኑን እንድንቀይር የአዲስ አበባ መስተዳድር በመጻፉ አንድነት ፓርቲ ለመስተዳድሩ ደብዳቤያቸውን መቀበሉን በማስታወቅ ሰላማዊ ሰልፉ ሚያዚያ 5/2006 እንደሚከናወን ይፋ አድርጓል፡፡

Read More →
Latest

የአሉላ፣ የዮሐንስ፣ የጎበና እና የምኒሊክ ትውልድ! ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2006 á‹“.ም. (Thursday, April 3, 2014) ————- ግርማ ሞገስ

By   /  April 3, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on የአሉላ፣ የዮሐንስ፣ የጎበና እና የምኒሊክ ትውልድ! ሐሙስ መጋቢት 25 ቀን 2006 á‹“.ም. (Thursday, April 3, 2014) ————- ግርማ ሞገስ

የዚህ ጽሑፍ ግብ በመንግስት ስልጣን ሽሚያ የተነሳ በአንድ ወገን በዮሐንስ እና በአሉላ ትውልድ በሌላ ወገን በምኒልክ እና በጎበና ትውልድ መካከል የነበረውን የፖለቲካ ባላንጣነት፣ ለስልጣን ሲሉ የተደራረጉትን እና የፈጸሙትን ስህተት መተረክ አይደለም። በመካከላቸው የነበረው ጸብ ዙፋኑ ለእኔ ይገባ ነበር የሚል ጸብ ነበር፡፡ የስልጣን ጸብ ነበር። በእርስ በርስ ጦርነት የሚፈጸመው ስርዓት አልባው የመንግስት ሽግግር ባህላችን የፈጠረው ጸብ […]

Read More →
Latest

ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው? by መስፍን ወልደ-ማርያም

By   /  April 2, 2014  /  Ethiopia  /  Comments Off on ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ! መጠላለፍ ወደየትኛው ገደል እየመራን ነው? by መስፍን ወልደ-ማርያም

መስፍን ወልደ ማርያም መጋቢት 2008 የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው ‹እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!› በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ […]

Read More →
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

This site is protected by wp-copyrightpro.com

Skip to toolbar