www.maledatimes.com ደሴ በሰላማዊ ሰልፍ ተናወጠች - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ደሴ በሰላማዊ ሰልፍ ተናወጠች

By   /   April 6, 2014  /   Comments Off on ደሴ በሰላማዊ ሰልፍ ተናወጠች

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 30 Second

አትንኩኝ ፣ባዩ እና ካልነካችሁኝ አልደርስባችሁም የሚለው እልኸኛው የደሴ ከተማ ህዝብ ከቤቱ ውልቅ ብሎ ወደ አደባባይ በመውጣት ብሶቱን አሰምቶአል ።በደሴው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከአስር ሺ በላይ የሚሆን ህዝብ ፍርሃትን ሰብሮ የደሴ ጎዳናዎች ላይ ወጥቷል። ህዝቡ አሁንም ወደ ሰላማዊ ሰርፉ በመጉረፍ እየተቀላቀለ ነው። መብቱን እና ነጻነትን በማወቅ ጥያቀዎቹን ለማሰማት የአንድነት ፓርቲ ጥሪን ተከትሎ አደባባይ የወጣው ህዝብ በመፈክር እና በዝማሬ ብሶቱን እያሰማ ነው።

ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ
– አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚሉ መፈክሮች ተሰምተዋል
“እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን !!! ” የደሴ ነዋሪዎች
የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በደሴ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉ ታውቋል።
ከቅስቀሳ ጀምሮ በደህንነቶች እና በፖሊስ ሃይሎች ወከባ እና መንግስታዊ ውንብድና የተደረገበት የደሴው ሰልፍ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም ለመብቱ እና ለነጻነት ያለውን ቀናኢነት በማሳየት ትልቅ ትብብር አድርግዋል። በደሴ ከተማ በዛሬው እለት የተደረገው ሰልፍ ከጠዋት ጀምሮ ህዝቡ ፍርሃቱን በመስበር ወደ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ያሰማ ሲሆን ፖሊሶች መንገድ በመዝጋት ሽብር ለመፍጠር ቢሞክሩም ህዝቡ እያሳበረ በሰልፉ ላይ በመገኘት ተቃውሞውን አሰምቷል።

ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ መፈክሮች ደምቆ ነበር።ህዝቡ አንግቦት ክንበሩት መፈክሮች ውስጥ ፦
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ – አንድነት ኃይል ነው
– የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ – መሬት ለህዝብ ይመለስ
– ጭቆና በቃን – ድል የህዝብ ነው – በግፍ የታሰሩ ይፈቱ ……… የሚሉ ይገኙበታል።
የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊሶች እና ደህንነቶች ቀበና ሼል አከባቢ የሚገኘውን የአንድነት ዋና ጽ/ቤት በመክበብ ወከባ ሲፈጽሙ ተስተውሏል።

በደሴው ሰላማው ሰላፍ ላይ የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንቱ አቶ ተክሌ በቀለ እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ሃላፊው ዘለቅ ረዲ የደሴ የአንድነት ሰብሳቢ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

አንድነት ፓርቲ በደሴ የተሳካ ሰላማዊ ሰልፍ አደረገ።
#Ethiopia #UDJ #Dessie #EPRDF #MillionsofVoicesforlandownership

ምንሊክ ሳልሳዊ
"እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን !!! ” የደሴ ነዋሪዎች
የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት በሚል መሪ ቃል አንድነት ፓርቲ የጀመረውን ዘመቻ በማስመልከት የመጀመሪያውን ሰላማዊ ሰልፍ በደሴ ከተማ በተሳካ ሁኔታ ማድረጉ ታውቋል።
ከቅስቀሳ ጀምሮ በደህንነቶች እና በፖሊስ ሃይሎች ወከባ እና መንግስታዊ ውንብድና የተደረገበት የደሴው ሰልፍ ህዝቡ ከፓርቲው ጎን በመቆም ለመብቱ እና ለነጻነት ያለውን ቀናኢነት በማሳየት ትልቅ ትብብር አድርግዋል። በደሴ ከተማ በዛሬው እለት የተደረገው ሰልፍ ከጠዋት ጀምሮ ህዝቡ ፍርሃቱን በመስበር ወደ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ያሰማ ሲሆን ፖሊሶች መንገድ በመዝጋት ሽብር ለመፍጠር ቢሞክሩም ህዝቡ እያሳበረ በሰልፉ ላይ በመገኘት ተቃውሞውን አሰምቷል።

ከ60 ሺህ በላይ የከተማው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይህ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ መፈክሮች ደምቆ ነበር።ህዝቡ አንግቦት ክንበሩት መፈክሮች ውስጥ ፦
-መሬት ከካድሬው ወደ ህዝቡ ይመለስ - አንድነት ኃይል ነው
- የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ - መሬት ለህዝብ ይመለስ
- ጭቆና በቃን - ድል የህዝብ ነው - በግፍ የታሰሩ ይፈቱ ......... የሚሉ ይገኙበታል።
የደሴው ሰላማዊ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት የአዲስ አበባ ፖሊሶች እና ደህንነቶች ቀበና ሼል አከባቢ የሚገኘውን የአንድነት ዋና ጽ/ቤት በመክበብ ወከባ ሲፈጽሙ ተስተውሏል።

በደሴው ሰላማው ሰላፍ ላይ የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ተቀዳሚ ም/ፕሬዝዳንቱ አቶ ተክሌ በቀለ እንዲሁም የውጪ ጉዳይ ሃላፊው ዘለቅ ረዲ የደሴ የአንድነት ሰብሳቢ ንግግር ማድረጋቸው ታውቋል። የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ምንሊክ ሳልሳዊ
አዲስ አበባ የሚገኘው የአንድነት ቢሮ በከፍተኛ ሁኔታ በፖሊስ እና በደህንነት ሃይሎች ተከቧል። የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ነው። ከ60 ሺ በላይ የሚሆን ህዝብ ወጥቶ ተቃውሞውን እየገለፀ ነው፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on April 6, 2014
  • By:
  • Last Modified: April 6, 2014 @ 7:06 am
  • Filed Under: Ethiopia
  • Tagged With:

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar