www.maledatimes.com 5910 ጀነሬተሮች ርክክብ መደረጉን እና የመስኖ አገልግሎት ለማስፋፋት ጠቃሚ መስመር መዘርጋቱን ተገለጸ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

 5910 ጀነሬተሮች ርክክብ መደረጉን እና የመስኖ አገልግሎት ለማስፋፋት ጠቃሚ መስመር መዘርጋቱን ተገለጸ

By   /   July 18, 2020  /   Comments Off on  5910 ጀነሬተሮች ርክክብ መደረጉን እና የመስኖ አገልግሎት ለማስፋፋት ጠቃሚ መስመር መዘርጋቱን ተገለጸ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 59 Second

ውሃ ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ የማይተካ ሚና ያለው ውድ ሃብት በመሆኑ ሁሉም በአግባቡ መጠበቅና መጠቀም እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ ገለጹ። 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው የውሃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖች ለሁሉም ክልሎች ማከፋፈል ጀምሯል።

የውሃ፤ መስኖና ኢነርጂ እንዲሁም የግብርና ሚኒስቴሮች በጋራ በመሆን የኮሮና ወረርሸኝ በግብርናው ዘርፍ ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ መቀነስና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የውሃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖችን ለሁሉም ክልሎች አከፋፍለዋል።

ከፓምፖቹ በተጨማሪም ለሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት ድጋፍ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች ለክልሎቹ ተሰጥተዋል።

በርክክቡ ሥነ-ሥርዓት ላይ የክልል የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በዚሁ ጊዜ ውድ የተፈጥሮ ሃብት የሆነውን ውሃ በአግባቡ ማመንጨት፣ መጠበቅና መጠቀም ይገባል ብለዋል።

ውሃ ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ የዓለም የዲፕሎማሲና የግጭት መነሻ እንደሚሆን ገልጸው፣ ይህን ውድ የተፈጥሮ ሃብት መጠበቅ ግዴታ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተውታል።

የኢትዮጵያ ዋነኛ የውሃ ምንጭ ዝናብ በመሆኑ ለደን ልማት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑንም  አስታውቀዋል።

እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ገለጻ፣ ያለውን የውሃ ሃብት በማጠራቀም ለተለያዩ አገልግሎቶች ማዋል ተገቢ ነው።

ይህንንም ለመጠጥ፣ ለመስኖ፣ ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ፣ ለንፅህናና ለሌሎችም አገልግሎቶች ማዋል ካልተቻለ፤ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አስረድተዋል።

እያንዳንዱ አርሶአደር ያለውን የውሃ ምንጭ ጥቅም ላይ ሊያውለው ይገባል ሲሉም ዶክተር ዓቢይ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ከየትኛውም ዓለም የተሻለ ውሃ የምታገኝ ቢሆንም፣ ውሃውን በአግባቡ ጥቅም ላይ አለማዋሏንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ ውሃን በመጠቀም 45ሺህ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ቢኖራትም፣ እስካሁን እያመነጨች ያለችው ግን ከአቅሟ 10 በመቶ አለመዝለሉንም ዶክተር ዓቢይ ያነሱት።

ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውሃ የማይተካ ሚና ያለው በመሆኑ ሁሉም የተፈጥሮ ሃብቱን መጠበቅ ይገባዋል ብለዋል።

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ በበኩላቸው በ2013 በጀት ዓመት ለመስኖ ልማት ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።

ለዚህም 16 ቢሊዮን ብር በጀት በመመደብ ነባርና አዳዲስ ፕሮጄክቶች ተቀርጸው የግብርናው ዘርፍ መሠረታዊ ለውጥ እንዲያመጣ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በግብርናው ዘርፍ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመቀነስና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት በመመደብ 10 ሺህ የውሃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖች መገዛታቸውን አብራርተዋል።

በመጀመሪያው ዙር ከ692 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገዙት 5 ሺህ 910 የውሃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖችም ለሁሉም ክልሎች ዛሬ መከፋፈል ጀምረዋል።

ፓምፖቹ በርካታ አርሶና አርብቶ አደሩን እንዲሁም ወጣቶችን የመስኖ ልማት ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ሚና እንዳላቸውም ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ፓምፖቹ ለክልሎቹ የተሰራጩት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ባወጣው የበጀት ቀመር መሠረት በማድረግ ነው።

ቀሪውን የውሃ መሳቢያ ሞተር ፓምፖች ግዥ በአጭር ጊዜ በመፈጸም ርክክቡ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ ፓምፖቹ በተለይ ለኩታ ገጠም እርሻ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

በሁሉም ክልሎች ያለውን መሬትና ውሃ በተቀናጀ መልኩ በመጠቀም የዘንድሮውን የእርሻ ጊዜ በተሻለ መልኩ መጠቀምና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሁለተኛው የከተሞች የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክት አቅም ግንባታ የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች ለክልል ከተሞች ተከፋፍለዋል።

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar