www.maledatimes.com በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በተከሰተው ሁከትና ግርግር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በተከሰተው ሁከትና ግርግር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ

By   /   July 18, 2020  /   Comments Off on በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በተከሰተው ሁከትና ግርግር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ

    Print       Email
0 0
Read Time:46 Second

በባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ በተከሰተው ሁከትና ግርግር የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አጋርፋ ወረዳ ሰሞኑን በተከሰተው ሁከትና ግርግር አጥፊዎች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በባሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ተስፋዬ ከበደ እንደገለጹት÷ በወረዳው ለጥፋት የተንቀሳቀሰው ቡድን ሲገለገልባቸው የነበሩ የጦር መሣሪያዎች ተይዘዋል።

ከነዚህም ዘጠኝ ሽጉጦች፣ አራት ክላሽንኮቭ ጠብ መንጃዎች እና በቁጥር 434 የሚሆኑ ተቀጣጣይ የፈንጂ ገመዶች ይገኙበታል፡፡

በተከሰተው ሁከትና ግርግር በወረዳው ኅብረተሰቡ ሲገለገልባቸው የነበሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች፣ በወረዳው የ64 አባወራ መኖሪያ ቤቶች ሲወድሙ በዚህም ከ1ሺህ 200 በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ኮማንደሩ አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያና ኅብረተሰቡ በሚገለገልበት ድልድይ ላይ ተጠምዶ የነበረ ተቀጣጣይ ፈንጂ የጸጥታ ኃይሎች ማክሸፋቸውን አስረድተዋል፡፡

በወረዳው በሁከት ፈጣሪዎች በርካታ ወንጀሎች መፈጸማቸውን የገለጹት ኃላፊው፤ የነፍስ ማጥፋት፣ ዘረፋና የቤትና የንብረት ቃጠሎ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተዘረፉ 101 የሚሆኑ የጦር መሣሪያዎች፣ ከመሥሪያ ቤቶቹ የተዘረፈ ንብረት እና ከአርሶ አደር የተዘረፉ 85 የቀንድ ከብቶችም መመለሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 4 years ago on July 18, 2020
  • By:
  • Last Modified: July 18, 2020 @ 3:21 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar