www.maledatimes.com በደምቢዶሎ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በደምቢዶሎ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

By   /   July 18, 2020  /   Comments Off on በደምቢዶሎ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 8 Second

******************

በደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የነበሩና ወደ ቤተሰቦቻቸው በመጓዝ ላይ የነበሩ “ተማሪዎችን አግተዋል” በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 17 ግለሰቦች በዛሬው ዕለት በሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው ፡፡

በእነ ከሊፋ አብዱረሂማን በሚጠራው የክስ መዝገብ ውስጥ 17 ግለሰቦች በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ 3 ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ክሱን አድምጧል፡፡

ህዳር 24 እና 25 ፣2012 በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የነበረውን ግጭት ተከትሎ በፍራቻ ወደ ቤተሰባቸው ሊሄዱ የነበሩ የአማራ ክልል ተማሪዎች በአንድ ዶልፍን መኪና ተሳፍረው ሲሄዱ በቄሌም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ ሰዬ እና አንሰሎ ወረዳዎች በሚገኙ ሚንኮና ሱዲ ቀበሌዎች መኪና በማስቆም ተማሪዎችን እየደበደቡ ጫካ በመውሰድ ለኦነግ ሸኔ አመራሮች ማስረከባቸው በክስ መዝገቡ ላይ ተገልጿል፡፡

በዛሬው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ባቀረበው ክስ 7 ተከሳች የቀረቡ ሲሆን ሁለቱ ምንም እንኳ በቁጥጥር ስር ቢውሉም በኮሮና ቫይረስ በመጠርጠራቸው በችሎቱ አልቀረቡም፡፡

ቀሪ ተከሳሾችን ፖሊስ አፈላልጎ መጥሪያ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

በእነ ከሊፋ አብዱረሂማን በሚጠራው የክስ መዝገብ ውስጥ 17 ግለሰቦች በጠቅላይ ዓቃቤ ህግ 3 ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ፣ሁለቱ ክሶች በፀረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጽ 3 ንዑስ ቁጥር ሶስት መሰረት የተፈፀመን የእገታና ጠለፋ የሽብር ወንጀልን የሚመለከቱ ናቸው፡፡

ሶስተኛው ክስ ደግሞ ተከሳሽ ተፈራ ሂካ ህዳር 26፣2012 ተማሪዎቹ በሚፈለገው ጫካ ውስጥ እየተጓዙ ሳለ መሽቶባቸው ታጋቾች መሆናቸውን እያወቀ ቤቱ በማሳደሩ እና ለየትኛውም የመንግስት አካል ባላማሳወቁ የሽብር ወንጀልን ባለማሰወቅ ወንጀል በሚል ክሶቹ መቅረባቸው ተመልክቷል፡፡

ዛሬ በአካል የቀረቡ ተከሳሾች “ጠበቃ እናቆማለን” ማለታቸውን ተከትሎ ከጠበቃቸው ጋር ተመካክረው እንዲቀርቡና ክሳቸው እንዲሰማ ችሎቱ ለሐምሌ 30፣20 12 ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

Traveler’s Alleged Crimes and Robbery at Bole Airport Raise Concerns

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar