www.maledatimes.com የአዲስ ጉዳይ ጋዜጣ አምደኛ የነበረውን እና የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ሃላፊ ክስ ቀረበበት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲስ ጉዳይ ጋዜጣ አምደኛ የነበረውን እና የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ሃላፊ ክስ ቀረበበት

By   /   November 1, 2014  /   Comments Off on የአዲስ ጉዳይ ጋዜጣ አምደኛ የነበረውን እና የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ሃላፊ ክስ ቀረበበት

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 4 Second

አዲስ ጉዳይ ጋዜጣ በመንግስት ጫና ከመዘጋቱ በፊት የጋዜጣው አምደኛ እና የሰማያዊ ፓርቲ የውጭ ግንኙነት ሃላፊ የሆነው ሰለሞን ጅማ በወያኔዎች በሚመራው የሰንደቅ ጋዜጣ ባለቤት በሆነውፋኑኤል ክንፉ መክብብና ባልደረቦቹ በተፈጠረብት ክስ መሰረት ለፍርድ ቤት እንዲቀብ ሲል ማዘዣ ሰጥተውታል ።በሌሎችም የአዲስ ጉዳዮች አምደኞች ላይ ተመሳሳይ ክስ ሊቀርብ እንደሚችልም ምንጮቻችን አክለዋል ። ይሄ እየተባባሰ የመጣውን የፕረስ ነጻነት አፈናን በግልጽ የሚጠቁም ነው ሲሉ የተናገሩት ምንጮቻችን በሌሎች ስም እና ድርጅቶች ተገን በማድረግ መንግስት የሚመሰርተውን የክስ መዝግብ እንዲያጤንበት ሲሉም መክረዋል ።

በሼክ መሃመድ ሁኔን አላህሙዲ እና በአቶ አብነት ገብረ መስቀል እየታገዘ በማስታወቂያ ሚንስትሮች የውስጥ ከፍተኛ ሚስጥር አቀባይነት እና የእኩል ንብረት ተካፋይ በሆኑት አቶ በረከት ስምኦን እና ሽመልስ ከማል የሚንቀሳቀሰው ይሄው ጋዜጣ ፡ከመንግስት በኩል በሚቀርበው ማዘዣ መሰረት በድርጅታቸው ስም በስም ማጥፋት ክስ ጋዜጠኛውን እና የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አካል የሆነውን አቶ ሰለሞን ጂማን ሊከሱት እንደሆነ ከሃገር ውስጥ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ።

እንደ ዘገባው ከሆነ በወያኔ አስተዳደራዊ ስር የሚተዳደሩት እና ነጻ ጋዜጠኞች ነን ብለው እራሳቸውን ወስነው ሆኖም ግን በመንግስት ትከሻ እራሳቸውን የሚያንቀሳቅሱት እነዚሁ ወገኖች የተለያዩ ጋዜጠኞችን ስራዎቻቸውን በንጽስር ውስጥ በማስገባት ንጹሃንን ጋዜጠኞች ወደ እስር ከሚዳርጉት ውስጥ ዋነኞቹ መሆናቸው አይዘነጋም ።

በተለይም በዛሚ ማስታወቂያ ስር የሚተላለፈው የወሮ ሚሚ ስብሃቱ ራዲዮ ፕሮግራም እና የ ሰንደቅ ጋዜጣ ከፍተኛውን የመንግስትን ድርሻ በመወጣት ለመንግስት የፕሬስ ልኡካን በመሆን የጀርባ አጥንትነታቸውን አሳይተዋል ።

በዚህ ክስ ላይ የራሱን የድርጅቱን ሰራተኞች እና የወያኔ አባላት የሆኑትን ሰዎች እንደምስክር ያቀረባቸው ከሳሽ አቶ ፋኑኤል ክንፈ መክብብ (የሰንደቅ ጋዜጣ ባለቤት) የጋዜጠኞችን ስም በማጥፋት ክሱ እንዲመሰረት ከሚያደርጉት ሰዎች መካከል አንዱ እንደሆነም መንጮጫችን ጠቁመዋል ።

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ ለሆዳቸው ያደሩ የሰንደቅ ጋዜጣ አዘጋጆች ምንም ስነ ምግባር ባልተሞላበት የጋዜጠኝነት መስመር በመጓዝ ለጥቅማቸው ሲሉ ሙያቸውን አሳልፈው የሰጡ ናቸው ሲሉ ገልጸው የተከፈተውንም ክስ የመንግስት አካላቶች ቀድመው ጫና ከማሳደራቸው በፊት እና ማናቸውንም ጋዜጠኞች ይህ ምርጫ ሲመጣ ወደ እስር ቤት የመወርወር አቅላቸውን የሚያሳጣቸውን ሃሳብ ወደ ኋላ በመተው ግድ ለሚሰጠው ሙያ ክብር በመስጠት ፍትህን በትክክለኛው መንገድ እንዲጓዝ ቢያደርጉ የተሻለ ለውጥ ሊመጣ ይችላል እንጂ በነሲብ ኣ በጥላቻ ብቻ ማናቸውንም ንጹሃን ዜጎች ወደ እስር ቤት መወርወር መፍትሄ አይሆንም ሲሉ ጠቁመዋል ።

የአዲስ ጉዳይ ጋዜጠኛ የነበረውም አቶ ሰለሞን ጂማ የተከሰሰበትም የፈጠራ ስራ እና በመንግስት እጅ የተቀነባበር ክስ እንጂ ትክክለኛ ያልሆነ እና እውነትን ያልተከተለ ነው ሲሉ ጠቁመዋል ።

ይህ በበንዲህ እንዳለ ማንኛውም ጋዜጠኛ ስለሚፈልጋቸው ነገሮች ሃሳብ የመስጠት ወይንም የመሰንዘር መብቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የሃገሪቱን የውሥጥ ፍላጎት ለሌላ ሃግር አሳልፎ የመስጠት ስራ እስካልሰራ እና ሃገሪቱን ለአደጋ እስካልዳረገ ድርስ ማንኛውንም ነገር የመጻፍ መብቱ እንዲጠበቅለት እና በሙያው ዘና ብሎ እንዲሰራ መደረግ አለበት ሲሉ አክለው ገልጸዋል ።

የዚህ የፍትህ መጓደል በእነ እስክንድር ነጋ በዞን ዘጠኝ ፣ርእዮት አለሙ ፣እና ሌሎችም ጋዜጠኞች ላይ እየተፈጸመ ያለው ሰበአዊ መብት ጥሰት ሃገሪቱን ወደ ኋላ እየጎተታት ያለው የመንግስት አሰራር ሂደት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ለአቶ ሰለሞን ጂማ የቀረበበት የክስ መዝገብ ይህንን ይመስላል

ለአቶ ሰለሞን ጂማ የቀረበበት የክስ መዝገብ ይህንን ይመስላል

charg later Maleda times 2 charg later Maleda times

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 10 years ago on November 1, 2014
  • By:
  • Last Modified: November 1, 2014 @ 2:59 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar