www.maledatimes.com አቶ ኃይለማርያም፣ የመንግሥትዎ ባህል ይቅርታ ማስጠየቅ ወይስ መጠየቅ?! አካል አልባ ይቅርታ ጠያቂው – ድህነት! በኤልያስ ገብሩ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

አቶ ኃይለማርያም፣ የመንግሥትዎ ባህል ይቅርታ ማስጠየቅ ወይስ መጠየቅ?! አካል አልባ ይቅርታ ጠያቂው – ድህነት! በኤልያስ ገብሩ

By   /   December 1, 2014  /   Comments Off on አቶ ኃይለማርያም፣ የመንግሥትዎ ባህል ይቅርታ ማስጠየቅ ወይስ መጠየቅ?! አካል አልባ ይቅርታ ጠያቂው – ድህነት! በኤልያስ ገብሩ

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 34 Second

ይህቺን ጽሑፍ በ‹‹ፍኖተ ነጻነት›› ጋዜጣ ላይ ጽፌ ላቀርብ የነበረው የዛሬ አንድ ወር ገደማ ነበር፡፡ ጽሑፏን ከጀመርኩኝ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ሳልቋጫት ዛሬ ላይ ደረስኩና በዚህ ዕትም (አራተኛ ዓመት ቁጥር 86) ለንባብ አበቃኋት፡፡ ወደጽሑፌ ላምራ፡-

የዘንድሮ የህዝብ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች መደበኛ ስብሰባ ከወራቶች በፊት በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ንግግር እና ሪፖርት በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡
በወቅቱ ፕሬዚዳንቱ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት፣ በመንግሥት ወገን ሆነው የተፈጸሙ ሀገራዊ ስኬቶችን እና ‹‹ተፈጠሩ ያሏቸውን›› መጠነኛ ችግሮች ገልጸው ነበር፡፡ በተለይ የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግርን አስመልክቶ ችግሩን ከማመን ባለፈ ኅብረተሰቡን ‹‹ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን›› እስከማለት ደርሰው ነበር፡፡
በዚህ የአራተኛው የፓርላማ ዘመን፣ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ሆነው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የፕሬዚዳንቱን ሪፖርት በመንተራስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተውላቸውም ነበር፡፡ የአቶ ግርማ ጥያቄ በቀዳሚነት ያተኮረው ፕሬዚዳንቱ የሀይል መቆራረጥ ችግርን በተመለከተ ህብረተሰቡን ‹‹ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን›› በማለት የተናገሩትን በማንሳት፣ ‹‹ያልተለመደ ቢሆንም ይቅርታ ማለት ጥሩ ነው›› በማለት ነበር፡፡
ከሳምንት በኋላ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ግርማ የፕሬዚዳንቱን ሪፖርት ተንተርሰው ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ሲጀምሩ፣ አቶ ግርማ ስለይቅርታ ጉዳይ ያነሷት ሀሳብ እንዳብከነከናቸው ከንግግራቸው መረዳት ይቻላል፡፡ አቶ ኃይለማርም፣ መንግሥታቸው የረዥም ዓመት ይቅርታ የመየጠቅ ባሀል እንዳለው፣ ሥርዓቱ ሲሳሳት ወይም ችግር ሲፈጠር ሕዝብን ይቅርታ የመጠየቅ የተለመደ ባህል ያለው መሆኑንና አቶ ግርማ ‹‹ያልተለመደ›› በማለት ያነሱትን ሃሳብ ሸንቆጥ የሚያደርግ አስተያየት በመሰንዘር ወደሌሎች ምላሾቻቸው አምርተዋል፡፡
የዚህ ጽሑፌ ዋና ነጥብ እዚህ ጋር ይጀምራል፡፡ ለሰው ልጅ ጤናማነት ወሳኝ ከሆኑ ድርጊቶች መካከል ይቅርታ ማድረግ መቻል ትልቅ ነገር መሆኑ ይገባኛል፡፡ ይቅርታ በበዳይ እና በተበዳይ መካከል የሚኖር መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ እውነተኛ ይቅር ባይነት ለበዳይም ሆነ ለተበዳይ ወሳኝ መድኃኒት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ይቅርታ ለበዳይ ውስጣዊ ሰላምን ሲሰጠው ለተበዳይ ደግሞ ጉዳቱን በተወሰነ ደረጃ ይጠግናል ተብሎ ይታመናል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ኅብረተሰቡን ይቅርታ ያሉበት ንግግር ከልብ የመነጨ ከሆነ እኔም በጥሩ ጎኑ እወስደዋለሁ፡፡ ነገር ግን፣ እንዲሁ በአፍ ለማለት ያህል (lip service) አስበው ሪፖርታቸው ውስጥ የሰነቀሯት ከሆነ ደግሞ ‹‹አጉል የተለመደ የመንግሥት አስመሳይነት›› በማለት በድርጊታቸው ማዘን ይኖርባቸዋል እላለሁ፡፡
ወደሌላ ነጥብ ስመጣ፡- ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ‹‹መንግሥታችን ይቅርታ የመጠየቅ የተለመደ ባህል አለው›› ያሉትን አነጋገር በግልጽ እተቻለሁ፡፡ ሥርዓቱ ሥልጣን ከመጨበጡ በፊትም ይህ ያሉት የይቅርታ ባሀል እንደነበረውም ሊነግሩን ሞክረዋል – ጠቅላያችን! ይህ ሚዛን አይደፋም፡፡ እሳቸው ቢሆኑ የ‹‹ድል አጥቢያ›› የሥርዓቱ ሰው ሆነው ስለቀደመው የትጥቅ ትግል ባህል ሊነግሩን መታተራቸው ያስገምታቸዋል፡፡ በዚያን በትግሉ ወቅት የነበሩ የሥርዓቱ ታጋዮች የ‹‹ይቅርታ ባህሉ››ን ጉዳይ ቢነግሩን ኖሮ ደስ ይል ነበር፤ በእነሱ ያምራል፡፡
እንደጠ/ሚኒሥትራችን ሁሉ፣ በአሁን ወቅት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን በ2002 ቱ አራተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ወቅት፣ ፓርቲያቸውን ወክለው የምርጫ ክርክር ሲያደርጉ፣ ከሥርዓቱ ጋር ታግለው፣ የትናንት ነጻ አውጪዎችን ለመንግሥትነት ካበቁት ሰዎች መካከል ግንባር ቀደም የነበሩትን አቶ ስዬ አብርሃን ‹‹እኛ አራግፈን የጣልናቸውን …›› በማለት ሊያቀሏቸው ሲሞክሩ ተስተውሏል፡፡ ይህ የማያስከብር የ‹‹ድል አጥቢያ የእኔነት በሽታ!›› ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በወቅቱ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ስዬ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ወክለው በትግራይ ክልል ተንቤን ወረዳ መወዳደራቸው ይታወሳል፡፡
ወደአቶ ኃይለማርያም ስመለስ፣ የትግል ወቅቱን ትተው፣ ለ23 ዓመታት በሥልጣን ላይ የሚገኝ መንግሥታቸው፣ ሰፊውን ሕዝብ የቱ ጋር እና በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ነበር ይቅርታ ሲጠይቅ የተስተዋለው? በማለት ጥያቄዬን አቀርብላቸዋለሁ፡፡ መንግሥት ‹‹ይቅርታ የመጠየቅ ባህል›› ከነበረው ባህል በተደጋጋሚ የሚደረግ ማኅበራዊ ልምድ ነውና መቼ ነው ደጋግሞ ሕዝብን ተጸጽቶ ይቅርታ የጠየቀው? ለየትኛዎቹ ጉዳዮችስ ይሆን መንግሥት ‹‹ይቅርታ የመጠየቅ›› ባህሉን ተጠቅሞ ይቅርታ ሲጠይቀን የተገኘው? ከእነዚህ ነጥቦች አኳያ አቶ ኃይለማርያም ምሳሌዎችን እያጣቀሱ እና መረጃዎችን በመንተራስ በምላሻቸው ውስጥ ቢያካትቱት ኖሮ ‹‹አለን›› የሚሉትን የይቅርታ ባህል እንመለከተው ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ባናውቀው እንኳ እንደአዲስ እንገነዘበው ነበር፡፡ ግን፣ ምላሻቸው ‹‹እንዲህ ብዬ መመለስ›› አለብኝ ከሚል የአንባገነንነት አንደበት የፈለቀ መሆኑ ይሰማኛል፡፡
አካል አልባው ይቅርታ ጠያቂው – ድህነት!
———————
በግሌ ሥርዓቱ ይቅርታ የመጠየቅ ባህል ሳይሆን ይቅርታ የማስጠየቅ የተለመደ ባህል አለው እላለሁ፡፡ ጥቂት ምለሳሌዎችን ላንሳ፡- በአንድ ወቅት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ እንዲሁ በፓርላማ ውስጥ ከኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግር ጋር በተያያዘ መንግሥታቸው ይቅርታ መጠየቅ እንደሚኖርበት በአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ ተጠይቀው ነበር፡፡ አቶ መለስ ግን ‹‹ችግሩን የፈጠረው ድህነታችን ነው፡፡ ለዚህ ችግር ይቅርታ መጠየቅ ካለበት፣ ይቅርታ ማለት የሚኖርበት ራሱ ድህነት ነው›› የሚል አስገራሚ ንግግር መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ድህነት አካል የለውም፡፡ አካል የሌለውን ነገር ነው እንግዲህ አቶ መለስ በድፍረት ይቅርታ ይበል ያሉት፡፡ ታዲያ ተተኪው አቶ ኃይለማሪያምም የ‹‹ይቅርታ ባህል አለን›› የሚሉት ይህንን ይሆን?! የ‹‹ሥርዓቱ ባህል ይቅርታ ማስጠየቅ ነው›› ስል አንድም ከዚህ ተነስቼ ነው፡፡ ሥርዓቱ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ግዑዝ የሆነውንም ድህነትንም ይቅርታ የሚያስብል ‹‹ጎብዝ ጀግና›› መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡
ይህም ብቻ አይደለም፤ የ1997 ዓ.ም ሀገር ዓቀፍ ምርጫን ተከትሎ የተፈጠረውን ግርግር በመንተራስ ለእስር የተዳረጉ የቅንጅት አመራሮች እና የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ እስከዕድሜ ልክ የሚደርስ ፍርድ ካስፈረደ በኋላ ከእስር የተለቀቁት የ‹‹ይቅርታ ፎርም›› ሞልተው መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሳ በስዊድን ሀገር ከእስር የወጡበትን እውነታ ከተናገሩ በኋላ ‹‹የተናገርሽውን አስተባብይ አለበለዚያ ይቅርታሽ ይነሳል›› ተብለው ወ/ሮዋ ‹‹ቃሌ›› በሚለው ሀሳባቸው በመጽናታቸው ለዳግም የሁለት ዓመት እስር ተዳርገው ነበር፡፡ ወ/ት ብርትኳን ከቃሊቲ የተፈቱት ‹‹በይቅርታ›› መሆኑ ይታወሳል፡፡ ወ/ሮዋ ይቅርታ እንዲጠይቁ ተደርገው ከእስር መውጣታቸውን ከሚያምኑ ሰዎች መካከል እኔ አንዱ ነኝ፡፡
የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና አቶ ስዬ አብርሃ በ2002 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ከአንድነት ፓርቲ ጋር በይፋ መቀላቀላቸውን ሲያስታውቁ፣ ዶ/ር ነጋሶ ‹‹ሕገ መንግሥቱ ሲረቀቅ ህዝቡን አወያተን ነው ያልኩት ስህተት ስለሆነ የኢትዮጵን ህዝብ በይፋ ይቅርታ እጠይቃለሁ›› ሲሉ አቶ ስዬ አብርሃ ግን የ‹‹ኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ለመየጠቅ ገና አልደረሰም›› የሚል ይዘት ያለው ሀሳብ መዘንዘራቸው ይታወሳል፡፡ የ‹‹ድል አጥቢያው›› ፕሬዚዳንት ላጠፉት ጥፋት ይቅርታ በይፋ ሲጠይቁ ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ከሥርዓቱ ጋር አብረው የነበሩት የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ግን ‹‹ገና ነው›› የሚል ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ አቶ ኃይለማርያም ሥርዓቱ የቀደመ ይቅርታ የመጠየቅ ባህል እንደነበረው የተነጋሩትን በትልቅ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንድንከት ያስገድደናል፡፡ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው 11 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ስውዲናዊያን ጋዜጠኞች ከእስር የወጡት በይቅርታ መሆኑስ እንዴት ይዘነጋል? በዚህ ጉዳይ ሌላም የተለያዩ ምሳሌዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ አቶ ኃይለማርያም ‹‹መንግሥታችን የተለመደ የይቅርታ ባህል አለው›› ያሉትን እንኳ ተውዋት፡፡ ሥርዓትዎ ይቅርታ የመጠየቅ ሳይሆን የማስጠየቅ ልምድ ነው ያለው፡፡ ‹‹አይ ይቅርታ የመጠየቅ ልምድ ነው ያለን›› የሚሉም ከሆነ ሀሳብ አቅርቡና በሀሳብ መሟገት እንችላለን፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

አቶ ኃይለማርያም፣ የመንግሥትዎ ባህል ይቅርታ ማስጠየቅ ወይስ መጠየቅ?!
አካል አልባ ይቅርታ ጠያቂው  - ድህነት!
---------------
ይህቺን ጽሑፍ በ‹‹ፍኖተ ነጻነት›› ጋዜጣ ላይ ጽፌ ላቀርብ የነበረው የዛሬ አንድ ወር ገደማ ነበር፡፡ ጽሑፏን ከጀመርኩኝ በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች ሳልቋጫት ዛሬ ላይ ደረስኩና በዚህ ዕትም (አራተኛ ዓመት ቁጥር 86) ለንባብ አበቃኋት፡፡ ወደጽሑፌ ላምራ፡-
የዘንድሮ የህዝብ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች መደበኛ ስብሰባ ከወራቶች በፊት በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ንግግር እና ሪፖርት በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ 
በወቅቱ ፕሬዚዳንቱ በርካታ ሀገራዊ ጉዳዮችን በማንሳት፣ በመንግሥት ወገን ሆነው የተፈጸሙ ሀገራዊ ስኬቶችን እና ‹‹ተፈጠሩ ያሏቸውን›› መጠነኛ ችግሮች ገልጸው ነበር፡፡ በተለይ የኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግርን አስመልክቶ ችግሩን ከማመን ባለፈ ኅብረተሰቡን ‹‹ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን›› እስከማለት ደርሰው ነበር፡፡
በዚህ የአራተኛው የፓርላማ ዘመን፣ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራር ሆነው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የፕሬዚዳንቱን ሪፖርት በመንተራስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተውላቸውም ነበር፡፡ የአቶ ግርማ ጥያቄ በቀዳሚነት ያተኮረው ፕሬዚዳንቱ የሀይል መቆራረጥ ችግርን በተመለከተ ህብረተሰቡን ‹‹ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን›› በማለት የተናገሩትን በማንሳት፣ ‹‹ያልተለመደ ቢሆንም ይቅርታ ማለት ጥሩ  ነው›› በማለት ነበር፡፡
ከሳምንት በኋላ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ አቶ ግርማ የፕሬዚዳንቱን ሪፖርት ተንተርሰው ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ሲጀምሩ፣ አቶ ግርማ ስለይቅርታ ጉዳይ ያነሷት ሀሳብ እንዳብከነከናቸው ከንግግራቸው መረዳት ይቻላል፡፡ አቶ ኃይለማርም፣ መንግሥታቸው የረዥም ዓመት ይቅርታ የመየጠቅ ባሀል እንዳለው፣ ሥርዓቱ ሲሳሳት ወይም ችግር ሲፈጠር ሕዝብን ይቅርታ የመጠየቅ የተለመደ ባህል ያለው መሆኑንና አቶ ግርማ ‹‹ያልተለመደ›› በማለት ያነሱትን ሃሳብ ሸንቆጥ የሚያደርግ አስተያየት በመሰንዘር ወደሌሎች ምላሾቻቸው አምርተዋል፡፡
የዚህ ጽሑፌ ዋና ነጥብ እዚህ ጋር ይጀምራል፡፡ ለሰው ልጅ ጤናማነት ወሳኝ ከሆኑ ድርጊቶች መካከል ይቅርታ ማድረግ መቻል ትልቅ ነገር መሆኑ ይገባኛል፡፡ ይቅርታ በበዳይ እና በተበዳይ መካከል የሚኖር መሠረታዊ ነገር ነው፡፡ እውነተኛ ይቅር ባይነት ለበዳይም ሆነ ለተበዳይ ወሳኝ መድኃኒት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ይቅርታ ለበዳይ ውስጣዊ ሰላምን ሲሰጠው ለተበዳይ ደግሞ ጉዳቱን በተወሰነ ደረጃ ይጠግናል ተብሎ ይታመናል፡፡
የፕሬዚዳንቱ ኅብረተሰቡን ይቅርታ ያሉበት ንግግር ከልብ የመነጨ ከሆነ እኔም በጥሩ ጎኑ እወስደዋለሁ፡፡ ነገር ግን፣ እንዲሁ በአፍ ለማለት ያህል (lip service) አስበው ሪፖርታቸው ውስጥ የሰነቀሯት ከሆነ ደግሞ ‹‹አጉል የተለመደ የመንግሥት አስመሳይነት›› በማለት በድርጊታቸው ማዘን ይኖርባቸዋል እላለሁ፡፡
ወደሌላ ነጥብ ስመጣ፡- ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም ‹‹መንግሥታችን ይቅርታ የመጠየቅ የተለመደ ባህል አለው›› ያሉትን አነጋገር በግልጽ እተቻለሁ፡፡ ሥርዓቱ ሥልጣን ከመጨበጡ በፊትም ይህ ያሉት የይቅርታ ባሀል እንደነበረውም ሊነግሩን ሞክረዋል - ጠቅላያችን! ይህ ሚዛን አይደፋም፡፡ እሳቸው ቢሆኑ የ‹‹ድል አጥቢያ›› የሥርዓቱ ሰው ሆነው ስለቀደመው የትጥቅ ትግል ባህል ሊነግሩን መታተራቸው ያስገምታቸዋል፡፡ በዚያን በትግሉ ወቅት የነበሩ የሥርዓቱ ታጋዮች የ‹‹ይቅርታ ባህሉ››ን ጉዳይ ቢነግሩን ኖሮ ደስ ይል ነበር፤ በእነሱ ያምራል፡፡
እንደጠ/ሚኒሥትራችን ሁሉ፣ በአሁን ወቅት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን በ2002 ቱ አራተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ወቅት፣ ፓርቲያቸውን ወክለው የምርጫ ክርክር ሲያደርጉ፣ ከሥርዓቱ ጋር ታግለው፣ የትናንት ነጻ አውጪዎችን ለመንግሥትነት   ካበቁት ሰዎች መካከል ግንባር ቀደም የነበሩትን አቶ ስዬ አብርሃን ‹‹እኛ አራግፈን የጣልናቸውን …›› በማለት ሊያቀሏቸው ሲሞክሩ ተስተውሏል፡፡ ይህ የማያስከብር የ‹‹ድል አጥቢያ የእኔነት በሽታ!›› ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በወቅቱ የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ስዬ፣ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ወክለው በትግራይ ክልል ተንቤን ወረዳ መወዳደራቸው ይታወሳል፡፡ 
  ወደአቶ ኃይለማርያም ስመለስ፣ የትግል ወቅቱን ትተው፣ ለ23 ዓመታት በሥልጣን ላይ የሚገኝ መንግሥታቸው፣ ሰፊውን ሕዝብ የቱ ጋር እና በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ነበር ይቅርታ ሲጠይቅ የተስተዋለው? በማለት ጥያቄዬን አቀርብላቸዋለሁ፡፡ መንግሥት ‹‹ይቅርታ የመጠየቅ ባህል›› ከነበረው ባህል በተደጋጋሚ የሚደረግ ማኅበራዊ ልምድ ነውና መቼ ነው ደጋግሞ ሕዝብን ተጸጽቶ ይቅርታ የጠየቀው? ለየትኛዎቹ ጉዳዮችስ ይሆን መንግሥት ‹‹ይቅርታ የመጠየቅ›› ባህሉን ተጠቅሞ ይቅርታ ሲጠይቀን የተገኘው? ከእነዚህ ነጥቦች አኳያ አቶ ኃይለማርያም ምሳሌዎችን እያጣቀሱ እና መረጃዎችን በመንተራስ በምላሻቸው ውስጥ ቢያካትቱት ኖሮ ‹‹አለን›› የሚሉትን የይቅርታ ባህል እንመለከተው ነበር፡፡ ከዚህ ቀደም ባናውቀው እንኳ እንደአዲስ እንገነዘበው ነበር፡፡ ግን፣ ምላሻቸው ‹‹እንዲህ ብዬ መመለስ›› አለብኝ ከሚል የአንባገነንነት አንደበት የፈለቀ መሆኑ ይሰማኛል፡፡ 
አካል አልባው ይቅርታ ጠያቂው  - ድህነት!
---------------------
በግሌ ሥርዓቱ ይቅርታ የመጠየቅ ባህል ሳይሆን ይቅርታ የማስጠየቅ የተለመደ ባህል አለው እላለሁ፡፡ ጥቂት ምለሳሌዎችን ላንሳ፡- በአንድ ወቅት የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ እንዲሁ በፓርላማ ውስጥ ከኤሌክትሪክ ሀይል መቆራረጥ ችግር ጋር በተያያዘ መንግሥታቸው ይቅርታ መጠየቅ እንደሚኖርበት በአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተወካይ ተጠይቀው ነበር፡፡ አቶ መለስ ግን ‹‹ችግሩን የፈጠረው ድህነታችን ነው፡፡ ለዚህ ችግር ይቅርታ መጠየቅ ካለበት፣ ይቅርታ ማለት የሚኖርበት ራሱ ድህነት ነው›› የሚል አስገራሚ ንግግር መናገራቸው ይታወሳል፡፡ ድህነት አካል የለውም፡፡ አካል የሌለውን ነገር ነው እንግዲህ አቶ መለስ በድፍረት ይቅርታ ይበል ያሉት፡፡ ታዲያ ተተኪው አቶ ኃይለማሪያምም የ‹‹ይቅርታ ባህል አለን›› የሚሉት ይህንን ይሆን?! የ‹‹ሥርዓቱ ባህል ይቅርታ ማስጠየቅ ነው›› ስል አንድም ከዚህ ተነስቼ ነው፡፡ ሥርዓቱ ሰዎችን ብቻ ሳይሆን ግዑዝ የሆነውንም ድህነትንም ይቅርታ የሚያስብል ‹‹ጎብዝ ጀግና›› መሆኑን ማየት ይቻላል፡፡ 
ይህም ብቻ አይደለም፤ የ1997 ዓ.ም ሀገር ዓቀፍ ምርጫን ተከትሎ የተፈጠረውን ግርግር በመንተራስ ለእስር የተዳረጉ የቅንጅት አመራሮች እና የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች ላይ እስከዕድሜ ልክ የሚደርስ ፍርድ ካስፈረደ በኋላ ከእስር የተለቀቁት የ‹‹ይቅርታ ፎርም›› ሞልተው መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡
የቅንጅት አመራሮች ከእስር ከወጡ በኋላ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሳ በስዊድን ሀገር ከእስር የወጡበትን እውነታ ከተናገሩ በኋላ  ‹‹የተናገርሽውን አስተባብይ አለበለዚያ ይቅርታሽ ይነሳል›› ተብለው ወ/ሮዋ ‹‹ቃሌ›› በሚለው ሀሳባቸው በመጽናታቸው ለዳግም የሁለት ዓመት እስር ተዳርገው ነበር፡፡ ወ/ት ብርትኳን ከቃሊቲ የተፈቱት ‹‹በይቅርታ›› መሆኑ ይታወሳል፡፡ ወ/ሮዋ ይቅርታ እንዲጠይቁ ተደርገው ከእስር መውጣታቸውን  ከሚያምኑ ሰዎች መካከል እኔ አንዱ ነኝ፡፡
የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና አቶ ስዬ አብርሃ በ2002 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ከአንድነት ፓርቲ ጋር በይፋ መቀላቀላቸውን ሲያስታውቁ፣ ዶ/ር ነጋሶ ‹‹ሕገ መንግሥቱ ሲረቀቅ ህዝቡን አወያተን ነው ያልኩት ስህተት ስለሆነ የኢትዮጵን ህዝብ በይፋ ይቅርታ እጠይቃለሁ›› ሲሉ አቶ ስዬ አብርሃ ግን የ‹‹ኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ለመየጠቅ ገና አልደረሰም›› የሚል ይዘት ያለው ሀሳብ መዘንዘራቸው ይታወሳል፡፡ የ‹‹ድል አጥቢያው›› ፕሬዚዳንት ላጠፉት ጥፋት ይቅርታ በይፋ ሲጠይቁ ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ ከሥርዓቱ ጋር አብረው የነበሩት የቀድሞ የመከላከያ ሚኒስትር ግን  ‹‹ገና ነው›› የሚል ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ አቶ ኃይለማርያም ሥርዓቱ የቀደመ ይቅርታ የመጠየቅ ባህል እንደነበረው የተነጋሩትን በትልቅ ጥያቄ ምልክት ውስጥ እንድንከት ያስገድደናል፡፡ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው 11 ዓመት ጽኑ እስራት ተፈርዶባቸው የነበሩት ሁለት ስውዲናዊያን ጋዜጠኞች ከእስር የወጡት በይቅርታ መሆኑስ እንዴት ይዘነጋል? በዚህ ጉዳይ ሌላም የተለያዩ ምሳሌዎችን ማንሳት ይቻላል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ አቶ ኃይለማርያም ‹‹መንግሥታችን የተለመደ የይቅርታ ባህል አለው›› ያሉትን እንኳ ተውዋት፡፡ ሥርዓትዎ ይቅርታ የመጠየቅ ሳይሆን የማስጠየቅ ልምድ ነው ያለው፡፡ ‹‹አይ ይቅርታ የመጠየቅ ልምድ ነው ያለን›› የሚሉም ከሆነ ሀሳብ አቅርቡና በሀሳብ መሟገት እንችላለን፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on December 1, 2014
  • By:
  • Last Modified: December 1, 2014 @ 6:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar