www.maledatimes.com ታላላቅ አባቶቻችን እና የፈረሳቸው ስም dawit kebed - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ታላላቅ አባቶቻችን እና የፈረሳቸው ስም dawit kebed

By   /   February 22, 2015  /   Comments Off on ታላላቅ አባቶቻችን እና የፈረሳቸው ስም dawit kebed

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 14 Second
የ30 ያህል የፈረስ ስሞች እና ጀግኖች አባቶቻችን ዝርዝር ተመለከትኩ። የአንዳንዶቹ ታሪካዊ ሰዎች ስም ባለመስፈሩ ስለአንዳንዶቹ ታሪክ ጭምር ጻፍኩኝና ወደ ፌስ ቡክ ስመለስ ቀደም ሲል የተጻፉትን፤ የ30 ሰዎች ስም ዝርዝር ብፈልግ ብፈልግ አጣሁት። እንግዲህ በፍለጋ ግዜ በከንቱ ላለማባከን፤ ይህ ያዘጋጀሁትም ጽሁፍ ሳይለጠፍ እንዳይቀር በማለት እነሆ ትንሽ ወግ ላካፍላቹህ ወደድኩ።
ከ30ዎቹ ዝርዝር ውስጥ የልጅ እያሱ፣ የበላይ ዘለቀ፣ የራስ ሃጎስ፣ የራስ ደረሶ፣ የደጃች ገረሱ ዱኪ፣ የደጃች አያሌው ብሩ ፈረሶች ስም አላየሁም። የነዚህ ጀግኖች ስም ደሞ ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትምና ይቺን ማስታወሻ አዘጋጀሁ። በነገራችን ላይ እንዲያው የፈረስ ስም ይባል እንጂ፤ አንዳንድ የፈረስ ስም ዘመኑን ወይም የፈረሱን ባለቤት ባህሪ ጭምር ያንጸባርቃል። ለምሳሌ የምኒልክ ፈረስ አባ ዳኘው ሲባል፤ በዘመኑ አጼ ምኒልክ የዳኝነት እና የፍትህ ስርአት መዘርጋታቸውን ለማሳየት ጭምር ነው።
ሌላም ምሳሌ ልስጥ። ደጃች አያሌው ብሩ የፈረሳቸው ስም አባ ይርጋ ይባል ነበር። ከምኒልክ ዘመን ጀምሮ በልጅ እያሱም፣ በንግሥት ዘውዲቱም፤ ደጃዝማች ተብለው ከፍም ዝቅም ሳይሉ በዚህ ማዕረግ ብቻ ረግተው ብዙ ቆዩ። “የራስነት ማዕረግ ይሰጥዎታል” ተብለው ቤጌምድርን ሲያስተዳድሩ ቆይተው ከጣልያን ተዋግተው እና ታስረው ወጥተውም፣ በ1940 እስኪሞቱ ድረስ የደጃዝማችነት ማዕረጋቸው እንደረጋ ነበር የቆየው። እናም የፈረሳቸው ስም እንደሳቸው የደጃዝማችነት ማዕረግ በዚያው ረግቶ ስለቆየ፤ “አባ ይርጋ” ተብሎ ቀረ።
የጎጃሙ ራስ ደረሶ ደግሞ ጸብ ወዳድ ነበሩ። ከእምባቦ ጦርነት በፊት ከራስ ጎበና ጋር ጭምር ተዋግተዋል። ፈረሳቸውንም የሳቸውን ባህሪ ተከትሎ፤ “አባ ጠቦ” ተብሎ ይጠራ ነበር። አንዳንዴ ከፈረስ ስም ውጪ ህዝቡም የሚሰጠውን የፈረስ ስም መዘንጋት የለብንም። ለምሳሌ የፊታውራሪ የፈረስ ስም አባ መቻል ሆኖ ሳለ፤ በፍርድ አዋቂነታቸውና በጦርነት ግዜ መላ ስለማያጡ ህዝቡ እስካሁን “አባ መላ” በሚለው የፈረስ ስማቸው ነው የሚያውቃቸው።
በላይ ዘለቀ በፈረስ እየጋለበ ጦርነት ሲያካሂድ የነበረበትን ታሪክ ብዙም አናውቅም። ሆኖም የበላይ ዘለቀን ኮስታራነት የተመለከተው ህዝብ በላይ ዘለቀንም “አባ ኮስትር” ነበር ብሎ የሚጠራው – በ1937 አዲስ አበባ ውስጥ፡ በስቅላት መገደሉ ሳይዘነጋ።
አባ ፈንቅል ደግሞ የትግራዩ ራስ ሃጎስ ፈረስ ስም ነው። ብዙዎች በታሪክ የምታውቋቸው ራስ አሉላ አባነጋ በዶጋሊ እና ሰሐጢ ላይ ዬሩትን ታላቅ ገድል እንጂ ስለአሟሟታቸው ብዙም አናውቅም። ራስ አሉላ አባ ነጋ ከአባ ፈንቅል ጋር በተራ የድንበር ጸብ ምክንያት ጦርነት ገጥመው ነው የሞቱት። የሞቱትም ጥር 10፣ 1891 ነበር።
የኦሮሞው ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ የፈረስ ስም ደሞ አባ ቦራ ነበር። በነገርዎ ላይ ደጃዝማች ገረሱ ዱኪ፤ በአምስቱ አመት የጣልያን ወረራ ወቅት ከሸዋ እስከ ጅማ፤ ከጅማ እስከ ኢሉ አባ ቦር ድረስ እየተዘዋወሩ ብዙ ጀብዱ የፈጸሙ ጀግና ናቸው። እንደአያሌው ብሩ በደጃዝማችነት ማዕረግ መቅረታቸው ቅር እንዳላቸው ነው የሞቱት። ታዲያ እሳቸው የ’ራስነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው ሳይሆን የፊታውራሪነት ማዕረግ ነበር የፈለጉት። ፊታውራሪነት በተለይ ለጦር መሪ የሚሰጥ ማረግ ሲሆን፤ የፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ፈረሰኛም ሆነው በጦር መሪነት ብዙ የሰሩ ነበሩ – በ1958 ነው የሞቱት።
እንዳላሰለች በማለት… በመጨረሻ የልጅ እያሱ ፈረስን አስታውሼ በዚሁ ላብቃ። ልጅ እያሱ በነገሱበት ወቅት አገሩ ሁሉ ከዳር እስከ ዳር ሰላም ሆኖ ነበር። አገር ሰላም ሲሆን ደግሞ ስለፍቅር እና ስለጤና ነው የሚወራው። እናም በዚህ የሰላም እና የጤና ዘመን ላይ የደረሱት ልጅ እያሱ፤ ፈረሳቸውም አባ ጤና ተባለ። ለናንተም ጤና ይስጥልን።
(የሰላሳዎቹን ስም ዝርዝር እንዳገኘሁ እለጥፋለሁ፤ ወይም ያገኛቹህ ለጥፉልን።) የህን መሰለኝ ያለከው ከ Getachew Shiferaw የተገኘ ነው።
ታላላቅ አባቶቻችን እና የፈረሳቸው ስም በጥቂቱ
………………………………………………….

1. አባ ዞብል……………አጼ ፋሲል
2. አባ ታጠቅ………….አጼ ቴዎድሮስ
3. አባ በዝብዝ…………አጼ ዮሃንስ
4. አባ ዲና ………… ሳህለ-ስላሴ ንጉስ ሸዋ
5. አባ ዳምጠው……. ሀይለ-መለኮት ንጉስ ሸዋ
6. አባ ዳኛው ………..አጼ ምኒልክ
7. አባ ጎራው…………..ፊት አውራሪ ገበየሁ
8. አባ ጠና…………….ንጉስ ተክለ-ሀይማኖት
9. አባ ጠጣው………….ራስ ወሌ
10. አባ ነፍሶ …………..ደጃች ባልቻ ሳፎ
11. አባ ግርሻ……………ራስ ዳርጌ
12. አባ ጥጉ……………..ራስ ጎበና
13. አባ መቻል………….ፊታውራሪ ሀብተ-ጊወርጊስ (አባ መላ)
14. አባ ነጋ………………ራስ አሉላ
15. አባ ሻንቆ……………ንጉስ ሚካኤል
16. አባ ቃኘው…………..ራስ መኮንን
17. አባ ጅፋር…………..አባ ጅፋር ንጉስ ጂማ
18. አባ ጠቅል………….አጼ ሀይለ ስላሴ
19. አባ ሰጉድ…………..ንጉስ ወልደ ጊዎርጊስ
20. አባ ቀስቅስ………….ልዑል ራስ እምሩ ሀይለስላሴ
21. አባ ቀስቅስ………….ልዑል ራስ ካሳ ሀይሉ
22. አባ ዳማ……………..አፈ ንጉስ ነሲቡ
23. አባ ገስጥ……………..ራስ አበበ አረጋይ
24. አባ ቀማው……………ራስ ደስታ የጎጃም ባላባት
25. አባ ደልድል………….ራስ ዘውዴ
26. አባ ቀማው……………ራስ ቢትወድድ ተሰማ
27. አባ ይትረፍ…………..ራስ አባተ
28. አባ ጋተው……………ቀኛዝማች መኮንን ወልደ ገብርዔል
29. አባ ድክር…………….አቶ በዛብህ
30. አባ ናዳ……………….አቶ ክብረት (የመራቤቴ አርበኛ)
አባቶቻችን ከእነዚህ ፈረሶቻቸው ጋር ነበር በዱር በገደሉ እየተዋደቁ ነጻይቱን ኢትዮጵያን ያስረከቡኝ፡፡ ምንም እንኳን ልጆቻቸው ታሪክ አስቀጣይ ባንሆንም ቅሉ፡፡
ማሳሰቢያ፤ እነዚህ ከላይ የተቃቀስኳቸው እኔ የማውቃቸውን እና መረጃ አገላብጨ ያገኘኋቸውን ብቻ ነው፡፡ የበለጠ መረጃ ያላችሁ ብትጨምሩበት ታሪኩ ሙሉ ይሆናል፡፡ የተሳሳትኩት ካለም ለመታረም ፈቃደኛ ነኝ፡፡ ክብር ለታላላቆቻችን ይሁን፡፡
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on February 22, 2015
  • By:
  • Last Modified: February 22, 2015 @ 1:54 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar