www.maledatimes.com እንባ ያራጨን ዜና - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

እንባ ያራጨን ዜና

By   /   April 11, 2015  /   Comments Off on እንባ ያራጨን ዜና

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 58 Second

33333222

እርቧቸው ከእስር ቤት ሊያመልጡ ሲሉ 2 ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ 10 ቆሰሉ

700 ኢትዮጵያዊያን በየመን እስር ቤት በርሃብ ሊያልቁ ነው

በግሩም ተ/ሀይማኖት

ከየመን ኢሚግሬሽን እስር ቤት ውስጥ ሊያመልጡ ያሉ 2 ኢትዮጵያዊያ ተገደሉ 11 ቆሰሉ የሚል ወሬ ትላንት ማታ (አርብ) ሰማሁ፡፡ የሰማሁትን ወሬ እርግጠኛ ነው አይደለም ለማለት ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ወደ ኢሚግሬሽን (ጀዋዛት) እስር ቤት ሄድኩ፡፡ በእውነቱ ስደት ከወጣሁበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ አይነት አሰቃቂ በርሀብ መጠውለግ አላየሁም፡፡ ከ15 አመት ልጅ ጀምሮ በእስር ቤቱ ውስጥ ታፍገዋል፡፡

ክስት፣ ጥውልግ ብለው ተስፋ መቁረጥ፣ ሞት አፋፍ ላይ ያማከለ ተክለሰውነት ዝብርቅርቅ ሆነው ታዩኝ፡፡ እዚህ ሀገር ቆይቼ እስከመቼ የሰዎችን ችግር እያየሁ አነባለሁ? የሚል ጥያቄ ውስጤ ተላወሰ፡፡ ዮሴፍ ልጆቹን የማናግረበት ድረስ መጣና የቆምክበትን ቦታ አይተኸዋል? አለኝ፡፡ አይኔን ርሃብ ካጎሳቆላቸው እና ካቦሳቆላቸው ልጆች ላይ መንጭቄ አነሳሁና በፍጥነት የቆምኩበትን መሬት አየሁት፡፡ የገፋኝ መሰለኝ፡፡ ደም…የወገኖቼ ደም ላይ ነው የቆምኩት፡፡ ለካ የተመቱበት ቦታ ላይ ነበርኩ፡፡ ራሴን አዞረኝ፡፡ አጥወለወለኝ፡፡ ቋቅ የሚለኝ ሁሉ መሰለኝ አጥወለወለኝ፡፡ ርሀብ የጎዳውን ሰውነት ጥይት ሲነድለው በሀሳብ አየሁና ጩህ ጩህ አለኝ፡፡

ልጆቹ ውሃ ውሃ አምጣልን እባክህ ጥም ልንሞት ነው አሉኝ ግማሹ ሲጋራ ይለምናል ግማሹ ስልክ ወደቤተሰቡ መደወል ይፈልጋል፡፡ ምንም እንኳን እኔም ሞት ያጠላበት ከአናቴ የጄት ጥይት የሚወነጨፍበት ቦታ በሰቀቀን ቢሆንም ያለሁት እነሱ ላይ ሞትን ገዝፎ አየሁት፡፡ ሞት አስፍስፎ ሊውጣቸው የተዘጋጀ መሰለኝ፡፡ በመጥፎ አጋጣሚ ላይ ሆኜ ስላገኘኋቸው አዘንኩ፡፡ ነገር ከፍቶ ነገር ሰፍቶ ከተማዋ ሞት አርግዞ ሊፈነጭባት ከሬሳ ሳጥን ጎን ሆና በጦር መሳሪያ በተቀነባበረ ሙዚቃ ትደነክራለች፡፡

አብረውኝ ያሉት ካልድ ለገሰ እና የሴፍ ግራ ተጋብተዋል ሁኔታው ሁላችንንም ነው ያስደነገጠው፡፡ እስከመቼስ ደማችን በየቦታው ይፈሳል? እስረኞቹ እጅ እጃችን እያዩን ነው፡፡ የምንችለውን ያህል አድርገን ወጣን፡፡ ከልጆቹ ያገኘሁትን መረጃ እነሆ፡-

በየመን ሰነዓ ኢምግሬሽን እስር ቤት ውስጥ ከ700 በላይ ኢትዮጵያዊያን በርሃብ ከማለቃችን ብለው ለማምለጥ ባደረጉት እንቅስቃሴ 2 ተገደሉ 11 ደግሞ ቆሰሉ አሉን፡፡ ምግብ ማቅረብ አንችልም ብለዋቸው ጥሬ ሩዝ ተሰጥቷቸው ራሳቸው አብስለው በቀን አንዴ ነው የሚበሉት፡፡ እሱም ካለቀ የለም ስለተባሉ በቁጠባ የመቃመስ ያህል ነው የሚበሉት፡፡ ማታ ደግሞ አንዳንድ ዳቦ ይሰጣቸዋል፡፡ በመራባቸው ምክንያት ተደጋጋሚ ጩኸትም ረብሻም ቢደርጉ ምንም መፍትሄ አላገኙም፡፡ በርሀብ ከማለቃቸው በፊት እስር ቤቱን ጥለው መውጣት ፈልገው ቢጠይቁም ስላልተፈቀደላቸው ለማምለጥ ሞከሩ፡፡ የሚግሬሽን እስር ቤቱ ጊቢ ያሉበት አጥር ብቻ መስሏቸው ነበር፡፡ ሶስት ዙር አጥር እንዳለው አላወቁም፡፡ በሩ ሲከፈት ጠብቀው ለማምለጥ ሞከሩ፡፡ ተኩስ ተከፈተባቸው፡፡

ሁለቱ ሞቱ 11 ያሉ ቆሰሉ፡፡ የቀሩት በዱላ እስኪበቃቸው ተወገሩ፡፡ ርሃቡ ግን አሁንም ያለ ነው፡፡ ሁሌም ለበዓል ዕለት እንደማደርገው ነገ እሁድን አብረን ከእስረኞች ጋር ምሳ ለመብላትና ለማብላት ተዘጋጅቻለሁ፡፡ ግን ያዘጋጀሁት ለነገ የበዓልን ብቻ ነው፡፡ ከነገ በኋላ እንዴት ይሆን ርሀቡን የሚገፉት፡፡

ጥሪ፡- እባካችሁ በተለይ የመን ያላችሁ ወገኖች አቅም ያላችሁ በቻላችሁት መጠን ከምንጎርሰውም ቢሆን እያጎረስን ህይወታቸውን እንታደግ፡፡ አቅሙ የሌላችሁ በስራም ቢሆን በማገዝ ከጎኔ ሁኑ…..

About Post Author

Abby

Internet reporter, freelancer and webmaster.
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on April 11, 2015
  • By:
  • Last Modified: April 11, 2015 @ 11:43 am
  • Filed Under: Ethiopia

About the author

Internet reporter, freelancer and webmaster.

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar