www.maledatimes.com በእስር ቆይታዬ ወቅት ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ ርዕዮት አለሙ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በእስር ቆይታዬ ወቅት ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ ርዕዮት አለሙ

By   /   July 23, 2015  /   Comments Off on በእስር ቆይታዬ ወቅት ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ ርዕዮት አለሙ

    Print       Email
0 0
Read Time:57 Second

===================
የፕሬስ ነፃነትን በማፈንና የሰብአዊ መብትን በመርገጥ የሚታወቀው የኢህአዴግ መንግስት የፈፀመብኝን እስር በመቃወምና በማውገዝ
እንዲሁም ያለቅድመ ሁኔታ እፈታ ዘንድ በመጠየቅ ከጎኔ ለነበራችሁ በሙሉ ምስጋናዬን የማቀርበው በታላቅ ትህትናና አድናቆት ነው፡፡
በነዚያ የጨለማ ቀናት አብሮነታችሁ ያልተለየኝ አለምአቀፍና ሀገር አቀፍ የሚዲያ ተቋማት ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡

ዩኔስኮ፣ አለምአቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን፣ ሚዲያ ሌጋል ዲፈንስ ኢንሼቲቭ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂዩማን ራይትስዎች፣
ሲፒጄ፣ ፔን ኢንተርናሽናል፣ ዶሀ ፍሪደም ሴንተር፣ አርቲክል 19ንና ሌሎች ያልጠቀስኳችሁ በርካታ አለምአቀፍ ድርጅቶች ለጉዳዬ
የሰጣችሁት ትኩረት በኢትዮጵያ ያለውን አምባገነን ስርዓት በማጋለጥ በኩል ትልቁን ድርሻ ተጫውቷልና ከፍ ያለ ምስጋናዬን
አቀርብላችኋለሁ፡፡

መፈታቴን እንደራሳቸው ጉዳይ ቆጥረው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እንደ ማርቲን ሽቢዬ፣ፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም፣ አና ጎሜዝ፣ ናኒ ጃንሰን፣ ክርስቲያን አማንፑርና ሌሎች ዘርዝሬ መጨረስ የማልችላቸው በርካታ ግለሰቦች ለጉዳዩ የነበራቸውን ጠንካራ መሰጠት አብዝቼ አደንቃለሁ፡፡

ምንም እንኳን በአስከፋ ሁኔታ ተገልዬ የቆየሁባቸውና ጤናዬ ተቃውሶ የነበረባቸው መጥፎ ጊዜያትን ያሳለፍኩ ቢሆንም ከእስር የወጣሁት ግን ሁኔታዎቹ ሞራሌን ሳይሰብሩትና ይልቁንም ለዲሞክራሲ በተለይ ደግሞ ለፕሬስ ነፃነት መከበር የምችለውን ሁሉ ለማድረግ የበለጠ ቁርጠኝነት ኖሮኝ ነው፡፡

በመሆኑም ለዲሞክራሲ ስለታገሉና ሀሳባቸውን ስለገለፁ ብቻ በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ካለምንም ጥፋታቸው ታስረው የሚሰቃዩ በጣም
ብዙ አርበኞችና ጓዶች ከሀሳቤ አይለዩም ፡፡ ኢፍትሀዊነትን አምርራችሁ የምትጠሉ ኢትዮጵያዊያንም ሆናችሁ የሌላ ሀገራት ዜጎች ለነዚህ ሰዎች መፈታት ያላሳለሰ ጥረት ታደርጉ ዘንድ እጠይቃለሁ፡፡

በድጋሚ አመሰግናለሁ
ርዕዮት አለሙ

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on July 23, 2015
  • By:
  • Last Modified: July 23, 2015 @ 6:57 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar