www.maledatimes.com በነገራችን – ላይ የአለማችን ቁጥር አንድ ሃብታም ሚስት ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ወረደች !! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በነገራችን – ላይ የአለማችን ቁጥር አንድ ሃብታም ሚስት ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ወረደች !!

By   /   August 3, 2015  /   Comments Off on በነገራችን – ላይ የአለማችን ቁጥር አንድ ሃብታም ሚስት ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ወረደች !!

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 34 Second

Alex Abreham በነገራችን – ላይ
የአለማችን ቁጥር አንድ ሃብታም ሚስት ውሃ ልትቀዳ ወንዝ ወረደች !!
(አሌክስ አብርሃም)

ይህች ምስሉ ላይ ውሃ ባናቷ ተሸክማ የምትመለከቷት ሴት ….ማን ትመስላችኋለች … ግዴለም ማንነቷ ይቆያችሁ ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ …ባልዲዋን ለአፍታ አሳርፋ አንድ የስልክ ጥሪ ብታደርግ ሰማዩን በኤሊኮፕተር ምድሩን በዘመኑ መኪናዎች ማጥለቅለቅ የምትችል ሴት ናት !! እና ምንድነው እንዲህ የሚያኳትናት በሉኛ ….ወዲህ ነው ነገሩ ….

በአገራችን ነባራዊ ሁኔታ እንኳን የሃብታም ሚስት የሃብታም ቅምጦች አፈር አይንካን ሲሉ ማየት የተለመደ ነው ! ምን ሩቅ አስኬደን እዚች የፈረደባት ኮንዶሚኒየም ላይ እንኳን አንዳንድ የአዲስ አበባ ሃብታሞች ልብስና ቀለብ ችለው የሚያደልቧቸው ወዛዝርት ከተቻለ በግል መኪና (አቶዝና ያሪስ ውለው ይግቡ) እሱም ካልሆነ ወጣ ሲሉ ‹‹ ህዝብ ህዝብ ላለመሽተት ›› ካለላዳ ታክሲ እንዲች ብለው እግራቸውን አያነሱም !

ከወደማላዊ የሰማነው ዜና ደግሞ ይህን ብሶታችንን አስረስቶ ለካስ ይች አለም ቢያንስም ሰው አላት እንድንል አስገድዶናል … ቢልጌትስን ታውቁታላችሁ ….(ወዳችሁ ነው የምታውቁት … ሌላውን ተውትና ይሄን ያፈጠጣችሁበትን ኮምፒውተር ፕሮግራም ሰርቶ ያገናኘን ማን ሆነና) …. እና ይህ ሰው በአለም ላይ ከሃብቱ ቀጥሎ የሚታወቀው የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳት ነው … እንደውም በሚስቱና በራሱ ስም ባቋቋሙት ፋውንዴሽን /Bill & Melinda Gates Foundation / አፍሪካን በየአመቱ የአህያ ጆሮ የሚያካክል ዶላሩን እየመዘረጠ በቸርነት ሲረዳ ቆይቷል …(አፍሪካየ አንዳች ሰላቢ አለባት እንጅ የሱ እርዳታ ብቻ ሰው ባደረጋት ነበር )
እና የቢልጌትስ ባለቤት መሊንዳ ጌትስ /MELINDA Gates/ በዚሁ በጎ አድራጎት ድርጅታቸው በኩል ዶላር እየወረወሩ ረዳሁ ማለቱ ብቻውን አላረካ ቢላት …የአፍሪካዊያንን እናቶች ድካም እና ህመም በአካል ለመካፈል ወሰነች….ወስናም አልቀረች ወደማላዊ ሄዳ ይች ‹‹ሽ አሽከር ከፊቷ ሽ አሽከር ከኋላዋ የሚያረግድላት ›› እመቤት በአምሳ አመቷ የማላዊ እናቶች ጋር ሃያ ሊትር የሚይዝ የፕላስቲክ ባልዲዋን አንጠልጥላ በ50 ዓመቷ ወንዝ ወረደች …ለምን አትሉም …ውሃ ልተቀዳ!!

ፎቶው ላይ እንደምትመለከቱት ለሰአታት አብራቸው ተጉዛ ውሃ ቀድታ ተመለሰች …አለም ይህንን ድርጊት አይቶ ተደመመ !!የሚሊንዳም ፍላጎት ለአፍሪካዊያን እናቶች አለም ትኩረት ይስጥ ነው ጥያቄዋ ..ንፁህ ውሃ ያገኙ ዘንድ እንርዳቸው ነው ዘመቻዋ! እኔም ከዛዛዛዛዛ ላይ ወርዶ እንዲህ የሰዎችን ችግር ከነድካምና ህመሙ መካፈል ከተቻለ እዚች አፍንጫችን ስር ያሉትን ሚሊየን ችግረኞች በችግራችሁ አለን ብንል ምን ይለናል ስል አካፈልኳችሁ ! አይታፈር መቸስ የማላዊ መንግስት ባለቤቷም መጥቶ በጀሪካ ውሃ ቢቀዳ ለገፅታ ግንባታ ጥሩ ነበር ….ይሉ ይሆናል ውስኪ ፉት እያሉ !አፍሪካ ነዋ !!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on August 3, 2015
  • By:
  • Last Modified: August 3, 2015 @ 8:25 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar