www.maledatimes.com ለወያኔ ህልምና ቅዠቱ ይበቃዉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ለወያኔ ህልምና ቅዠቱ ይበቃዉ

By   /   September 15, 2015  /   Comments Off on ለወያኔ ህልምና ቅዠቱ ይበቃዉ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 33 Second

ወንድወሰን አደም (ከኖርዌይ)

የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ታሪክ ያልዉ ኩሩና ጨዋ፣ ባሕሉንና ወጉን የሚጠብቅ ሌላዉን ዜጋ አክባሪ፣ እንገዳ ተቀባይና አብሮ መኖርን የሚያዉቅ ተወዳጅ ሕዝብ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይህ ማራኪ፣ ያሸበረቀ ባህልና ወግ ያለዉ፣ የጀግንነት ታሪክን በየጊዜዉ በቆራጥነት ያስመዘገበ፤ አገሩንና ክብሩን ከአሸባሪዎችና ወራሪዎች የጠበቀ፤ ባሕሉንና ወጉን ክብሩን ያላስደፈረ ኩሩና ቆራጥ ሕዝብ ነዉ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለነፃነቱ እና ለሀገሩ ክብር ሲል የዉጭ  ወራሪዎችንና የአገር ዉስጥ አባገነኖችን በመቃወም የመረረ የነፃነት ትግል ሲያካሂድ የቆየ ከመሆኑም ባሻገር የነፃነት ትግሉንም በብዙ መንገድ ሲያካሂድ የኖረና በድል በማጠናቀቅ ያስመሠከረ ጀግና አገር ወዳድ ሕዝብ ነዉ፡፡

ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ይህን ጠንቃቃና ባለ ታሪክ ሕዝብ የታላቂቱን የሀገሩን ክብርና ባሕል የሚያጎድፍና የሚያረክስ መልኩን በመቀየር ዘረኝንት፣ ጠባብ የብሄርተኝነትን አሰተሳሰብ ያሰፈነና የሕዝቦችን የመተሳሰብ፣ የመግባባት፣ የእኩልነት እና የአንድነትን ስሜት የገደለ፣ ሕዝቦችን በቋንቋ፣ በዘር፣ በጎሣ፣ በሃይማኖት በመከፋፈልና በመሰነጣጠቅ፤ የከፋፍለህ ግዛን የእድሜ ማራዘሚያ ስልት ተጠቅሞ የሀገርን እድገትና የህዝቦችን ነፃነት የገፈፈና ሰብአዊ መብቶችን የነጠቀ አምባገነን የወያኔ መንግስት ተጭኖት አንዳለ ቢታወቅም ለምንም ለማንም ያልተንበረከከውና የማይንበረከክዉ ኩሩና ጀግና የሃገሬ ሕዝብ ዛሬም አልህ አስጨራሹን ትግል ከግብ ለማድረስ  በትጋት አየሰራ ይገኛል ፡፡

በተጨማሪም ድህነትን በህዝቦች ጫንቃ ላይ በመጫን፣ የህዝብን ሀብት በመዝረፍ  የራሱን ካድሬና ተከታዮችና  ያለልክ ያበለጸገዉ ወያኔ፣ ነፃነትን የገፈፈና ብዙዎችን አፍኖ የገደለ፣ የሕዝብን ድምጽ በማፈን መብት የነጠቀ አምባገነን ገዥ በመሆን፣ የሰዎችን ሞራልና ወኔ የሰለበ፣ በብዙ ርካሽ አስተሳሠቦችና ልምዶች የሰዎችን ትኩረትና ዝንባሌ አጣርሶ የመብት፣ የፍትህ እና የነፃነት ጥያቄ አንዳያነሳ በማድረግ አቅምንና ችሎታን እያዳከመ  የሚኮራበትን ታሪኩንና ባሕሉን እንዳያስታዉሰዉና እንዳያስበዉም እንደውም ጭራሽም እንደሌለዉ፤ ከኖረዉም የዘር ልዩነትና ጥላቻን አስረግዞ በመራራ መርዝ አገርን ለመግደልና ጨርሶ ለማጥፋት ብሎም ሥር መሠረት አልባ ለማድረግ የሚሰራ ታሪክ አጥፊ፣ ዘረኛና ሽፍታ የጥቂቶች ወንበዴዎች ስብስብ መሆኑ ከታወቀ የቆየ ቢሆንም ለነፃነቱ የማይደክም ሃያል ሕዝብ እንዳለ ግን ወያኔ ራሱ ያዉቀዋል፡፡

የአዲስ አስተሳሰብ ግኝት እንዳይባል እዉነታን ክዶና ታሪክን አጥፍቶ፣  ከባህልና ከእምነት ነጥሎ፥ ምንጭ የሌላትና ዝክረ ታሪክ አልባና የማትታወቅ አገር አድርጎ ለማስቀረት የጣረ ሲሆን፣ ረጅም ታሪክ ባለቤት፣ የታሪክ አሻራዋ የማይጠፋ፣ የተስፋም ቃል ያላትን አገር ባዶ ለማስቀረት ለረጅም ጊዜ ሲሠራ ቢቆይም ታሪክ የሚደግም እንደቀድሞው ለሃገርና ለህዝብ አንድነት የቆመ አርበኛ መዉጣቱ ግድ ነወ፡፡

እንዲህ ባለ ትዉልድ መሃል አመባገነኑ ወያኔ ወጣቱንና ሰላማዊውን ትዉልድ በዘርና በሃይማኖት በመከፋፈል፣ የብዙ ሱሶችና የስነ ልቦና ተጎጅ የሚያደርጉ የአጉል ባህል ማራገፊያ እንዲሆን በማድረግ አቅሙን፣ እዉቀቱንና ወኔዉን በመንጠቅ ደካማ አድርጎ በማስቀረት ራእይና ተስፋ የሌለዉ ህዝብ በማድረግ በማን አለብኝነት ህዝብን ያደኸየ፣ ያንገላታ፣ ብዙዎች ለአንድነት የቆሙ ምሁራንን የገደለ፣ ከሀገር ያፈናቀለ፣ በእስር እና በእንግልት በወኅኒ ያማቀቀ፣ ያሰቃየና የገደለ አምባገነን መሆኑ ይታወቃል፡፡

ነፃነት በትግል እንጂ በችሮታ አይመጣም፤ ሰላማዊ መንገድን ለማይቀበሉ እንደ ያኔ ላሉ አምባገነኖች የትጥቅ ትግል አስገዳጅ ምርጫ ነዉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ በኋላ እምቢ ለሀገሬ ለነፃነቴ፣ ለክብሬና ለታሪኬ የሚል፤ ለነገ የሀገር እድገትና ነፃነት የሚቆም፤ አገራዊ ስሜት ያለዉና በአዲስ ራዕይ ፍትህና ነፃነት የሠፈነባት፣ የሕዝቦች የበላይነት የሚረጋገጥባት፤ እኩልነትና አንድነት የሚንፀባረቅባት በአዲስ አስተሳሰብ ድሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን በነፃና ፍትሃዊ መልካም አስትዳድር ለመተካት የሚያስችል መርሃ ግብር በመክፈት ወቅታዊና አማራጭ በሆነዉ ትግል ሁሉም ሀገር ወዳድ ዜጋ የሀገር እድገትና ለዉጥ ግድ የሚለዉ ትዉልድ ለዚህ የትግል ሂደት የበኩሉን ድጋፍና እገዛ በማድረግ በዚህ ጎዳና ለተሰለፉ የኢትዮጵያ ጀግኖች ልጆች ጎን መቆም የግድ ይላል፡፡

በዚህም መሠረት በየትኛዉም የትግል መስመር ለተሠለፉ የነፃነት ታጋይ ህዝቦች አበረታችና  በግንባር ለነፃነት ትግል ለተሰለፉት ህዝባዊ ኃይላት ያለንን ማንኛዉንም  ድጋፉንና አጋረነት ከታላቅ አክብሮት ጋር በመግለፅ ከጎናቸዉ መቆማችንን ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡

ይህ አገርን የማዳን የትግል ተግባር በየትኛዉም የዓለም ክፍል የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን በተለመደዉና ቀጣይነት ባለው የትግል ሂደት በተጠናከረ ሁኔታ እንዲቀጥል ቀስቃሽ የሆነ ተግባር ሲሆን፤ በተጠናከረ  አንድነትና ትብብር አገርና ህዝብ ነፃ የሚወጣበት የትግል አሰገዳጅ ምርጫ በመሆኑ፤ ወያኔ ተንኮታኩቶ የሚወድቅብት ጊዜው አሁንና አሁን መሆኑን ያረጋግጣል፡፡

ሆኖም ይህ ጀግና ህዝብ ከአብራኩ በወጡ ገዥዎች ነፃነቱ ተገፎ፣ መብቶቹ ተረግጠው የመከራ ኑሮ እየገፋ አያሌ ዘመናት ኖሯል፡፡ ይህ የመከራና የሰቆቃ ኑሮ ዛሬም አላበቃም፣ እንዲያውም “ከጭቆና ነፃ አወጣንህ” እያሉ የሚሳለቁበት ግፈኛ ገዥዎች የጫኑበትን የስቃይ ቀንበር ተሸክሞ የውርደት ኑሮ እየኖረ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ የአገር ውስጥ ገዥ መደቦች የጫኑበትን የስቃይና የመከራ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል፣ ፍትህ፣ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት ኑሮ ለመኖር ዓመታት የፈጀ ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለበት ትግል አድርጓል፡፡ እስካሁን ትግሉን በአሸናፊነት ተወጥቶ የናፈቀውን ፍትህ፣ ሰላምና ብልፅግና ማግኘት አልቻለም፡፡

ለዚህ በርካታ ምክንያቶች ያሉት ቢሆንም ዋናው ምክንያት ህዝባዊ ትግሉን በተባበረና በተቀናጀ መልክ መስራት አለመቻሉ ነው፡፡ ይህ ስር የሰደደ ያለመተባበር ችግር ወያኔ ዘመን ተባብሷል፡፡ ወያኔ ሆን ብሎ የፈጠረው የመለያየት እና የከፋፍለህ ግዛው ፖሊሲ ለጋራ ድል አብሮ መታገልን በጭራሽ አስቸጋሪ ጉዳይ አድርጎት ቆይቷል፡፡ ዛሬ ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ በጋራ አብሮ በመታገል የሚገኘው ዘርፈ ብዙ ጥቅም የገባቸውና ካለፈው ተደጋጋሚ የታሪክ ስህተት የተማሩ፣ በአገራችን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመሰረት በምድር ላይ በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ አራት ድርጅቶች ሰሞኑን በጥምረት ተሳስረው በጋራ ለመታገል ወስነዋል፡፡ እነዚህ አራቱ ድርጅቶች ለብዙ አመታት የአብሮ መታገል ፍላጎት እንቅፋት የሆነውን የገዢ መደቦች የከፋፍለህ ግዛው ሴራ በጣጥሰዋል፡፡ ይህ ዛሬ በጥምረት የተጀመረው ትብብር እያደገ ሄዶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ውህደት እንዲያድግ ይደረጋል፡፡አንድነት ኃይል ነዉ::

Capture

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 9 years ago on September 15, 2015
  • By:
  • Last Modified: September 15, 2015 @ 12:17 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar