www.maledatimes.com ከፍትህና ከዲሞክራሲ እየተጣሉ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መቆም አይቻልም! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ከፍትህና ከዲሞክራሲ እየተጣሉ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መቆም አይቻልም!

By   /   June 23, 2016  /   Comments Off on ከፍትህና ከዲሞክራሲ እየተጣሉ ለፍትሕና ለዲሞክራሲ መቆም አይቻልም!

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 12 Second

ግራ የገባው ግንቦት 7

ያሬድ ኃይለማርያም

ሰኔ 2008 ዓ.ም

ለትግላችን ብቸኛውን ሚና የሚጫወተውን የኤርትራ ሕዝብና መንግስትን ለማዳከም የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርገውን ሴራ ለመቃወም ይህንን ፒትሽን ፈርሙ” – ነአምን ዘለቀ (አ. ግንቦት 7)

“particular individuals, including officials at the highest levels of State, the ruling party – the People’s Front for Democracy and Justice – and commanding officers bear responsibility for crimes against humanity and other gross human rights violations.” UN UN Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea

 

ሰሞኑን በማህበረ-ድረገጾች ላይ ግንቦት 7 በአመራሩ አቶ ነአምን ዘለቀ በኩል ያቀረበውን የኤርትራን መንግስት ደግፉልን የሚል ጥሪ የያዘ አንድ የቪዲዮ ምስል ተመልክቼ ነበር፡፡ ላላያችሁት ቪዲዮው ይህንን ቢጫኑ ያገኙታል፡-  https://www.facebook.com/search/top/?q=petition%20for%20eritrea&em=1 ወይም

ዘ-ሃበሻ በተሰኘው የዜና ምንጭ የፌስ ቡክ ገጽ ላይ ያገኙታል፡- https://www.facebook.com/Zehabesha/videos/1100393513366187/

የድርጅታቸው ጥሪ ባጭሩ ጥላና ከለላ የሆነንን የኤርትራን መንግሥት የአለም አቀፉ ማህበረሰቡ በክፉ አይን እያየብን ነውና  የኢሳያስን መንግስት በክፉ አይን ያየውን የተባበሩት መንግስታት በማውገዝ ለኢሳያስ ያለንን የወዳጅነት ድጋፍ ለማሳየት ከዚህ የሚከተለውን ፊርማ በመፈረም አጋርነታችሁን ግለጹ የሚል ነው፡፡ የፊርማ ማሰባሰቢያው መልዕክትም ይህን ይመስላል፡- https://hagger.wufoo.eu/forms/i-reject-the-coie-and-sr-report/

I Reject the COIE and SR Report

  • I the undersigned, categorically and unequivocally reject the politically motivated report of the Report of the Commission of Inquiry on Human Rights in Eritrea (COIE) and the Special Rapporteur (SR) on the Human Rights Situation in Eritrea.

    The resolution and the appointment of the SR and establishment of the COIE are in fact a continuation of an orchestrated 16-year long political campaign that seeks to demonize and delegitimize Eritrea in the international arena, and erode the final and binding Eritrea Ethiopia Boundary Commissions delimitation and demarcation decisions.

ወደ ግል አስተያዬቴ ከመግባቴ በፊት ይህ የኤርትራን መንግስት ሰላም የነሳውና ስጋት ውስጥ የጣለው፤ እንዲሁም የግንቦት 7 አመራሮች አይናቸውን በጨው አጥበው ያለ አንዳች ሃፍረት በአደባባይ የተቃውሞ ጥሪ ያቀረቡበትን ሪፖርት ይዘት ላላያችው ሰዎች ነገሩን ለማመዛዘን ያመቻችሁ ዘንድ ይህን ቪዲና የተባበሩት መንግስታትን መግለጫ ከዚህ የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች በመጨቆን ልትመለከቱዋቸው ትችላላችዉ፡፡

https://vimeo.com/169860877

http://www.ohchr.org/EN/NewsEvents/Pages/DisplayNews.aspx?NewsID=20067&LangID=E

 

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ቢሮ ትላንት ባወጣው በዚህ ሪፖርት አንባገነኑ የኤርትራ መሪ አቶ ኢሳያስ በዜጎቻቸው ላይ የሰውን ስብእናን የሚጻረር ከፍተኛ ወንጀል መፈጸማቸውን ያረጋገጠ መሆኑን እና ለዚህም ወንጀላቸው ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጽዋል፡፡ እንዲህም ሲል በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የከፋ ሁኔታ ገልፆጻል፡-

“There is no genuine prospect of the Eritrean judicial system holding perpetrators to account in a fair and transparent manner. The perpetrators of these crimes must face justice and the victims’ voices must be heard. The international community should now take steps, including using the International Criminal Court, national courts and other available mechanisms to ensure there is accountability for the atrocities being committed in Eritrea,” – See more at: http://www.ohchr.org/EN/NewsEvents/Pages/DisplayNews.aspx?NewsID=20067&LangID=E#sthash.xO8q0CsB.dpuf

አንባገነኑ ኢሳያሳ አፎረቄ አመራር በዙ ሺ ዎች ተገድለዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኤርትራዊያንን ከአገር ተሰድደዋላ፤ በሪፖርቱ ላይ እንደተገለጸው በ2015 ብቻ ከ42 ሺ በላይ ኤርትራዊያን ከአገር ተሰደዋል፣ እጅግ በርካቶች ታፍነው የደረሰቡበት አይታወቅም፤ ይህም ጋዜጠኞችን እና ምሁራንን ያካትታል፡፡

ከዚህ አይነቱ አውሬ አንባገነናዊ ሥርዓት ጋር ግንባር ፈጥሮ ሥልታዊ የሆነ የመታገያ መንገድ ማመቻቸት አልበቃ ብሎ ይህ ወንጀለኛ ሥርዓት እንዳይወገድ በፊርማችሁ ድጋፍ አድርጉለት ብሎ አይን ባወጣ መልኩ በአደባባይ ጥሪ ማድረግ የግንቦት 7 አመራሮችን ከግራ መጋባት ያለፈ ክሽፈት ከማሳየት ባለፈ እንታገልለታለን ከሚሉት የፍትህና የዴሞክራሲያዊ መርህ በምን ያህል ጥልቀት በተቃርኖ መቆማቸውንም ነው የሚያመላክተው፡፡

በአዲስ አበባ የከተመውን እና ለ25 አመታት የኢትዮጵያን ሕዝብ ሲያስለቅስ፣ ሲገድል፣ ሲያፍን፣ ሲያስርና ለስደት ሲዳርግ የኖረውን የወያኔን ክፉና አፋኝ ሥርዓት ሊዋጋ አደባባይ የወጣና ጫካ የገባ ኃይል፣ ወያኔ ማቅ ያለበሰውን እና መቀመቅ የከተተውን የፍትህ፣ የዴሞክራሲና የሕግ ልዕልና ጭላንጭል በትግላችን ከወደቀበት ቅርቃር አውጥተን ኢትዮጵያን የሰላም፣ የልማትና የዜጎች ነጻነት ሙሉ በሙሉ የተረጋገጠባት አገር እናደርጋለን ብለው ሌት ተቀን የሚምሉና የሚገዘቱ የግንቦት 7 አመራሮች ምን ግራ ቢገባቸው ነው በአደባባይ አለም በሰው ዘር ላይ የከፋ ወንጀል በመፈጸም ተጠታቂ ያደረገውን የኤርትራን መንግስት ለመታደግ ባደባባይ ድጋፍ የሚያሰባስቡት፡፡

ለሻቢያ እድሜ እየለመኑ የወያኔን እድሜ ያሳጥርንልን ማለት ለእኔ ግራ ከመጋባት ያለፈ ትርጉም የለውም፡፡ ሁለትም ከአንድ ምንጭ የተቀዱ፣ በአንድ መስክ ያደጉ፣ በአንድ አይነት መርዝ የናወዙ፣ በተመሳሳይ የጥፋት ተልኮ ውስጥ ሆነው ኢትዮጵያንና የዛሬዋን ኤርትራን ተባብረው መቀመቅ የከተቱና ሕዝቦቹንም ያዋረዱ እኩይ ስርዓቶች ናቸው፡፡ እንደ ግንቦት 7 ላለ ድርጅት መመሸጊያ በማጣት ኤርትራ በርሃዎች ውስጥ መከተሙና ወያኔን ለማስወገድ ከኢሳያስ ጋር ማደሙ አማራጭ ላይኖረው ይችላል፡፡ ከዚያ ባለፈ ኢሳያስን ታላቅና ተወዳጅ መሪ በማስመሰልና ሌላው አለም፤ የተባበሩት መንግስታትና አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች በኢሳያስ ላይ የሚያሰሙትን እሮሮና ውንጀላ ለመከላከል እሱን በማውገዝ ለኢሳያስ ጥብቅና መቆም በታሪክ ተጠያቂ ያደርጋል፤ በነገው የሁለቱ አገሮችና ሕዝቦች ግንኙነትም ላይ መጥፎ ጠባሳን ይተዋል፡፡ ከዚያም ባለፈ ይህ አይነቱ ድርጊት ኢሳያስን ከመደገፍ ባለፈ በኤርትራ በየማጎሪያ ቤቱ ታስረው ስቃይ በሚፈጸምባቸው ግፉአን ላይ ማላገጥ ነው የሚሆነው፡፡ ለብዙ ሚሊዮን ኤርትራዊያን ሲዖል የሆነችው አገራቸው ለእኛ መሸሸጊያ ሆናናለች በሚል እርካሽ ስሌት የኢሳያስን እድሜ ያርዝምልን፣ ሻቢያንም በመንበሩ ያቆይልን የሚለው ጸሎት በምድርም በሰማዩም ሰሚ ባይኖረውም ያስተዛዝባል፡፡ ከግፉአን ጎን አብረን መቆም ቢያቅተን እንኳ በበደላቸው ላይ ሌላ በደል እንዲፈጸም በሃሊዮም ይሁን በግብር ከግፍ ፈጻሚዎቹ ጎን እንዳንቆም የሚያደርገን ትንሽም የሞራን እንጥፍጣፊ ካለች ትበቃናለች፡፡ የግንቦት 7ቱ አቶ ነአምን ዘለቀ ጥሪ ግን በ1997ቱ የኢትዮጵያ ምርጫ የፓርቲዎች ክርክር ወቅት “ማፈር ድሮ ቀረ” የምትለዋን የፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ንግግር አስታወሰኝ፡፡

አገርን የማዳኑ ትግል እየተስተዋለ ቢሆን ይበጃል!

ያሬድ ኃይለማርያም

ከብራስልስ፣ ቤልጂየም

 

 

 

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on June 23, 2016
  • By:
  • Last Modified: June 23, 2016 @ 9:22 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar