www.maledatimes.com ጋዜጠኛ አበራ ዋጊ በድንገተኛ አደጋ ህይወቱ አለፈ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ጋዜጠኛ አበራ ዋጊ በድንገተኛ አደጋ ህይወቱ አለፈ

By   /   September 18, 2016  /   Comments Off on ጋዜጠኛ አበራ ዋጊ በድንገተኛ አደጋ ህይወቱ አለፈ

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 35 Second

በሳንዲያጎ ከተማ ነዋሪ የነበረው እና በቀድሞው ማእበል ጋዜጣ አዘጋጅ የነበረው ፣እንዲሁም በምንሊክ ሳተናው እና አስኳል ጋዜጦች ላይ በከፍተኛ አርቶት የሚታወቀው ጋዜጠና አበራ በትላንትናው እለት በደረሰበት የመኪና አደጋ በሳንዲያጎ ከተማ ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ፣በዛሬው እለት በሳንዲያጎ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ አባላቶች እና እንዲሁም የኢትዮጵያውያን እድር ተወካዮች በስደት ከሚገኙት የኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ጋር በጉዳዩ ምክክር ያደረጉ ሲሆን ፣ የሳንዲያጎ ህዝብ ተወካዮች ስለ ጋዜጠኛው ያላቸውን መልካም ክብር እና ስለ ስብእናውም ሆነ በማህበረሰባቸው ዘንድ ስላደረገው መልካም ነገር ሲመሰክሩ ቆይተዋል ፣ከዚያም አልፎ አቶ አበራ ለሳንዲያጎ ህዝብ እንደ ቤተሰብ አባል በእያንዳንዱ ህዝብ ጥልቅ ሃዘንን የፈጠረ ሲሆን ፣እንደማንኛውም የቤተሰብ አካል ከእጃችን ድንገት የጠፋብን አንጡራ ሃብታችን ነበር ሲሉ ተናግረዋ።

አቶ አበራ በጣም በስራው ታታሪ የነበረ ስሆን በብዙ ስራዎቹ ከመታወቁም በላይ በተለይም በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት የመጀመሪያውን የጦርነት ዘገባ በነጻ መገናኛ ብዙሃኑ ሲያቀርብ ከፍተኛ ስቃይ እና እንግልት ከመድረሱም በላይ ከሃገር ተሰዶ እንዲወጣ የተደረገበትም ዋነኛ ምክንያቱ መሆኑን ከታሪኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአሁን ሰአት ላይ አቶ አበራ አስከሬን በሆስፒታል በምርመራ ላይ የሚገኝ ሲሆን በፖሊስም የምርመራው ስራ ተጠናቆ ለወዳጅ ዘመዶቹ አስከሬኑ ሊሰጥ እንደሚችል ከሳንዲያጎ ማህበረሰብ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ነጻ ጋዜጠኞች ማህበርም በጋዜጠኛ አበራ ዋጊ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ሲገልጽ ፣በጠቅላላ ማህበሩ ስም የወጣውን መግለጫ ከስር አያይዘንላችኋል ሊንኩን ይጫኑት

abera-wegi

 በጋዜጠኛ አበራ ወጊ ህልፈት አዝነናል መልካም ስሙ ግን ከመቃብር በላይ ይኖራል!
 
በሳዲያጎ ከተማ ነዋሪ የነበረው እና ለረዥም ግዜ በነጻ ፕሬስ ጋዜጠኝነት ያገለገለው፤ ጋዜጠኛ አበራ ወጊበድንገተኛ የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት መለየቱን የሰማነው፤ በጥልቅ የሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነን ነው።ጋዜጠኛ አበራ ወጊ ዛሬ በእስር ከሚገኘው ከጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ጋር አብሮ ሰርቷል። በተለይም ማዕበልበተሰኘው ጋዜጣ ላይ ዋና አዘጋጅ በመሆን ለብዙ አመታት አገልግሏል።
 
አቶ አበራ ወጊ የማዕበል ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በነበረበት ወቅት፤ በበሳል ብዕሩ ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳዮችላይ ትኩረት ሰጥቶ ጽፏል። በተለይም በዚሁ የማዕበል ጋዜጣ የፊት ገጽ ላይ፤ኢትዮጵያዊነት የቃል ኪዳንማተማችን ነውየሚለውን መሪ ቃል ያመነጨው፤ አቶ አበራ ወጊ ነበር።ከዚሁ የጋዜጠኝነት ስራው ጋር በተያያዘ፤የታሰረበት እና ለብዙ ስቃይ የተዳረገበት የክስ መዝገብ፤ አነጋጋሪ እና አስገራሚ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን፤ በህግ ስም የተስራውን ግፍ ስለሚያሳይ፤ በዚህ አጋጣሚ ለመጥቀስ እንወዳለን።  

ወቅቱ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጦርነት ውስጥ ውስጡን እየተካሄደ የነበረበት ግዜ ነው። እናም ጋዜጠኛአበራ በድንበር አካባቢ ይደረግ የነበረውን የተኩስ ልውውጥ በዜና መልክ አቀረበ። ዜናውን ተከትሎበወቅቱየትግራይ ፕሬዘዳንት የነበሩት አቶ ገብሩ አስራት፤በትግራይና ኤርትራ ድንበር፤ እንኳንስ ጦርነት ተነስቶ ክባድ የተኩስ ድምፅ ሊሰማ ቀርቶ፤ የባረቀም ጥይት የለም።ሲሉ፤ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ ደግሞ፤በኤርትራእና ኢትዮጵያ ድንበር፤ እንኳንስ ጥይት ጅራፍም አልጮኸም።በማለት ፓርላማውን ፈገግ አደረጉት።ተከታዮቻቸውም የጦርነት ሰበር ዜና አቅራቢውን፤ ጋዜጠኛ አበራ ወጊንህዝብን ከህዝብ ጋር ለማጣላት፤ የሃሰትዜና አቀረብክብለው አሰሩት።
 
ጋዜጠኛ አበራ ወጊ፤ በዚህ ዜና ምክንያት እስር ቤት እያለ፤ ውስጥ ውስጡን ሲደረግ የነበረው ጦርነትተጋግሎ ሊደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደረሰ። እንደ ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ግንቦት 4 ቀን፤ 1990 ..በፓርላማ ደረጃ ጦርነቱ ታወጀ። ምንም እንኳን ጦርነቱ ገሃድ ቢወጣም ለአቶ አበራ ወጊ ግን ምህረትአልተደረገለትም፤ ወይምለካስ ያቀረብከው ዜና እውነት ነበር።ተብሎ ይቅርታ አልተጠየቀም። ጦርነቱ ተፋፍሞእያለ የጠቅላይ ሚንስትሩ መግለጫ እንደ መረጃ ቀርቦም ጭምር፤ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ 2 ችሎትዳኛ ሃጎስ ወልዱ፤ በአቶ አበራ ላይ የአንድ አመት ተኩል እስራት ፈረደበት።
 
አቶ አበራ ወጊ ከላይ በተጠቀሰውየኢትዮጵያ ኤርትራ ጦርነትለአንድ አመት ከስድስት ወር ከታሰረበኋላ ሲፈታ፤በሌላ ክስ ይፈለጋልብለው፤ ከእስር ቤቱ ውጪ የማዕከላዊ ምርመራ ፖሊሶች እየጠበቁት ነበር።ነዚህ ፖሊሶች በማምለጡ ምክንያት፤ ደህንነቶች ጭምር ጋዜጠኛ አበራ ወጊን ማደን የጀመሩበት አጋጣሚተፈጠረ። በዚህ መሃል ነው የሚወዳት አገሩን፤ ኢትዮጵያን ለቅቆ ለመሰደድ የበቃው።
 
ጋዜጠኛ አበራ በሳንዲያጎ ከተማ ነዋሪ በነበረበት ወቅት፤ በሃዘን እና በደስታ ከሌሎች ኢትዮጵያውያንአልተለየም። ከኢትዮጵያ ወጥተው በስደት  ላይ የነበሩ ጋዜጠኞችን ለመርዳት ይደረግ በነበረው እንቅስቃሴ፤ግንባር ቀደም ተባባሪ፤ ለተቸገሩ ደራሽ እና አጽናኝ ወንድማችን ነበር። ከጋዜጠኝነቱ በተጨማሪ ለኢትዮጵያአንድነት ለቆሙ የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች፤ ልባዊ ድጋፍ በመስጠት ይታወቃል።
 
በመጨረሻም በህይወት በነበረበት ወቅት በቁጭት ከሚናገራቸው ነገሮች እስር ቤት ውስጥ እያለአስፈላጊ ህክምና ባለማግኘቱ ለተባባሰ የስኳር ህመም መዳረጉን ሁሌም በቁጭት ከሚያነሳቸው ጉዳዮች ውስጥአንዱ ነው። በኋላ ላይ ህመሙ እየባሰበት ሲመጣ፤ ወደ ሆስፒታል ከወሰዱት በኋላ፤ ያልተገባ በሽታ በመርፌእንደተሰጠው፤ ይህንንም ከእስር ቤት ከወጣ በኋላ በህክምና  ማወቁን በቁጭት ይገልጽልን ነበር።
የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዘዳንት የነበሩት፤ አቶ ክፍሌ ሙላት ተጨማሪምስርነታቸውን ሲሰጡ፤በአቶ አበራ ወጊ ላይ የተደረገበትን በደል ይህ ብቻ አይደለም። ከእስር ቤት ከወጣ በኋላየነገረኝ አንድ ጉዳይ አለ።አንድ ቀን ለኢትዮጵያ ህዝብ ምስክርነትህን ትሰጥልኛለህ።በማለት፤ በእስር ላይ ሳለ ዘርእንዳያፈራ ለማድረግ አሰቃቂ ድብደባ ያደረጉበት መሆኑን ገልጾልኛል።በማለት ምስክርነቱን ሰጥቷል።በማያያዝም፤ሃሳብን በነጻነት በመግለጻቸው፤ ብዙ ግፍ ከተሰራባቸው የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች መካከል አንዱነበር።በማለት አቶ ክፍሌ ሙላት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።
 
ሌሎች በስደት ላይ የሚገኙ የቀድሞ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች፤ አቶ አበራ ወጊ በኢትዮጵያ ነጻፕሬስ ታሪክ ውስጥ ያበረከተውን መስዋዕትነት በማክበር፤ስምህ ከመቃብር በላይ ይኖራልለማለት፤ ይህንወቅታዊ መግለጫ አውጥተናል። ለወዳጅ እና ዘመዶቹ አምላክ መጽናናትን ይሰጥልን ዘንድ እንማጸናለን።
 
በህይወት በነበረበት ወቅት ራሱ ጋዜጠኛ አበራ  እንዳለው… “ኢትዮጵያዊነት የቃል ኪዳን ማተማችንነው”!
 
በስደት የሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች።
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on September 18, 2016
  • By:
  • Last Modified: September 18, 2016 @ 12:20 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar