www.maledatimes.com የቅንጅት እና ለአንድነት መስራች የነበሩት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል አረፉ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቅንጅት እና ለአንድነት መስራች የነበሩት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል አረፉ

By   /   October 6, 2016  /   Comments Off on የቅንጅት እና ለአንድነት መስራች የነበሩት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል አረፉ

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 45 Second
Hailu Shaul

Hailu Shaul

የመኢአድ ዋና ሃላፊ የቅንጅት ለአንድነት መስራች የነበሩት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል አረፉ። ለረጅም ዘመን በፖለቲካዊ ትግል እንቅስቃሴ እና በአመራር ደረጃ የሚታወቁት እንዲሁም በስፋት በምርጫ 97 አመተ ምህረት በተደረገው ሃገራዊ ምርጫ ላይ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድን)በመወከል ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመሆን የትግራይ  መንግስት የሆነውን ህወሃትን በዝረራ በመጣል አሸናፊ ሆነው የነበረ ሲሆን  በህገ መንግስቱ መሰረት የሚከበርላቸውን ያለ መከሰስ መብት በመለስ ዜናዊ ስልጣን እንዲነሳ መደረጉን እና ወደ እስርቤት መወርወራቸው የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው ። ጉዳያቸውም በ8ኛው ወንጀል ችሎት ሲታይ መቆየቱን አይዘነጋም ፣

ይህ በእንዲህ እንዳለ የህወህት መንግስት ግን በፈጠረው የውሸት ክስ  ህዝቦችን ለአመጽ በማነሳሳት (በዘር ማጥፋት እና በሃገር ክህደት ወንጀል ተከሰው ለ17 ወራት በቃሊቲ እስርቤት ከቆዩ በኋላ በመጨረሻም ፣በዳኛ አድል መሃመድ በኩል አንድ ጊዜ የሞት ፍርድ ቀጥሎም የእድሜ ልክ እስራት እያለ ፍርድ በማዛባት ሲያንገላታ ቆይቶ በስተ መጨረሻም በሃገር ሽማግሌዎች ድርድር ምክንያት ይቅርታ ጠይቀዋል በማለት  ከሌሎች 38 የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች  እና ከ40 በላይ ጋዜጠኞች ጋር በጋራ በመሆን መፈታታቸውን ይታወቃል ። ከእነዚህም ታሳሪዎች መከከል አቶ በፍቃዱ ደግፌ (ኢኮኖሞስት) ዶክተር ብርሃኑ ነጋ (ኢኮኖሚስት) ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው ኬሚካል ኢንጂነር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ጂኦግራፊ አቶ ሙሉነህ ኢዩኤል ኢኮኖሚስት በጥቂቱ የሚገኙበት ሲሆን ፣ከጋዜጠኞች በአሁን ሰአት በእስር ቤት ውስጥ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ፣በኢሳት ላይ በስራዎቻቸው  አድናቆትን የተቸሩት እና የቀድሞው የኢትዮጵ ጋዜጣና መጽሄት አሳታሚ ሲሳይ አጌና ፣ፋሲል የኔአለም፣ ደረጀ ሃብተ ወልድ በእስር ቤት ውስጥ አብረው ቆይታን ማድረጋቸው የሚታወስ ነው

በ1936 እንደ አውሮጳውያን  አመተ ምህረት በሰሜን ሸዋ  የተወለዱት እና በስራቸው ኢንጂንየር የነበሩት አቶ ሃይሉ ሻውል  የቅንጅት ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን ከዚያ በፊትም በመላው አማራ ድርጅት የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን ቦታ ተክተው ለአማራው ህዝብ ሲታገሉ የቆዩ አንጡራ የኢትዮጵያ ህዝብ ልጅ ናቸው ። ሆኖም የመላው አማራ ድርጅት ለሁለት ከተከፈለ በሁዋላ እርሳቸው የእራስቸውን የፖለቲካ ድርጅት ለማቋቋም በመወሰናቸው እና የቀድሞውን የመላው አማራ ድርጅት ሃብት የነበረውን መኢአድን በወያኔ በኩል እንዲከፋፈል በመደረጉ የስልጣን ገደባቸውም ሊወሰን በመቻሉ እና ይትግል ሃይላቸው እንዲቀንስ በማድረጉ ወያኔ ያደረገውን ሴራ ሁል ጊዜም ሲያወግዙ እንደነበር የማለዳ ታይምስ አዘጋጅ ይገልጻል።

የወያኔ መንግስት ይህንን የፖለቲካ ክፍፍል ያደረገበት ነበረረበት ዋነኛ አላማ በ1997 አመተምህረት የነበረውን ምርጫ ለማሸነፍ ይረዳው ዘንድ የተለያዩ የእራሱን የድርጅት አባሎች በመኢአድ ስር እንደ አባልነት እንዲሰገሰጉ በማድረግ የተለያዩ የአላማ ልዩነቶችን እንዲያንጸባርቁ አድርጉ የሃሳብ ልዩነታቸውን ይዘው እንዲገነጠሉ በ1996 አመተ ምህረት መደረጉ ይታወሳል።

ከዚያም በሁላዋ በ1997 አመተ ምህረት ከ5በላይ የሚሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች በመሰባሰብ ቅንጅትን የፈጠሩ ሲሆን በግንቦት 7 በተከናወነው ሃገራዊ ምርጫ የወያኔ መንግስት በጠቅላላ ሃገሪቱ ሽንፈትን ቢከናነብም ሽንፈቱን ባለመቀበሉ ምክንያት ፣ህብረተሰቡ በሃገሪቱ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣቱ አስመልክቶ እናም የህዝቡ ወደ ፓርላማ ግቡ አትግቡ ክርክ እንደዚሁም የወያኔ የማስፈርሪያ ዛቻ ቢጫ እና ቀይ መስመር አልፋችኋል የሚሉትንም ሆነ ሌሎችን ጉዳዮች ተከትሎ ፣ ህዝቡ በራሱ መነሳሳት ወደ ጎዳና በመውጣት መጹን ያነሳሳው ሲሆን እንደ እነ ሽብሬ ደሳለኝን እና ሌሎች ከ250 በላይ ዜጎችን ህይወት በአዲስ አበባ  የወያኔ መንግስት የቀጠፈ ሲሆን የ4 የመከላከያ ፖሊሶችም ህይወት ጠፍቶአል።

በዚህም ወቅት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ለ17 ወራት በእስር በቆዩበት ወቅት የምግብ አድማ ለረጅም ቀናት ያደረጉ ሲሆን በዚህም ወቅት ለዲያቤቲክ በሽታ በዳረጋቸውን እና አይናቸውን በወቅቱ ለማየት ከልክሎአቸው እንደነበር የማለዳ ታይምስ አዘጋጅ የዘላለም ገብሬ ዘገባ ያመለክታል።

በ2007 አመተ ምህርት የይቅርታ ደብዳቤ በእነ ሃይሌ ገብራስላሴ በኩል (የሃገር ሽማግሌ ) ልከው መንግስት ይቅርታ አድርገዋል እስከተባለበት ወቅት ምንም አይነት የህክምና አገልግሎት ያልተሰጣቸው ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል በ2008 አመተምህረት ከእስር ከተፈቱ በሁዋላ ይሄው በሽታቸው ወደ አደገኛ ሁኔታ ላይ መድረሱን ከህክምና ባለሙያዎች የተገለጸላቸው መሆኑን ያትታል ፣የቀድሞዋ የህግ ባለሙያም ብርቱቃን ሚደቅሳ በወቅቱ በእስር አብራቸው የነበረች ሲሆን የይቅርታ ደብዳቤው ዕራሱ በመንግስት እና በእነ ሃሌ የተንኮል ስራ ተመቻችቶ የወያኔን የፖለቲካ ስርትራቴጂ ሊጠቅም በሚችል መልኩ እንዳቀናበሩት ለመገናኛ ብዙሃኖች መግለጿ ይታወቃል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ አቶ ሃይሉ ሻውል ከማንኛውም የፖለቲካ እንቅስቃሴ እራሳቸውን በጤናቸው ጉድለት አርቀውም እንደነበር ማለዳ ታይምስ አትቷል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 8 years ago on October 6, 2016
  • By:
  • Last Modified: October 6, 2016 @ 6:43 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar