www.maledatimes.com የወያኔ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ይፋ አደረገ። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የወያኔ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ይፋ አደረገ።

By   /   October 16, 2016  /   Comments Off on የወያኔ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ይፋ አደረገ።

    Print       Email
0 0
Read Time:4 Minute, 36 Second

በማንኛውን የሀገሪተሩ ክፍል የተከለከሉ ተግባራት
==========================

ማንኛውን ሁከት እና ብጥብጥና በህዝቦች መካከል መጠራጠር እና መቃቃር የሚፈጥር ይፋዊም ሆነ ድብቅ ቅስቀሳ በማናቸውም መልኩ እና ዘዴ ማድረግ፤ ፅሁፍ ማዘጋጀት ማተምና ማሰራጨት፣ ትእይንት ማሳየት፣ በምልክት መግለፅ ወይም መልእክትን በማናቸውም ሌላ መንገድ ለህዝብበ ይፋ ማድረግ ፈቃድ ሳይኖር በማንኛውም ህትመት ወደ ሀገር ወስጥ ማስገባት ወይም ወደ ውጪ ሀገር መላክ በመመሪያው ተከልክሏል።

መልእክት በኢንተርኔት፣ በሞባይል በጽሁፍ፣ በቴሌቭዠን፣ በሬድዮ፣ በማህበራዊ ሚድያ ወይም በሌሎች የግንኙነት ዘዴዎች መለዋወጥም በመመሪያው ተከለከለ ተግባር ነው።14666121_10154667052469923_5950289807064951447_n

ከሽብርተኛ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ማድርግ
=======================
በሽብርተኝነት ከተሰየሙ ድርጅቶች እና ከፀረ ሰላም ሃይሎች ቡድኖች ጋር ማንኛውንም ግንኙነት ማድረግ፤ የአሸባሪ ድርጅቶች የተለያዩ ፅሁፎችን ማሰራጨት፣ አርማቸውን መያዝ ወይም ማስተዋወቅ፣ የቴሌቭዥን ወይም የሬድዮ ፕሮግራሞችን መከታተል፣ የኢሳት፣ ኦ ኤም ኤን እና የመሳሰሉትን የሽብርተኛ ድርጅቶች ሚድያዎች ማሳየት፣ መከታተል እና ሪፖርት ማድረግ የተከለከለ ነው።

ያልተፈቀደ ሰልፍ እና የአደባባይ ስብስባ
=======================
የህዝብና የዜጎች ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ከኮማንድ ፖስቱ ፈቃድ ውጪ ማንኛቸውንም ሰልፍ እና የአደባበይ ስብስባ ማድረግ ከተከለከሉ ተግባራት ውስጥ አንዱ ነው።

ለህዝብ አገልግሎት አለመስጠት
=================
በመመሪያው እንደ ተደነገገው ህዝብ የሚጠቀምባቸውን ወይም ፈቃድ የወጣባቸው የንግድ ስራዎች፣ ሱቆች፣ ወይም የመንግስት ተቋማት መዝጋት ወይም ምርት እና አገልግልት ማቋረጥ፣ ከስራ ቦታ ያለበቂ ምክንያት መጥፋት ወይም ስራ ማቆም፣ ተገቢውን አገልግሎት አለመስጠት እና ስራ መበደል ክልክል ነው።

የመንግስት ወይም የግል ተቋማት ሰራተኞች ወደ መደበኛ ስራቸው እንዳይገቡ መዛት እና ማስፈራራትም ተከልክሏል።

በትምህርት ተቋማት አድማ ማድረግ ከተከለከሉ ተግባራት መካከል የሚጠቀስ ነው።

መመሪያው በትምህርት ቤቶች፣ በዩንቨርስቲዎች፣ እና በሌሎች የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደትን የሚያውክ አድማ ማድረግ፣ የትምህርት ተቋማትን መዝጋት ወይም በነዚህ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድረስ የተከለከለ መሆኑ ተመላክቷል።

በስፖርት ማዘውተሪያ አድማ ማድግም የተከለከለ ሌላው ተግባር ሲሆን፥ መመሪያው ላይ እንደሰፈረው በስፖርት ማዘውተሪያ ማእከላት፣ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ የሆኑ ሁከቶችን፣ ብጥብጦችን መፍጠር የተከለከለ መሆኑ ተደንግጓል።

የተሸከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ማወክ
===================
መመሪያው የተሽከርካሪ፣ የእግረኛ እና ሌሎች የመጓጓዣ ዘዴዎችን እንቅስቃሴ መንገድ በመዝጋት በዛቻ እና በሌሎች መሰል ድርጊቶች ሰላማዊ እንቅስቃሴን ማወክ፣ አገልግሎት ማስተጓጎል፣ የመጓጓዣ ዋጋ ታሪፍ መጨመር፣ የሚመለከተው አካል ከደለደለደው የስራ ስምሪት ውጪ መሆንን መመሪያው ይከለክላል።

በመሰረተ ልማት አውታሮች እና ሃይማኖታዊ ተቋማት ላይ ጉዳት ማድርሰም በመመሪያው ተከልክሏል።

በግል፣ በህዝብ እና በመንግስት ማናቸውም ተቋማት፣ መሰረተ ልማቶች፣ በኢንቨስትመንት እና በሌሎች የልማት አውታሮች እንዲሁም ሃይማኖታዊ ተቋማት ላይ በማንኛውንም ምንገድ ጉዳት ማድረስ ወይም ዘረፋ መጸፈምም የተከለከለ ነው ይላል መመሪያው።

ህዝባዊ እና ብሄራዊ በዓላትን ማወክን አስመልክቶ በመመሪያው የሰፈረው ድንጋጌውም፣ በኣላቱን በማንኛውም ሁኔታ ማወክ፣ ማደናቀፍ፣ ወይም ከበዓሉ አላማ ጋር የማይገናኙ፣ የፖለቲካ አጀንዳዎች ወይም መፈክሮችን በማንኛውም መንገድ ማስተጋባትን ይከለክላል።

በሃይማኖታዊ ፣ባህላዊ እና ህዝባዊ በኣላት ላይ ቅስቀሳ ማደረግ
==================================
በመመሪያው መሰረት በሃይማኖታዊ ተቋማት ውስጥ በሚደረጉ ስብከቶች እና ትምህርቶች ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ከማስተማር ውጪ በህዝቦች መካከል መጠራጠር እና መቃቃርን የሚፈጥር፣ በህብረተሰቡ ላይ ስጋት የሚፈጥር፣ ሁከት እና ብጥብጥ የሚቀሰቅስ ቅስቀሳ ማደረግ ተከልክሏል።

የህግ አስከባሪዎችን ስራ ስለ ማወክም መመሪያው ያስቀመጣቸው ክልከላዎች
==========================================
የህግ አስከባሪ አካላት የሚሰጡትን ማንኛውንም ትእዛዝ አለማክበር ስራቸውን ማደናቀፍ፣ ለፍተሻ አለመተባበር ወይም እንዲቆም ሲጠየቅ አለመቆም፣ ኬላዎችን ጥሶ ማለፍ ከተከለከሉ ተግባራት ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው።

በህግ አስከባሪ አካላት ባልደረቦች ላይ ጥቃት መፈፀም ወይም ለመፈፀም መሞከር የተከለከለ ሌላ ተግባር ነው።

ያልተፈቀዱ አልባሳትን ስለ መለስበስም
======================
የህግ አስከባሪ ሃይሎችን የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) መልበስ፣ ይዞ መገኘት፣ ቤት ማስቀመጥ፣ አሳልፎ መስጠት እና መሽጥ ክልክል መሆኑም በመመሪያው ተደንግጓል።

ማናቸውም የጦር መሳሪያ፣ ስለት ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ወደ ገበያ፣ ሀይማኖት ተቋማት፣ ህዝባዊ በዓላት የሚከበሩበት ወይም ወደ ማናቸውም ህዝብ የሚሰበሰብበት ቦታ ይዞ መግባት የተከለከለ ነው።

ማንኛውም የህግ አስከባሪ አካላት ባልደረባ ወይም ማንኛውም ህጋዊ ትጥቅ ያለው ሰው ትጥቁን በማንኛውም ሁኔታ በሶስተኛ ሰው እጅ እንዲገባ ማድረግም የተከለከለ ነው።

ማንነትን ወይም ዘረን መሰረት ያደረገ ማንኛውም አይነት ጥቃት መፈፀም ወይም ጥቃት አንዲፈፀም የሚያነሳሳ ንግግር መናገርንም መመሪያው ይከለክላል።

ማንኛውም ሰው ከውጭ መንግስታትም ሆነ ከውጭ ማንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የሀገር ሉአላዊነት፣ ደህንነት እና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ሊጎዳ የሚችል ግንኙነት እና የመልእክት ልውውጥ ማድረግም በመመሪያው የተከለከለ ነው።

እንዲሁም ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የሀገርን ሉአላዊነት፣ ደህንነት እና ህገመንግስታዊ ሰርዓትን የሚጎዳ ማናቸውም ጋዜጣዊ መግለጫ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሚዲያዎች መስጠጥም መመሪያው ከልክሏል።

ያልተፈቀደ ቦታ ከመገኘት ጋር ተያይዞም መመሪያው፥ ከስደተኛ ካምፕ አግባብ ካለው አካል ከሚሰጥ ፈቃድ ውጪ መውጣት ወይም ህጋዊ ቪዛ ሳይኖረው ወደ ሀገር ወስጥ መግባት ክልክል ነው።

ከኮማንድ ፖስቶ እውቅና እና ፈቃድ ሳያገኙ ዲፕሎማቶች ለራሳቸው ደህንነት ጥበቃ ሲባል ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ራዲየስ ውጪ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑም በመመሪያው ላይ ተብራርቷል።

የህግ አስከባሪን በተመለከተም ማንኛውም የህግ አስከባሪ አካል ባልደረባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈጻሚ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ መልቀቅ ወይም አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር የዓመት እረፍት ፈቃድ መውሰድንም መመሪያው ይከክላል ተብሏል።

በመመሪያው የተከለከሉ ተግባራትን በማለፍ ህገ ወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ሰዎችን፣ በገንዘብ እና በቁሳቁስ ወይም በማናቸውም ሌላ መንገድ መደገፍ እንዲሁም ከለላ መስጠት፣ መደለያ መስጠት እና ማበረታታትንም መመሪያው እንደሚከለክል ተነግሯል።

በተወሰኑ አካባቢዎች እንዳይፈጸሙ የተከለከሉ ተግባራት
==============================

ኮማንድ ፖስቱ እየወሰነ ይፋ በሚያደርጋቸው ቦታዎች ወይም አካባቢዎች ላይ ማናቸውነም የጦር መሳሪያ፣ ስለት፣ ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ከግቢውና ይዞታው ውጪ ይዞ መንቀሳቀስ ክልክል መሆኑ በመመሪያው ላይ ተገልጿል።

የሰዓት እላፊን በተመለከተ
==============
የኢኮኖሚ አውታሮች፣ መሰረተ ልማትና የኢንቨስትመንት ተቋማት፣ የእርሻ ልማቶች፣ ፋብሪካዎችና መሰል የልማት ተቋማት አካባቢ ከቀኑ 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከተፈቀደለት ሰራተኛ በስተቀር ማንኛውም ሌላ ሰው መንቀሳቀስንም መመሪያው ይከለክላል።

በእነዚህ ስፍራዎች ላይ የሰዓት እላፊውን ተላልፎ በተገኘ ማንኛውም ሰው ላይ የጥበቃ ወይም የህግ አስከባሪ አካላት አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ስልጣን እንደተሰጣቸውም ተብራርቷል።

የሰዓት እላፊን በተመለከተም ማናቸውም ሰው በኮማንድ ፖስቱ ውሳኔ የሰዓት እላፊ በይፋ በሚገለጽበት ቦታና ጊዜ የሰዓት እላፊ ክልከላን በመተላላፍ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ አንደማይፈቀድም ተገልጿል።

በተያያዘ ሰላምና ፀጥታን ሊያደፈርሱ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎች ወይም ቡድኖች ወይም ለጉዳት ተጋላጭ ናቸው ተብለው የሚገመቱ ሰዎች ወይም ቡድኖች ወደ ተወሰነ አካባቢ ወይም ህንፃ እንዳይገቡ ወይም በተፈቀደላቸው አንድ የተወሰነ አካባቢ ብቻ እንዲቆዩ የተሰጠን ትእዛዝ መተላለፍ ክልክል መሆኑም ተገልጿል።

ለአካባቢው ደህንነት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ወደ ተዘጋ መንገድ ማንም ሰው እንዳይገባ በኮማንድ ፖስቱ የተሰጠውን እድግ ወይም ክልከላ መተላለፍም መመሪያው ይከለክላል።

መረጃ የመስጠት እና የማስታወቅ ግዴታን በተመለከተ
==============================
ማኛውም ቤት፣ ቦታ፣ ክፍል ወይም ተሽከርካሪ ወይም ተመሳሳይ መገልገያዎችን አከራይ ከሆነ የተከራዩን ማንነት በዝርዝርና በጽሁፍ የመያዝ እና አቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ በ24 ሰዓት ወስጥ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፤ በተጨማሪም የውጭ ሀገር ዜጋን ያከራየ እንሆነ የፓስፖርቱን ኮፒ እና የኪራዩን ውል በአቅራቢያው ላለ ፖሊስ ጣቢያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት።

የህዝብ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅ ሲባል ማንኛውም ተቋም መረጃ እንዲሰጥ በየደረጃው ባለ የህግ አስከባሪ አካል ሲጠየቅ የመስጠት እና የመተባበር ግዴታ አለበት።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on October 16, 2016
  • By:
  • Last Modified: October 16, 2016 @ 11:47 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar