www.maledatimes.com በጎንደር እና ጎጃም ላይ የህወሃት(ተሃት) መንግስት የተጠናከረ ጥቃት ከፍቷል - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

በጎንደር እና ጎጃም ላይ የህወሃት(ተሃት) መንግስት የተጠናከረ ጥቃት ከፍቷል

By   /   November 2, 2016  /   Comments Off on በጎንደር እና ጎጃም ላይ የህወሃት(ተሃት) መንግስት የተጠናከረ ጥቃት ከፍቷል

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 54 Second

 1003337_10151791565549743_1973492391_n

አለበል አማረ እንደአጠናቀረው
የህወኃት አገዛዝ ራሱን በኮማንድ ፖስት ካደራጀበት ጊዜ ጀምሮ በአንዳንድ የአማራ ከተሞች፤ ህዝቡ ለወሳኙ ተጋድሎ ለሚያደርገው ሁለገብ ዝግጅት የተፈጠረውን ክፍተት ተጠቅሞ ባለፉት የተጋድሎ እንቅስቃሴወች እንቅስቃሴውን በማስተባበርና በመምራት ወሳኝ ያላቸውን ወጣቶች፤ በክልላችን በሚኖሩ የትግራይ ተወላጆችና በተወሰኑ የኛወቹ አጋሰሶች ጥናት አካሂዷል።

ይህንን ጥናት ታሳቢ በማድረግም በያዝነው ሳንት ጀምሮ የተጠናከረ ግን ያልተሳካ ጅምላ አፈሳ በማድረግ ላይ ነው።
ጀግኖቹ የጎንደርና የጎጃም አማራ ወጣቶች በያሉበት በቻሉት ሁሉ እየተፋለሙ ነው፤ በአንዳንድ አካባቢወችም ድንቅና ግሩም የሆኑ አኩሪ ታሪኮች እየተሰሩ ነው።
በዚህ በያዝነው ሳምንት በአንዳንድ አካባቢወች የተወሰነ ወጣት በህወኃት የአፈና ኃይሎች ተይዘው በኮማንድ ፖስቱ እስር ላይ የሚገኝ ቢሆንም ( ኮማንድ ፖስቱ የራሱ እስር ቤቶች መመስረቱ ታውቁአል) አብዛኛው ወጣት ግን ጫካ መግባቱ ተረጋግጧል።
እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ለማክሸፍና ወደ ተሟላ አጥቂነት ለመሸጋገር የአማራ የጎበዝ አለቆች እያካሄዱት ያለውን ተጋድሎ እንዲሁም በውጭ ያሉ የተጋድሎ አክቲቪስቶች የተቀናጀ የተጋድሏቸው እንቅስቃሴወችን በማድነቅና የሚካሄዱት የተጋድሎ ስራወች እንደተጠበቁ ሁነው፤
ከማያቸውና ከምታዘባቸው ይበልጥ ልንረባረብባቸው፤ ትኩረት ልንሰጥባቸው የሚገቡን ጉዳይዮችን ለማጋራት ፤
√ የአማራ ወጣት ገዳይ ጠላቶቹን በዱር በገደሉ በከተማ በገጠሩ አምርሮ እየተጋደለ ይገኛል፤ ወጣቱ የሚታገለው ከተደራጀ፣ የፋይናንስና የማተሪያል አቅም ካለው ጨቁአኝ ኃይል ጋር በመሆኑ ተመጣጣኝ ነገር ኣንኩኣን ማቅረብ ባይቻልም አቅም የፈቀደውን ያክል ድጋፍ ማግኘት ይገበዋል፤ ስለሆነ በአማራ ተጋድሎ ስም ግልፅና አስቸኩኣይ የሃብት (ገንዘብ) ማሰባሰብ ስራ በዘመቻ መከናወን አለበት። ይህንንም በተለይ በውጭ በስራው እየተሳተፉ ያሉ ወጣቶች ተቀዳሚ ተግባራቸው ማድረግ አለባቸው።
√የተጋድሎው አዝማሚያ ሁለገብ ስራው እንደተጠበቀ ሁኖ፤ በበረሃ የመደራጀትና የመዘጋጀት ስራ ትኩረት የሚያስፈልገው ይመስላል። ይህን ስራ በተወሰኑ አካባቢወች ብቻ አለመወሰን፣ የሰው ኃይል ችግር እስከለለ ድረስ የበዙ መሬቶችን መጠቀም ለተጋድሎው ስራ ጊዜ ያሳጥራል ኪሳራ ይቀንሳል በአንጻሩ የጠላትን ኃይልና ሃሳብ ይበታትናል።

√የአማራ ህዝብ በቀንደኛ ጠላቱ ህወኃት ላይ ራሱን የመካለከል ተጋድሎ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስካለንበት ጊዜ ድረስ የትግራይ ተወላጆች በቀጥታ በመሳተፍም ሆነ የመረጃ ምንጭ በመሆን ከባድ ጉዳት እያደረሱብን ነው፤ ስለሆነም እነዚህን የጠላት አቅሞች መስበርና የጥንካሬ ምንጭ እንዳይሆኑ የማድረግ ስራ በቁርጠኝነት መስራት ቀጣይ መሆን አለበት፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የራሳችን አጋሰሶችንም ለይተን የማውገዝና በማይታረሙት ላይም አስተማሪ ኣርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።
√ለአማራው ተጋድሎ እንቅፋት ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ የኃይማኖቶቻችን ሃላፊወችና መሪወች ናቸው። የአማራ ህዝብ ለየኃይማኖቱ በጥብቅ አማኝ መሆኑን የተረዳው ህወኃት ይህንን ክፍተት በሚገባ በመጠቀም ከባድ ጉዳት እንዲደርስብን እያደረገ ነው። ጥቂት የሃይማኖት አባቶች እውነተና አባትነታቸውን እያስመሰከሩ ያሉ ቢሆንም አብዛናው የኃይማኖቶቻችን መሪወች የፖለቲካ ሹመኞች መሆናቸው ከተረጋገጠ ቆይቷል፤ በተግባርም የህወኃትን ስርዓት ዕድሜ ለማርዘም ተግተው የሚሰሩ ቅጥረኞች ናቸው። የአማራ ወጣት እምነቱን እና መሪወቹን ለይቶ መመልከት አለበት እላለው። እምነቱን ማመን ይኖርበታል ለህወኃት ዕድሜ ምርዘም የሚሰሩ መሪወቹ ግን ህዝቡ የከዱ ስለሆኑ ማመን የለበትም።
ውድማው ይለቅለቅ ይሰጣበት ነዶ፣
የኛ ተራ ቀርቷል ያ ሂዶ ያ ሂዶ፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on November 2, 2016
  • By:
  • Last Modified: November 2, 2016 @ 12:54 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar