ሙሽሮች በሰርጋቸው ማግስት መኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ

ሙሽራና ሙሺሪትን ጨምሮ ስምንት ሰዎች በመኪና አደጋ ህይወታቸው አለፈ። ነገሩ የሆነው አገር ቤት ነው። የቡራዩ ነዋሪ የሆኑት ሙሽሪትና ሙሽራ ፣ ከነሚዜዎቻቸው ሠርጋቸውን ያደረጉት ጎጃም ነበር። ሠርጉም የነበረው ባለፈው ቅዳሜ ሲሆን፣ ሠርጉም ተከናውኖ እሁድ መመለስ ነበረባቸው። ዜናው እንደሚለው ፣ የአባይን በረሃ መንገድ በሰላም ጨርሰው ሰሜን ሸዋ፣ በተለይም በዳበን ወረዳ፣ አናጅሩ የተባለው መንደር አካባቢ ሲደርሱ  ከገልባጭ መኪና ጋር በመጋጨታቸው በቢቸና ከተማ ከተካሄደው ሰርግ ሲመለሱ የነበሩት ሙሽሮች ከነቤተሰቦቻቸው ወዲያውኑ ህይወታቸው አልፏል።
ሾፌራቸው ግን ተጠንቅቆ ማለፍ ሲገባው፣ ከፊቱ ያለውን ሌላ መኪና ቀድሞ ለማለፍ ባደረገው ሙከራ ክፊት ለፊታቸው ከመጣው ገልባጭ ጋር ሊጋጩ ችለዋል። በውስጡ ከነበሩት 15 ሰዎች መካከልም ስምንቱ ህይወታችው ሲያልፍ ፣ ክሟቾች መካከል ሙሽሮቹ እና ሚዜዎቻቸው ይገኙበታል ተብሏል። የቆሰሉት ሌሎች አምስት ተሳፋሪዎች ደግሞ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው በማለት የዞኑ የፖሊስ መምሪያ ክፍል ሃላፊ የሆኑት  ኮማንደር ደረጀ ፈጠነ፥ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው አምስቱ ሰዎች ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተወስደው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።
በአገር ቤት ብዙውን ጊዜ ደርቦ ለማለፍ በመሞከር ከሌላ አቅጣጫ የሚመጣን መኪና ባለማስተዋል እንዲሁም፣ ጠጥቶና በጫት ምርቃና በከፍተኛ ጡዘት ውስጥ ሆኖ  መኪናን በማሽከርከር እና ከፍጥነት በላይ በመንዳት የሚደርሱ አደጋዎች ትልቁን ሥፍራ ይይዛሉ። 
የኢትዮጵያ የተሽከርካሪዎች ትራፊክ አደጋ ቁጥጥር መምሪያ ክፍል ለዚህ ከፍተኛውን የሆነውን ሃለፊነቱን ሊወጣ እና እንደዚህ አይነት የማን አለብኝነት እና ህግን በአግባቡ ባለመጠቀም ከህግ ውጭ የሚሆኑ ለአደጋው ሰለባ በሚያደርሱ ባለንበረቶችን እና አሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ከፍተኛ ቅጣት ሊጣልበት ይገባል ፣ አደንዛዥ እጾች ከሚሰኙት መካከል እንደ ጫት አይነቶቹን እና መጠጥ በመጠጣት የሚያሽከረክሩትን ከአስር አመት ያላነሰ የእስር ቅጣት የሚያደርስ እና የመንጃ ፈቃድ የሚያስነጥቅ ቢሆንም በከተማዋ የተሰራጩት ፖሊሶች በሙስና የተዘፈቁ መንግስት የቀጠራቸው ዘራፊዎች በመሆናቸው ብቻ በእነዚህም አይነቶቹ ፖሊሶች ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሚስጥራዊ ሂደት ክትትል በማድረግ ፣በስራ ቦታ ላይ ፣የመንግስት ስራን አግባብ ባልሆነ ቦታ ላይ በመጠቀም ወንም በመባለግ መክሰስ እና ቅጣት ሊጣልባቸው ይገባ ነበር ሆንም ግን መንግስት የሌለው አገር ፣እራሱ መንግስት ነኝ የሚለው ዘራፊ ድርጅት በቀጠራቸው ግለሰቦች ሲዘረፍ ማየት ዝምታን ፈጥሮለታል ፣ለቀጠራቸውም አገልጋዮች መልካም እድልን ፈጥⶂአል
Image may contain: one or more people, people standing, tree, outdoor and nature

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar