የ17 አመቷን ልጅ አፈቅርሻለሁ በማለት በስለት ወግቶ በአደባባይ ገደላት

በጠራራ ፀሐይ ‹‹አፈቅርሻለሁ!›› በሚል ምክንያት የ17 ዓመቷ ተማሪ ኑሃሚን ጥላሁን በስለት ወግቶ የገደለው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ የሚል ዜና ብንሰማም ለእንደዚህ አይነቱ ነፍሰ ገዳይ የሞት ፍርድ የማይፈርድ የዳኝነት ና የፍትህ ስርአት መኖሩ ግን በጣም ተስፋ አስቋራጭ ነገር ነው ፡፡

አስቡት ምንም ያላጠፋች ህጻን ልጅን የገደለ ነገ ከእስር ተፈቶ በአደባባይ ሲራመድ ማየት በጣም ያሳምማል! !

ሟቿ – የቦሌ ኮሙኒቲ የሕዝብ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነበረች፡፡ ከትምህርት ቤት ስተመለስ፣ ቦርሳዋን እንዳነገተች – እንደወጣች ቀርታለች፡፡
ኑሃሚንን ሕዝብ ተባብሮ ባልቻ ሆስፒታል አድርሷት የነበረ ቢሆንም በሕክምና ጥረት ሕይወቷን ለማትረፍ የተደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
በዚህን ጊዜ በሆስፒታል ግቢ የፈሰሰው ሕዝብ በዋይታ – በእንባ ሲራጭ ማምሸታቸውን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
የወንጀሉ ድርጊት የከተማችን መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል፡፡
እናቷ ወይዘሮ ወይንሸት ወዳጅ ሀዘን በሰበረው ድምፅ፤ ‹‹ … ልጄን ነጠቀኝ! … አበባዬን ነጠቀኝ! … እህቴን፤ ጓደኛዬን ነጠቀኝ! … እህህህ … አቧቷ በአንድ ዓመት ከስድስት ወራት እድሜ ላይ በሞት ተለይቷታል፡፡ ተለይቶናል፡፡ … ብቻዬን፤ ቀረሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋረደኝ ሲሉ
ገልፀዋል፡፡ ነብስ ይማር !!!

Image may contain: 1 person, hat, outdoor and closeup
Image may contain: 1 person, child and closeup
Image may contain: 1 person, sitting
Image may contain: 3 people, people standing

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar