www.maledatimes.com የማለዳ ወግ … ሰው ገድለው አንገታቸው ሊቀላና ሊያሳዝኑን የነበሩት በነጻ ተለቅቁ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የማለዳ ወግ … ሰው ገድለው አንገታቸው ሊቀላና ሊያሳዝኑን የነበሩት በነጻ ተለቅቁ!

By   /   March 24, 2017  /   Comments Off on የማለዳ ወግ … ሰው ገድለው አንገታቸው ሊቀላና ሊያሳዝኑን የነበሩት በነጻ ተለቅቁ!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 21 Second
* ሟች – ሊደፍራቸው የመጣ ሳውዲ ወጣት
* ገዳይ – ሚስትና ቤቱን የተከላከለ ጎልማሳ
*  ፍርድ ሰጭ – ከፍተኛው የሸሪአ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት
* እነ ሁሴን እንደገና አልተወለዱ ይሆን  ?

ልክ የዛሬ 3 ዓመት ገደማ ሳውዲ አረቢያ ጅዳ “ሀበሾች ሳውዲ ገደሉ!” ተባለ ፣ መረጃውን የሰማሁት እኔም በእስር ላይ እያለሁ ነበር ። እንዴት ገደሉ ብየ ስጠይቅ ቤታቸውን ሊዘርፉና የሀበሻውን አባወራ ቤት ሊዘርፉ የገቡ ሳውዲ ወጣቶች ሴቶችን ሊደፍሩ በተነሳ አምባጓሮ መሆኑን በደፈናው ሰማሁ ። ከዚያም የቀረውን ተባራሪ የእስር ቤት መረጃ የማጣራበት መንገዱ ዝግ በሆነበት የጨለማ ወቅት ገደሉ የተባሉት ወደሚታጎሩበትና እኔ ወዳለሁበት ወህኒ እስኪመጡ የታሳሪውን ተባራሪ የማያጠግብ መረጃ ሳነፈንፍና ስኮመኩም ከረምኩ  ። ከሶስት ወር በኋላ  እኔ ከወህኒ እስክወጣ ወደ ማዕከላዊው የብሪማን እስር ቤት ሳይመጡ ቀሩ ፣  እኔም ጉዳይ ተጣርቶ ለእስር ወጣሁ …

   ከእስር ከወጣሁ በኋላ ጉዳዩን ከገዳዮች አንደበት የመስማት እድሉ ገጠመኝ ” ከንጋቱ ላይ የኢድ በዓልን ልናከብር ስንዘገጃጅ ቤታችን ተንኳኳ ፣ ማነው ?  ስል ፖሊሶች ነን አሉኝ ፣ ከፈትኩላቸው ። ግብተው ሴትና ወንድ ብለው ለያይተው አስቀመጡን ፣ ዘረፋ ጀመሩ ፣ ዝም አልን ፣ ቆዩና ሴቶቻችን ለመድፈር ሲሞክሩ የባለቤቴን ጩኸት ሰማሁ ፣ ዘልዬ ከተዘጋው ክፍል ወጣሁና ከወጣቶች ጋር  ግብግብ ያዝን ፣ …ሟች ሳውዲ ስለት ይዞ ሊወጋኝ ሲሰነዝር የያዘውን ስለት ቀኝቸ ደረቱ ላይ ወጋሁትና ከቤቴ በር ገፍቸ አስወጣሁት ፣ ጓደኞቹ ተረባርበው ወሰዱት ፣ ፖሊስ ጠርተው ነበርና በፖሊስ ተከበን ተያዝን …ሚስቴን ሊደፍር ስከላከል ብወጋውም ይሞታል አላልኩም ነበር ፣ መሞቱን ሰማሁ ፣ አዘንኩ …” ይህን ምስክርነት የሰጠኝ የወንጀሉ ተጠያቂ ገዳይ ወንድም ሁሴን ሃሰን ነበር ! ታዲያ ያኔ በሞት ፍርደኞች መካከል የጨለማ ህይወትን ሲገፋ በነበረበት በጭንቋ ሰአት ሆን ብየ ነፍስ አላጠፋሁምና ስለፍርህ ድምጻችን አሰማልን ብሎ ተማጽኖኝ ነበር  !
ከዚያ ወዲህ ባሉት ጊዜያት  የወንደም ሁሴንን ወንድምና የሁለት ጓደኞቹን የፍርድ ሂደት በቅርብ ተከታትተዋለሁ ፣ መረጃም በሰፊው አቀርብበት ነበር ። ሳውዲ መተዳደሪያ ባደባደረጋቸው የሸሪአው ህግ ” የገደለ ይገድላል” ቢባልም እንኳ  የራሱ ስርአትና ደንብ ስለመኖሩ ይህ ውሳኔ ማሳያ ይመስለኛል ፣ ግፍ ሲፈጸምበት ራሱን ሲል ገደለ ትበሎ ይገደል እንደማይባል ትልቅ ማሳያ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን በስራ ላይ ውሎ በእኛ ዜጎች ላይ ስላየሁት ደስ ብሎኛል ። ለዜጎች መብት የምናስብ ከሆነም ይህ አስተማሪ ነው ።
የደስታየ ምንጩና ተወካዮቻችን የምመክረው !
=============================
የሳውዲ ህግ አያሰራንም ከሚለው ተራ ቱማታ መውጣት ከቻልን ብዙዎችን መታደግ እንደምንችል ምልክት ነው ።  ይህን እውነት ተከትለን በህግ አግባብ ፍትህ ማግኘት ስላለባቸው የሞት ፍርደኞች መብት ማስከበር ዙሪያ ተወካዮቻችን እንዳለባቸው ጠቋሚ ነው ።

እንደ ቀደሙት አመታት በየስብስባው  ” የሳውዲ ህግ ለመብት ጥበቃው አይመችም ” የሚል ስንካላ ምክንያት ከተወካዮቻችን ሲቀርብ መስማት አንሻም ። በተለይ በአረብ ሃገራት ያሉ የመንግሰት ተወካዮቻችን ከዚህ ፍርድ ተነስተው ምን እየሰራን ነው ብለው ራሳቸውን መመርመር ይገባቸዋል ! ልብ ያለው ልብ ይበል   ! የጎዳን የሳውዲ ህግ ሳይሆን ህጉን ተከትሎ መብታችን የሚያስከብር ሁነኛ የመንግሰት  ተወካይ ነው ፣ ደረቅ እውነቱ ይህ ነው ። ዛሬ ከምንም በላይ የዘገየው ፍትህ ርትዕ እንዲህ ተከብሮ በማየት ደስ ብሎኛል ፣ ነገም ግፍ ተፈጽሞባቸው የታሰሩት ዜጎቻችን ነጻ የሚወጡበት ተስፋ እንዳለ በሚያነላክተው የፍርድ ውሳኔ እርካታ ተስምቶኛል ፣ ተደስቻለሁ  !

   ሁሉንም በወጉ ከነጻ ከተፈቱት ከእነ ሁሴን ጋር ቁጭ ብለን እናዎጋለን  ፣ ደስታቸውን እንጋራለን ፣  የሞት ፍርደኞችን ህይወት ያለ ተስፋ የሚገፋበትን የጨለማውን የእስር ቤት የአመታት ውሎ አዳር በጨረፍታ ማውጋታችን አይቀርም  ! በእነ ሁሴን ዙሪያ መረጃ ስንለዋወጥ ትብብራችሁ ላልተለየኝ ፣ በጸሎት ለረዳችኋቸው ሁሉ እኔም እነሆ Mission Accomplished እያልኩ በደስታ ምስጋናዬን አቀርባለሁ  !
በዝርዝር እስክመለስ ወንድም ሁሴንና ጓደኛ ፣ ቤተሰቦቹ እንኳን ደስ አላችሁ ፣ እንኳን ደስ አለን  !

ዛሬም ዜጎቻችን በደል ደርሶባቸው በየወህኒው ይገኛሉ ፣  ስለተበደሉት ድምጻችን እናሰማ  !

ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓም
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on March 24, 2017
  • By:
  • Last Modified: March 24, 2017 @ 12:22 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar