www.maledatimes.com ይድነቃቸው ከበደ የመከላከያ ምስክሮቹን ዛሬ አስደመጠ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይድነቃቸው ከበደ የመከላከያ ምስክሮቹን ዛሬ አስደመጠ

By   /   June 15, 2017  /   Comments Off on ይድነቃቸው ከበደ የመከላከያ ምስክሮቹን ዛሬ አስደመጠ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 50 Second

በፍቃዱ ሃይሉ እንደዘገበው

(ፍርድ ቤቱ “ጥፋተኛ” ሆኖ ካገኘው “በቀላል እስራት፣ ወይም በመቀጮ፣ ወይም ወንጀሉ ከባድ በሆነ ጊዜ ከሦስት ዓመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ይቀጣል”)

ነሐሴ 28/2008 በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የደረሰውን ቃጠሎ ተከትሎ እስረኞች ወደ ዝዋይ እና ሸዋሮቢት መዘዋወራቸው ተጠቅሶ ጳጉሜ 3/2008 ቀን እስረኞቹ ያሉበትን አድራሻ እንደሚያሳውቁ ከማረሚያ ቤት አስተዳደር ተገልፆ ነበር።

በተጠቀሰው ዕለትም [ጳጉሜ 3/2008] የሚፈልጋቸውን እስረኞችን (ማለትም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ እስረኞች የተዘዋወሩበትን) አድራሻ ለማወቅ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሔደው የሰማያዊ ፓርቲ አባሉ ይድነቃቸው ከበደ፣ ሲመለስ ሲቪል በለበሱ ግለሰቦች ተይዞ መታሰሩ ይታወሳል። ለአንድ ሳምንት በእስር ቆይቶ በ5,000 ሺ ብር ዋስ ከእስር ከወጣ በኋላ በ14/3/20009 የወንጀለኛ ሕግ አንቀፅ 486(ሀ)ን በመተላለፍ፤ «ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አካባቢ የሕግ ታራሚዎች ቤተሰቦችን “መንግሥት ታራሚዎችን አቃጥሎ ለምን ዝም ብላችሁ ታያላችሁ፣ አትጮሁም ወይ፣ አታለቅሱም ወይ አሁን እኛም መታገል አለብን” በማለት የሐሰት ወሬዎች በማውራት፣ ሕዝብን በመቀስቀስ እና ማነሳሳት ወንጀል» በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቃቂ ቃሊቲ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበታል።

በመሐሉ፣ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከታወጀ በኋላ በድጋሚ ታስሮ አዋሽ ሰባት የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ “የተሐድሶ ሥልጠና” ወስዶ በታኅሣሥ ወር ከተፈታ በኋላ የቀጠለው ይህ ክሱ፣ ግንቦት 14/2009 ቀን በተሰሙት ሁለት የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ተፈፀመ የተባለውን ድርጊት በተመለከተ ተመሳሳይ ያልሆነ (እርስ በርሱ የሚጋጭ) ምስክርነት የሰጡ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን ከክሱ ነፃ ለመውጣት ራሱን መከላከል እንዳለበት ብይን ሰጥቷል።

ዛሬ በነበረው ቀጠሮ ይድነቃቸው ከበደ መከላከያ ምስክሮቹን እና የምስክርነት ቃሉን አሰምቷል። ማረሚያ ቤቱ ባቀረበው ጥሪ መሠረት ወደቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የሔደው የሚፈልገውን እስረኛ አድራሻ ለማወቅ እንደነበረ እና ማረሚያ ቤት ደርሶ እስረኛው የት እንዳለ ካወቀ በኋላ በመመለስ ላይ እያለ በሲቪል ፖሊሶች ተይዞ እንደታሰረ የምስክርነት ቃሉን በሚሰጥበት ጊዜ አስረድቷል።

አንደኛው ምስክር የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ የሽዋስ አሰፋ፣ ከይድነቃቸው ቀደም ብለው ማረሚያ ቤት እንደደረሱ፣ የሚፈልጉትን እስረኛና የተዛወረበትን አድራሻ ለመስማት ተቀምጠው እያሉ ይድነቃቸው ከሌላ ከማያቁት ሰው ጋር እንደመጣ፣ ይድነቃቸው የሚፈልገው እስረኛ አድራሻ ከእርሳቸው ቀድሞ በማወቁ ተሰናብቷቸው እንደሄደ እና በወቅቱ ምንም የተከሰተ ረብሻ እና ሁከት እንዳልነበረ መስክረዋል።

ሁለተኛ ምስክር የሆነው ሀይለመለኮት አሰፋ፣ ከይድነቃቸው ጋር አብሮ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሔዶ ይድነቃቸው የሚፈልገው እስረኛ የት እንዳለ ካወቀ በኋላ ወደየቤታቸው በመመለስ ላይ እንዳሉ ሲቪል የለበሱ ሰዎች ጠርተውት ትንሽ አናግረውት፣ በፒክአፕ መኪና ይዘውት እንደሄዱ፣ በወቅቱ ፖሊሶች እና ወታደሮች በአካባቢው በርከት ብለው እንደነበረ እና ሁኔታው ሁሉ ሠላም እንደነበረ ተናግሯል።

ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ከይድነቃቸው መከላከያ ምስክሮች ጋር አመሳክሮ የጥፋተኝነት ፍርድ ለመስጠት (“ጥፋተኛ” ወይም “ነፃ” ለማለት) ለሐምሌ 3/20093 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።Image may contain: 1 person, sitting and beard

No automatic alt text available.

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on June 15, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 15, 2017 @ 10:30 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar