www.maledatimes.com ተመላሽ ዜጋው ክብር ሊሰጠውና ሊስተናገድ ይገባል ! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ተመላሽ ዜጋው ክብር ሊሰጠውና ሊስተናገድ ይገባል !

By   /   June 23, 2017  /   Comments Off on ተመላሽ ዜጋው ክብር ሊሰጠውና ሊስተናገድ ይገባል !

    Print       Email
0 0
Read Time:3 Minute, 30 Second

የማለዳ ወግ…ተመላሽ ዜጋው ክብር ሊሰጠውና ሊስተናገድ ይገባል !
======================================
* በሪያድና ጅዳ የተመላሹ ወገን እልህ አስጨራሽ እንግልት !
* የሪያድ ኢንባሲ ዲፕሎማቶች ተገፊዎችን ጎብኝተዋል
* በጅዳ የቆንስል ኃላፊዎች የተገፊዎችን ሮሮ አይሰሙም

ተመላሹ ወገን ሪያድ ላይ …
==================
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በጅዳና በሪያድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ መስተጓጎል ስለሚንገላቱ ወገኖች ተደጋጋሚ መረጃ ደረሶኛል ። ወደ ቦታው በመደወል የደረሰኝን ሮሮ ለማጣራት ሞክሬያለሁ ። በሁለቱም ከተሞች በተለይ ከታዝነው ሳምንት ጀምሮ ቀንና ማታ የበቃውን ሙቀትና ውበቅ ከጾሙ ጋር ተቋቁመው የሚንገላቱ ወገኖች የሚሰማው ሮሮ ሰላም ይነሳል ። ማምሻውን በሪያድ አየር መንገድ በግምት 1000 በላይ የሚጠጉ ዜጎች በመንገላታት ላይ ስለ መሆነቸው መረጃ ደርሶኛል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቲኬት ቆርጠው ቅድሚያ ለትራንዙት ተጓዥ የውጭ ሀገር ዜጎች በተለይም ለምዕራብ አፍሪካ ተጓዦች ቅድሚያ እየሰጠ ተመላሽ ዜጎች ጉዟቸው ተሰርዞባቸዋል ። ይህም አሰራር ብዙዎችን ተመላሾችና ተመልካቺች በጅዳና በሪያድ ያስከፋ ሆኗል ። በሪያድ ዛሬ ሶስት ያህል በረራ ቢደረግም የተስተናገደው ኢትዮጵያዊ ቁጥር በጣም አናሳ እንደሆነ ተነግሮኛል ። በቁጭት አስተያየት የሰጡኝ ወገኖች ተመላሽ ዜጋው ከፍሎ ሲስተናገደደ እንደ ደንበኛና እንደ ዜጋ ክብር ሊሰጠው ሊስተናገድ ይገባል በማለት ጠንከር ያለ ቅያሞታቸውን ግልጸውልኛል ። ከቀናት በፊት ጉዟቸው በመሰረዙ ሆቴል እንዲይዙ የተደረጉት ማምሻውን ይሳፈራሉ ተብለው ወደ አየር ቢመጡም እቃቸው ሌላ ቦታ እነሱ ሌላ ቦታ ተለያይተው የታየውን መጨናነቅ ያሳዘናቸው የአይን እማኝ ምስክርነታቸውን ሰጥተውኛል ።

በሪያድ እየታዬ ያለውን መስተጓጎል ለመመልከት ዛሬ ምሽት የሪያድ ኢንባሲ ኃላፊዎች በቦታው ተገኝተው ነበር ። አምባሳደር አሚንና አምባሳደር ፈይሰል ከአየር መንገዱ አዳራሽ እንዳይገባ ተደርጎ እየተንገላታ ያለውን ተመላሽ ዜጋ ለማረገጋት ሞክረዋል። በተደጋገሚ መግለጫና ማብራሪያም ሰጥተዋል ። የተጎዳው ነዋሪ ወደ ሀገር ለመግባት ቲኬት ቁረጡ ብላችሁ ቆረጥን ። በሰአቱ ቤታችን ለቀን እቃችን ተዘግቶ በሰነበተው ካርጎ ለመላክ ወርውረን እጅ እግራችን ይዘን እንግባ ብንል አውሮፕላን የለም ተባልን ። የት እንግባ ? ከማን በደላችን እንናገር ? ምን የተጨበጠ መፍትሔ ትሰጡናላችሁ ? በኢትዮጵያ ኢንባሲ ቁረጡ እያላችሁ አስገደደዳችሁ አየር መንገዱ ጉድ ሲሰራን የት አላችሁ ? ገንዘባችን ከፍለን ህጋዊ ድጋፍና ግልጋሎት የነፈገንን የኢትዮጵያን አየር መንገድ እንዴትስ ከዚህ በኋላ እንመነው? ” ሲሉ ሞጋች ጥያቄዎችን ለኢንባሲው ኃላፊዎች ቀርቦላቸው እንደነበር መረጃው ደርሶኛል ።

ላለፉት ሶስት ወራት ስደተኛው ወደ ሀገሩ እንዲመለስ ከፍተኛ ስራን በመስራታቸው የሚመሰገኑት የኢንባሲው ኃላፊዎች ለጥያቄዎች አንድ በአንድ ምላሽ ባይሰጡም በደፈናው የሳውዲ መንግስት ተጨማሪ በረራ ስላልፈቀደ የተፈጠረ ችግር ነው ሲሉ መልሰዋል ። በማከልም ኃላፊዎች ከሳውዲ አየር መንገድ ጋር ሳይቀር በመመካከር ጉዞውን ለመሳለጥ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን በቦታው ምስክርነታቸውን የሰጡኝ ወገኖች አስረድተዋል። ይህ ዘገባ እስከተጻፈበት ሰአት ድረስ የሪያድ ኢንባሲ ተወካዮች ከሪያድ አየር መንገድ ኃላፊዎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተመካከሩ መሆናቸውን ሰምቻለሁ !

ተመላሹ ጅዳ ላይ …
==============
ጅዳ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስተንግዶውን ወደ ሐጅ ተርሚናል ከቀየረ ወዲህ በርካታ መንገላታት እየታዬ ነው ። ከሰኔ 10 ጅምሮ ባለት ስድስት ቀናት የበርካታዎች ጉዞ በመሰረዙ ቅሬታና ምሬትን ፈጥሯል ። በየቀኑ ከበረራው ለሚመለሰሱት አየር መንገዱ ሆቴል በመያዝ ቢንከባከባቸውን ሀገር ለመግባት የሚጉላሉት ዜጎች ከረር ያለ ተቃውሞ ማሰማት ይዘዋል። ማምሻውን ቀን ይገባል የተባለ 170 ሰው አካባቢ የሚይዝ አውሮፕላን ከምሽቱ 2:00 ግብቶና የተወሰኑትን ጭኖ ተመልሷል ። በረራው ከተከወነ በኋላ ሌላ በረራ የለም በመባሉ ተሳፋሪዎችን ወደ ሆቴል እንዲሄዱ ቢጠየቁም ” የናፈቀን ወደ ሀገር መሄድ እንጅ በሆቴል መንደላቀቅ አይደለም !” በሚል ሆቴል ከሄዱ ተራቸውን እንዳይነጠቁ በመስጋት በአየር መንገዱ አወላላ ሜዳ ለማደር ተገደዋል ። ይህ ሪፖርት ሲዘጋጅ ሁለተኛ 179 ተሳፋሪ የሚጭን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ግብቷል ። በቅደም ተከተል ሳይሆን የJune 22,2017 እና ከዚያ በፊት የተመለሱ ተሳፋሪዎች ሳይስተናገዱ የJune 24 ,2017 የዛሬ ተሳፋሪዎች መስተናገዳቸው ተቃውሞ ቢያስነሳም በግልግል ሁኔታውን ማብረድ ስለመቻሉ ሁነኛ መረጃ ደርሶኛል ።
አሁንም በጅዳ የሐጅ ተርሚናል ቁጥራቸው ከ800 እስከ 1000 ይደርሳሉ የሚባሉ ተመላሾች በረራ የሚያገኙበትን መንገድ በመማጸን ላይ ናቸው።

የጅዳ ቆንሰል አንድ ተወካይ ብቻ ሳምንቱን ከተሳፋሪዎች ጋረ በመሆን ለማስተባበት መሞከረቸው መልካም ድጋፍ ይጠቀሳል ። በአንጻሩ እንደ ሪያድ ኢንባሲ የጅዳ ቆንስል ዲፕሎማቶች የተሳፋሪውን ችግር ቀርበው ተመልክተውት አያውቅም። ትናንት አንድ ቆንስል ዲፕሎማት ሁኔታውን ለመታዘብ ቢመጡም ነዋሪውንም ሆነ የአየር መንገዱን ኃላፊዎች ሳያነጋግሩ መመለሳቸው ይጠቀሳል ።

ሀገር ግባ ተብሎ በገንዘቡ ቴኬት ገዝቶ ፣ ቤቱን ለቆ ሀብቱን ሸካክፎ በተዘጋው ካርጎ አስረክቦ ቲኬት በግል ገዝቶ መስተጓጎል ይከብዳል ። በሐጅ ተርሚናል ለመግባት ጉቦ ከፍሎ መሰቃዬት በራሱ ፈታኝ ሆኗል ። በዚህ የተማረሩት ተመላሾች ” የሚደርስብንን በደል ለጅዳ ቆንስል የበላይ አንባሳደር ውብሸት ደምሴና ከእውነት የራቀ ማስታወቂያና ማሳሰቢያ ሌት ተቀን ለሚለቀልቁት ዲፕሎማቶች ንገርልን ፣ ቢሮ ሆነው መናገር መፈላሰፍ ሳይሆን የህዝብ ተወካይ ናቸውና በአካል መጥተው ጉድ የሰሩትን ህዝባቸውን ያነጋግሩን ፣ መላ ይፈልጉልን ! ” ሲሉ በጸሀይና በወበቁ የመንገላቱ ተገፊ ተመላሽ ወገኖች የሰላ ምሬት የታከለበት አስተያየት ይሰጣሉ …

ከዚህ በላይ በአጭሩ ለማስተላለፍ የፈለግኩት መልዕክት ከዜጎች የደረሰኝ ነው ፣ አቅም ፈቅዶ በድምጽ መረጃው እስካቀርበው ለጉዳዩ ትኩረት ይሰጠው ዘንድ መልዕክቱን በማሰራጨት የወገኖቻችን ድምጽ እናሰማ ዘንድ አደራዬ የጠበቀነ ነው ! የወገኖቻችን እንግልት ድምጻችን ለማሰማት እኛ መንገላታት የለብንም ፣ ህመማቸው ህመማችን ሊሆን ግደ ይላል ! እናም የሚመለከታችሁ የመንግስት ተወላዮችና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኃላፊዎች ለዚህ ወገንን በበርሃ ሙቀት እያንገላታ ለላው እንግልት መላ ፈልጉለት ! ዜጋው ለመጓጓዣ ቲኬት ከፍሎ ነውና አየተገለገለ ያለው አንድም እንደ ደንበኛ ትክክለኛ ግልጋሎት ፣ ግልጋሎቱ ሲጎድል ደግሞ ለጎደለቅ ካሳ እየተከፈለው ፣ ከፍ ሲልም እንደ ዜጋ ክብር ሊሰጠው ሊስተናገድ ይገባል !

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 17 ቀን 2009 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on June 23, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 23, 2017 @ 11:18 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar