www.maledatimes.com የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህወሀት/ኢህአዴግ የአንድ ዓመት የአገዛዝ ጉዞ በተመለከተ ውይይት አደረገ!!! - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህወሀት/ኢህአዴግ የአንድ ዓመት የአገዛዝ ጉዞ በተመለከተ ውይይት አደረገ!!!

By   /   June 27, 2017  /   Comments Off on የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህወሀት/ኢህአዴግ የአንድ ዓመት የአገዛዝ ጉዞ በተመለከተ ውይይት አደረገ!!!

    Print       Email
0 0
Read Time:2 Minute, 5 Second

 

“ህወሀት በራሱ ጠመንጃ ወደራሱ አነጣጥሮ እንደቆመ 2009 ዓ.ም ጥሎት ሂዷል፡፡”ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
“ህወሃት ዓመቱን በከንቱ ያሳለፈው ከክህደት በመጀመሩ ነው፡፡” አቶ ወረታው ዋሴ
“የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሃት ምንም ሳይጠብቅ እንደሌለ ቆጥሮ ከገባበት ውስብስብ ችግር ለመውጣት በራሱ መፍትሔ መፈለግ አለበት፡፡”ወ/ሮ መዓዛ መሀመድ


የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህወሀት/ኢህአዴግ የአንድ ዓመት የአገዛዝ ጉዞ በተመለከተ ውይይት አደረገ!!!
(በሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ የህዝብ ግንኙነት ንዑስ ኮሚቴ)


የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ሸንጎ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2009 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ አገዛዙ በ2009 በጀት ዓመት መጀመሪያ እና መጨረሻ ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታ በተመለከተ ውይይት አደረገ፡፡ በውይይቱ ብዙ ሀገራዊ ጉዳዮች ተነስተው በመድረኩ መሪዎች በአቶ ወረታው ዋሴ፣በኢ/ር ይልቃል ጌትነትና ወ/ሮ መዓዛ መሀመድ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
አገዛዙ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ብዙ ነገሮችን ለመፈፀም ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆነም
በተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የሞቱ ሰዎችን በተመለከተ ተገቢው አንድም የመንግስት አካል ተጠያቂ አልሆነም፡፡
የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ አላገኘም፡፡
ኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ ከተማ ማግኘት የሚገባውና በህገ መንግሰቱ የተሰጠው የመብት ጥያቄ መልስ አልተሰጠም፡፡
በኢትዮጵያ የስራ አጥነት፣የኑሮ ውድነት እና መረን የለቀቀው ሙስና ጉዳይ መፍትሔ አላገኘም፡፡
ከተቃዋሚዎች ጋር አደርገዋለሁ የተባለው ድርድር ቀለብ ከሚሰፍርላቸው ጋራ የሚደረግ አሰልቺ ትያትር ሆኖ አልፏል፡፡
የህሌናና የፖለቲካ እስረኞች አሁንም በር እንደተቆለፈባቸው ናቸው፡፡ይባስ ብሎም በሃገራችን ምንም ዓይነት የህሊናና የፖለቲካ እስረኛ የለም በማለት አገዛዙ በህዝብ ቁስል ላይ መሳለቁን ቀጥሎበታል፡፡
እነዚህን ሁሉ ችግሮች በቀላሉ መፍታት ሲችል በተቃራኒው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ዜጎችን ማሳደድና ማፈን፣በየጦር ካምፑ ማጎር ዋነኛ የበጀት ዓመቱ ስራው አድርጎት አንድ ዓመት የኢትዮጵያውያን የመከራ ጊዜ አልፏል፡፡
በአጠቃላይ ባሳለፍነው የበጀት ዓመት ሀገራችን ከመቸውም ጊዜ በባሰ በከባድ ችግር ውስጥ ወድቃለች፡፡ይህ ሊሆን የቻለበት ዋናው ምክንያት አገዛዙ ለመጭው 25 እና 30 ዓመታት ያለምንም ተቀናቃኝ ስልጣን ላይ እቆያለሁ በሚል አቅዶ ስለነበረ እና ይህንን ህልሙን ወደ ቅዠት የለወጠ የህዝብ ተቃውሞ በመነሳቱ ነው፡፡ ባላሰበው ሰዓት ስልጣኑ አደጋላይ በመውደቁ ይህንን ሀቅ አምኖ ለመቀበል ባለመፈለጉ የሆነውን ሁሉ በክህደት በመጀመሩ ለተፈጠሩትና ለአንዣበቡት ችግሮች ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳይሰጥ አገዛዙ በራሱ ጠመንጃ ወደራሱ አነጣጥሮ እደቆመ እድሉን ሳይጠቀምበት 2009 ዓ.ም ጥሎት አልፏል፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ የተፈጠሩትን ችግሮች ካመነና የህዝብን ጥያቄ መመለስ ከጀመረ ውጤቱ ከስልጣን ወደኋላ ማፈግፈግና ለህዝብም ድል እዲጣፍጠው እና የበለጠ ግፊት በማድረግ ለስልጣናችን አደጋ ይሆናል ብሎ በማሰብ በራሱ አደርገቸዋለሁ ብሎ ቃል የገባቸውን ተግባራት እንኳ አንዱንም መፈፀም ሳይችል ራሱም ተጨንቆ የኢትዮጵያን ህዝብም እያስጨነቀ አንድ ዓመት የመከራ ዘመን አልፏል፡፡በዚህም ምክንያት ህወሃት/ኢህአዴግ በራሱ ፍርሃት ተከቦ በኢትዮጵያ የወደፊት ፖለቲካ ውስጥ በየትኛውም መመዘኛ የመፍትሔ አካል የማይሆንበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ስለሆነም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እና የዲሞክራሲ ሃይሎች ለሀገራችን ብቸኛ የመፍትሔ አካል መሆናችንን ተገንዝበን ከአለፉት ዓመታት ድክመትና ጥንካሬ ግንዛቤ በመውሰድ የኢትዮጵያ ወጣቶች የደም ዋጋ የከፈሉበትን የነፃነትና የእኩልነት ትግል ከግብ ለማድረስ ጠንክረን ለመስራት እና የሚከፈለውን ዋጋ ለመክፈለ የህሌና ዝግጅት ማድረግ እንዳለብ የጋራ ስምምነት ላይ በመድረስ የእለቱን ስብሰባ አጠናቋል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on June 27, 2017
  • By:
  • Last Modified: June 27, 2017 @ 11:36 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar