www.maledatimes.com ግልፅ ደብዳቤ ከጎሳዬ ተስፋዬ ለውድ ኢትዮጵያውያን በሰሜን አሜሪካ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ግልፅ ደብዳቤ ከጎሳዬ ተስፋዬ ለውድ ኢትዮጵያውያን በሰሜን አሜሪካ

By   /   July 15, 2017  /   Comments Off on ግልፅ ደብዳቤ ከጎሳዬ ተስፋዬ ለውድ ኢትዮጵያውያን በሰሜን አሜሪካ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 3 Second

” ይድረስ ለኢትዮጵያውያን
በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ የምትገኙ የስራዬ አድናቂዎች በሙሉ ይህን ግልፅ የሆነ መልእክቴን ከአክብሮት ጋር ወደናንተ ይደርስልኝ ዘንድ እወዳለሁ::
ኢትዮጵያዊነት ማለት ከአባቶቻችን የወረስነው ጀግንነት; ጨዋነት; እርስ በእርስ መከባበርና መዋደድ ነውና ዛሬም ከዚህ ማንነት ተካፋይ በመሆኔ የሚሰማኝ ደስታ ወደር የለውም::
ዛሬ ዛሬ እራሳችን በምንፈጥራቸው የሀሳብ ልዩነቶችና ያለመግባባት ችግሮች ሲያጋጥሙን ተወያይተንና ተከባብረን ጉዳዩን በመፍታት ፈንታ ብዙሀኑ ህዝብ በሚጠቀምባቸው ድረገፆች ላይ የተዛባ መልእክቶችን ማስተላለፍ የተለመደ ሆኗል!!
እንደሚታወቀው በያዝነው አመት የሰሜን አሜሪካ የስፖርት ፌዴሬሽን ላይ ሙዚቃዎቼን ለማቅረብና ከአድናቂዎቼ ጋር ለመገናኘት ዝግጅቴን አጠናቅቄ በስፍራው የተገኘሁ ቢሆንም በጥቂት ግለሰቦች ፍርደገምድል ውሳኔና ጫና እንዳሰብኩት ከአድናቂዎቼ ጋር ሳልገናኝ ቀርቻለሁ::
በዛ ሰአት በተፈጠረው የአድናቂዎቼ መጉላላት ከልብ ባዝንም በሶሻልሚዲያ ላይ ወጥቼ እሰጥ-አገባ መመላለሱ ስብእናዬና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት አስተዳደጌ ስለማይፈቅድ ብዬ ዝምታን መርጬ የነበረ ቢሆንም , እየተላለፈ ያለው የተዛባ መልእክትና የእናንተ የአድናቂዎቼ ፍቅር ; አክብሮትና ; የማበረታታት መልእክቶቻችሁ ይህንን እንድፅፍ አስገድዶኛል!!
የዚህ አይነቱ የተሳሳተ የስም ማጥፋት ዘመቻ በኔ ላይ ሲፈፀም ኢሄ የመጀመሪያው አይደለም ከዚ በፊትም በሀይማኖት ጉዳይ የተሳሳተ ነገር ተነስቶብኝ የነበረ ቢሆንም በእግዚአብሄር ፈቃድና በእናንተ አድናቂዎቼ ድጋፍ እንደተወጣሁት የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው!!
ዛሬም ከእውነት ጎን ቆማችሁ ፍቅራችሁንና ድጋፋችሁን በተለያዩ ድረገፆችና በግል ኢሜል በሜሴንጀር ከጎኔ ቆማችሁ ወገናዊነታችሁን ላደረሳችሁኝ አድናቂዎቼ እና ለእምነታችሁ ያደራችሁ ጋዜጠኞችና ጦማርያን ስለሁሉም ነገር ልባዊ ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ!!!
አሁንም ቢሆን እኔ አርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬ ከምንም ነገር የፀዳሁ ; በኢትዮጵያዊነቴ የማልደራደር ; እግዚአብሄር በሰጠኝ ፀጋ በሙያዬ ህዝቤንና ሀገሬን እንደማገለግል ቃል እየገባሁ እሰናበታለሁ:: እምነት አይሸጥም!!!!
ጎሳዮ ተስፋዮ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on July 15, 2017
  • By:
  • Last Modified: July 15, 2017 @ 6:19 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar