www.maledatimes.com ኢትዮጵያ ታላቁን የቱሪዝም አባትና ባለውለታዋን አጣች : - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ኢትዮጵያ ታላቁን የቱሪዝም አባትና ባለውለታዋን አጣች :

By   /   August 9, 2017  /   Comments Off on ኢትዮጵያ ታላቁን የቱሪዝም አባትና ባለውለታዋን አጣች :

    Print       Email
0 0
Read Time:51 Second

አሳዛኝ ሰበር መረጃ 🙁
===============

=================================
* አቶ ሐብተሥላሴ ታፈሰ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ለኢትዮጵያ የቱሪዝም አባት ይባላሉ፡፡ በፎቶግራፈርነት፣ በአስጎብኚት፣ በቱሪዝም ኮሚሽነርነትና የኢትዮጵያ ባህላዊ እሴቶች በአለም እንዲተዋወቅ ሰርተዋል – አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ፡፡

“ምድረ ቀደምት” ወይም “ላንድ ኦፍ ኦሪጅን” በዚህ አመት የሃገሪቱ መለያ ከመሆኑ በፊት ኢትዮጵያ ለረጅም አመታት የቱሪዝም መለያዋ አድርጋው ለነበረው “የ13 ወር ፀጋ” ወይም “Thirteenth month of sunshine” ፈጣሪ ናቸው፡፡

እኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ዛሬ ረፋድ በተወለዱ በ90 አመታቸው በባልቻ ሆስፒታል ማረፋቸውን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰምተናል፡፡

አቶ ሀብተስላሴ ለሀገሪቱ የቱሪዝም እድገት ላበረከቱት የላቀ አስተዋፅኦ በዚህ አመት በተደረገው 6ኛው የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ጉባኤ በምክር ቤቱ ስብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሣለኝ የእውቅና የወርቅ ፒን ተበርክቶላቸዋል፡፡

ባለፈው አመት ሐምሌ ወር ዮኒቲ ዩኒቨርስቲ ለዚህ ታላቅ ሰው የሊቀመንበሩን የእውቅና ሽልማት ሰጥቷቸዋል፡፡ የአቶ ሃብተስላሴን የቀብር ሥነ-ሥርዓት ለመፈፀም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ኮሚቴ አቋቁሞ እየተንቀሣቀሰ መሆኑን የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የህዝብና አለማቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ ተናግረዋል፡፡

ሸገር ለቤተሰቦቻቸው፣ ለዘመዶቻቸው እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ቱሪዝም ባለሞያዎች በእኚህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሞት የተሰማውን ሐዘን ይገልፃል..

( የመረጃዬ ምንጭ በሸገር ሬዲዮ ጋዜጠኛ ምስክር አወል የተሰራጨው መረጃ ነው )

ነፍስ ይማር 🙁

ነቢዩ ሲራክ
ነሐሴ 3 ቀን 2009 ዓም

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar