www.maledatimes.com የፌደራል መንግስት ቸልተኝነት ለነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቅ ምክንያት ነው ተባለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የፌደራል መንግስት ቸልተኝነት ለነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቅ ምክንያት ነው ተባለ

By   /   August 19, 2017  /   Comments Off on የፌደራል መንግስት ቸልተኝነት ለነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቅ ምክንያት ነው ተባለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 50 Second

ከአርባምንጭ ነዋሪዎች የተላከ
የኢህአዴግ ከፋፉለህ ግዛ ፖሊሲ አይደለም ለሰው ልጅ ለተፈጥሮም አደገኛ ነው

የፌደራል መንግስት ቸልተኝነት ለነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቅ ምክንያት ነው ተባለ።

ለነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክ ህልውና አደጋ ውስጥ መውደቅ ዋንኛ ምክንያት የፌደራል መንግስት ለሌሎች የሀገሪቱ ተፈጥሯዊ እና ታሪካዊ የመስህብ ስፍራዎች የሰጠውን ዓይነት በቂ ትኩረት በመንፈጉ እንደሆነ በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ የባለድርሻ አካላት ገለጹ።
የደቡብ መገናኛ ድርጅት ቃለመጠይቅ ያደረገላቸው የነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክ ሀላፊ አቶ አብርሀም ማርዬ በመጥፋት ዋዜማ ላይ ለሚገኝው ነጭ ሣር ከላይ እስከታች የሚገኘው ጉዳዩ የሚመለከተው አካል ዝምታን መምረጥ በተለይም የፌደራል መንግስት ያለውን አቅም ተጠቅሞ ጫና አለማሳደሩ እንዳስከፋቸው ጠቁመዋል።

ይሄ ሁሉ ሲሆን የት ነበር ጥያቄ የተነሳበት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ላይ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ እንደሚገኝ ቢገልጽም አሁን ላይ ነጭ ሣርን ለገጠመው ቀውስ የመፍትሄ ሀሳብ ይዞ መቅረብ ግን አልቻለም።
በዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሮክተሬት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ስሞን ሽብሩ በፓርኩ ውስጥ የሚገኙት እንስሳት በምግብነት የሚጠቀሙት ነጫጭ ሣር ሙሉበሙሉ በመጥፋቱ የቻሉት ህይወታቸውን ለማትረፍ እንደሸሹ እና የተቀሩትም ቢሆኑ በርሀብ እያለቁ መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል። በመሆኑም ነጭ ሳርን ወደነበረበት ለመመለስ ጊዜው እንደረፈደም ጠቁመዋል።

ሀዋሳ የሚገኘው የክልሉ መንግስት ባህል እና ቱሪዝም መስርያ ቤት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊ በጉዳዩ ዙርያ ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ፓርኩ ከዚህን ቀደም በደቡብ ክልል ይተዳደር እንደነበር ነገር ግን ከጥቂት ዓመት በፊት የፌደራል መንግስት ፓርኩን አስመልክቶ በወሰነው ውሳኔ በደቡብ እና ኦሮሚያ ክልል የሚገኝ ስለሆነ ሁለቱ ክልሎች ተነጋግረው ይወስኑ በማለቱ ፓርኩን የደቡብ ክልል ሙሉ በሙሉ በሀላፊነት እንዳይቆጣጠረው እንዳደረገ ጠቁመዋል።

የሥራ ሀላፊው ጨምረውም የነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክን በተመለከተ የፌደራሉ መንግስት ከዚህ ወንዝ ማዶ ደቡብ ከዚህ ወዲህ ያለው ደግሞ ኦሮሚያ በሚል ያስቀመጠው የድንበር ከለላ ሥራ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ገልፀውታል።
“ምነው ቱንጋ ላይ ለልማት በሚል የኦሮሞ ተዎላጆች ከገዛ መሬታቸው ይነሱ የለ፤ ለምን የተፈጥሮ ሀብት እንዳይጠፋ በሚል ከገዛ መሬታችን ላይ የጉጂ ኦሮሞዎች አይነሱም?”

በሳምንቱ መጀመርያ ጉባኤውን በአርባ ምንጭ ከተማ ያካሄደው የዞኑ ምክር ቤት በዚህ ጉዳይ ላይ ያሳለፈው ውሳኔ አለመኖሩ ዞኑ ለነጭ ሳር ጥሪ ምላሽ ለመስጠት እንዳልተዘጋጀ ያሳየ ሆኗል።
ከጥቂት ዓመታት በፊት በሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ አሁን በነጭ ሳር ፓርክ ላይ የደረሰውን ያክል ባይሆንም ተቀራራቢ ሊባል የሚችል አደጋ ተጋርጦበት የነበረ ቢሆንም መንግስት በራስ እና ዓለምአቀፍ ወዳጆች ጥረት በቀላሉ ወደነበረበት ደረጃ መመለስ ችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በሚያስተባብሩት የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት በኩል ይህ ጉዳይ የቀረበ የነበረ ቢሆንም እስካሁን “የይመለከተኛል”ዕርምጃ ሊወስድ ግን አልቻለም።

ምነው ውዱ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከእኛ እንዳልወጡ እንዲህ የነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርካችን ሊጠፋ ሲቃረብ ዝምታን መረጡ?

 

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 7 years ago on August 19, 2017
  • By:
  • Last Modified: August 19, 2017 @ 9:22 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar