www.maledatimes.com የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽኑ ሮም ላይ ተዘርፏል። - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽኑ ሮም ላይ ተዘርፏል።

By   /   October 17, 2017  /   Comments Off on የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽኑ ሮም ላይ ተዘርፏል።

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 52 Second
ካለፈው ኦገስት ወር ጀምሮ እጅግ ተጋንኖ ሲወራ የነበረ ጉዳይ ነው። ፌዴሬሽኑ ሮም ላይ ተዘርፏል። ይህንን “ዝርፍያ” ልዩ ያደረገው በቅንብር እና በጥናት የተሰራ ነው የሚሉት ጥቂት አልነበሩም። ከውጭ የሚወራው እና የሚጻፈው ነገር ብዙ ነው። ፌዴሬሽኑ እንዴት እና ለምን ተዘረፈ? የሚለው ጥያቄ ግን ምላሹ ከመላ ምት ያላለፈ አልነበረም።   ቅዳሜ፣ 14 ኦክቶበር 2017 በአምስተርዳም ከተማ የተካሄደው አመታዊው የቦርድ አባላት ስብሰባ ይህንን እንቆቅልሽ የፈታው ይመስላል። በእለቱ ከሳሽ እና ተከሳሽ  በተገኙበት፤  ጉዳዩን በግልጽ ለመወያየት ተችሎ ነበር።   ካሜራችን ሂደቱን በድምጽና ምስል ይዞታል።     (ቭድዮውን ይመልከቱ Part 1)
የኢትዮጵያውያን ስፖርት እና ባህል ፌዴሬሽን በአውሮፓ (ኢ.ስ.ካ.ፌ)  ባለፈው ቅዳሜ፣ 14 ኦክቶበር 2017 አመታዊውን የቦርድ ስብሰባ  በአምስተርዳም ከተማ  አድርጎ ነበር። ከ 21 ክለቦች የተውጣጡ 45 አባላት የተሳተፉበት ይህ ስብሰባ አራት አጀንዳዎች ላይ የተወያየ ሲሆን፣ አንድ ቀን ከፈጀው ከዚህ ውይይት በኋላ አዲስ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መርጧል።  በ2018 እና 2019 አዘጋጅ ሃገሮችም ታውቀዋል። በዚህም መሰረት በ2018 ስቱትጋርት – በ 2019 ደግሞ ዙሪክ በክለብ ደረጃ ፌስቲቫሉን ከዘጋጁ በኋላ – የማዘጋጀቱን ሃላፊነት  ፌዴሬሽኑ  መልሶ ይወስዳል። ላለፉት ሁለት አመታት በሆላንድ እና በሮም በፌዴሬሽኑ ሃላፊነት የተካሄዱት  ዝግጅቶች እንደተጠበቀው ውጤታማ ባለመሆናቸው ለመጭው ሁለት አመት የአዘጋጅነቱን ሃላፊነት አዘጋጅ ሃገር ክለቦች እንዲወስዱ ጉባኤው ወስኗል። የ2017ቱ የሮማ ዝግጅት ብዙ አወዛጋቢ ነገሮች ነበሩበት።
ከዝግጅቱ በኋላ የተወሰኑ ግለሰቦች የተሰራበትን ገንዘብ ይዘው መጥፋታቸው በስፋት ሲወራ መሰንበቱ ይታወሳል።  የፌዴሬሽኑ አመራር አባላት፣ ዮሃንስ መሰለ ፣   ግርማ ሳህሌ፣  ከበደ ሃይሌ፣  እና ኢብራሂም ገንዘቡ እንዴት እንደተወሰደ እና እነሱም ሊደርስ ከነበረው ችግር እንዴት እንዳመለጡ ተናግረዋል። በወቅቱ በዚያ ስፍራ የነበረው ጥሩ ያልሆነ ድባብ እና ወሬ የነበረው አማራጭ ስፍራውን ለቅቆ ማምለጥ እንደነበር ቢገልጹም፣ ያረፉበት ሆቴል ጭምር  ያልታሰቡ ክስተቶችን ተጋፍጠዋል።   ሆቴል የክፍላቸው በማስተር ቁልፍ  እንደበረበሩባቸውም ተናግረዋል።
የዝግጅቱ አስተባባሪ ከነበሩት ውስጥ አንድነት (ቀዮ) እና ፍራንሲስኮ በአምስተርዳም ተገኝተው በዚህ ጉዳይ ላይ  ማብራርያ ሰጥተዋል። የተባለውን  ገንዘብ መውሰዱን ቀዮ ያመነ ሲሆን፣  ለዚህ ድርጊትም ምክንያት እንዳለው ይገልጻል።
ጉባአኤው በአጀንዳው ላይ ሰፊ ውይይት ካደረገ በኋላ፣ በፌዴሬሽኑ እና በእነ ፍራንሲስኮ የቀረቡትን የፋይናንስ ዘገባ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ወስኗል።   ከጣልያን ሮቤርቶ፣ ከሆላንድ ክንፉ አሰፋ እና ከኮለን ተስፋዬ ጉዳዩን መርምረው ለአጠቃላይ ጉባኤ እንዲያቀርቡ  ተመርጠዋል።
ውድ ግዜያቸውን፣ ጉልበታቸውን ፣ ክህሎታቸውን እና ገንዘባቸውን በነጻ ሲያፈስሱ የቆዩ የአመራር አባላት ሃላፊነታቸውን በጨዋነት አስረክበዋል። እጅግ አስቸጋሪ ጉዞ እንደተጓዙ ግልጽ ቢሆንም ትእግስታቸው ግን የሚደነቅ ነበር።   ጉባኤውም የቀድሞውን አመራር አባላት በከፍተኛ ምስጋና ካሰናበታቸው በኋላ 9 አባላት ያሉበት አዲስ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መርጧል። አዲሶቹ የአመራር አባላት የሚከተሉት ናቸው።
  • አሳዬ ከኖርዌይ (ሊቀ መንበር)
  • ነቢዩ ሰቆጣው ከፍራንክፈርት
  • ተስፋዬ ከኮለን (ዋና ጸሃፊ)
  • ዳናኤል ከስዊዝ
  • አፈወርቅ አዘበርሊን
  • መስፍን  ከስቱትጋርት
  • ፋሲል ከካታንጋ – ለንደን
  • ሮቤርቶ ከሮማ
  • ቴዲ ከቤልጅየም
  • ብርሃኑ ክስዊድን (ገንዘብ ያዥ)
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar