www.maledatimes.com ዶ/ር አብይ ለምን ጋዜጠኞችን ይፈራሉ ?ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጠያቄ መጠየቅ የሚቻለው በዌብሳይት በመላክ ብቻ ነው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

ዶ/ር አብይ ለምን ጋዜጠኞችን ይፈራሉ ?ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጠያቄ መጠየቅ የሚቻለው በዌብሳይት በመላክ ብቻ ነው

By   /   July 24, 2018  /   Comments Off on ዶ/ር አብይ ለምን ጋዜጠኞችን ይፈራሉ ?ለጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጠያቄ መጠየቅ የሚቻለው በዌብሳይት በመላክ ብቻ ነው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 33 Second

የጠቅላይ ምንስትሩ የሚዲያ አሰባሳቢ ኮሚቴ መግለጫውን ግልጽ አድርጓል ፡፡

ጉዳዩ የሚዲያ፡ስነ፡ምግባርን፡የሚጻረር ስራ ነው ማለዻ ታይምስ 

በሰሜን አሜሪካ ለሚካሄደው የሃገራዊ ኮንፈረንስ ሁኔታ ጠቅላይ ሚንስትሩን ጥያቄዎች መጠየቅ የሚቻለው በዌብሳይት ላይ ጥያቄዎችን በማስገባት ብቻ መሆኑን የሚዲያ አሰባሳቢው ኮሚቴ ገልጧል ። እንደ ኮሚቴው ውሳኔ ከሆነ ማናቸውንም ሚዲያዎችም ሆኑ ግለሰቦች ጥያቄዎቻቸውን በዌብሳይ ማድረግ ያለባቸው እንደሆነ አሳውቀዋል። የዚህም ዌብሳይት አድራሻ የሚከተለው ሲሆን  በሶሻል መገናኛም እንዲያቀርቡ ታዟል ።

www.ethiopiandiaspora.net

Facebook: PM Abiy in DC, #መደመር, @DrAbiyUSVist

Instagram: MedemerUSA

Twitter: MedemerUSA

 በሃገራችን ውስጥ ስላለው ለውጥ መወያየት የምንችለው በዌብሳይት በተሰጡ ጥያቄዎች መሆን የለበትም የሚሉት ሚዲያዎች ተቃውⶁቸውን ማሰማት ጀምረዋል።

የቀድሞውን ስርአት ለመመለስ የሚያስችል ከሆነ መገናኛ ብዟሓኖችን ለማፈን የሚረዳ አካሂያድ ከጅምሩ እየተከናወነ ነው ሲሉም መክረዋል።

በዚህ አይነት ሁኔታ የቀድሞው መንግስት ህወሃት ለሃያ አመታት ያፈነውን የመገናኛ ብዙሃን እግደት እና ሂደትን ዛሬ ዶክተር አብይ አህመድ ጥያቄዎችን ከመገናኛ ብዙሃኖች በቀጥታ የማይቀበል ከሆነ እና ለመገናኛ ብዙሃኖች የቀጥታ መግለጫ የማይሰጥ ከሆነ ምንም አይነት የለውጥ ሂደትም ሆነ የመደመር መንገድ የለውም ሲሉ ተችተዋል ።

በዚህም ሂደት የዶክተር አብይ መግለጫ መሆን ያለበት ተብሎ እንደታሰበው እና እንደተገመተው ከሆነ ፣ማንኛውም ሰው የፈለገውን ጥያቄ መጠየቅ የሚገባው በግንባር ቀደም ሲሆን ፣ከተቻለም ደግሞ ማህበረሰቡ ለመገናኛ ብዙሃኖች በመላክ ፣መገናኛ ብዙሃኖች ጥያቄውን ፣ በትክክለኛ መልኩ ህዝቡን በመወከል ማቅረብ አለባቸው ፣ እንጂ ፣የጠቅላይ ሚንስትሩ የሚዲያ አሰባሳቢ ኮሚቴ ማናቸውንም ሚዲያዎችንም ሆነ ፣የህትመት እና የሬዲዮ ድርጅቶችን ሊወክሉ አይችሉም በማለት ገልጸዋል።

በሌላም በኩል አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎችም በፌስቡክ ገጾቻቸው ላይ የሰጡት አስተያየት እንዳለም ለመግለጽ እንወዳለን።

ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን እታፈን ዋነኛ መንስኤ ባለስልጣናትም ሆኑ ፣ባለሃብቶች፣ የኪነጥበብ ሰዎች፣ ሙዚቀኞች፣ ዘፋኞች/አዝማሪዎች ፣ሌሎችም የሙያ አካላት፣ እና ምሁራን፣ ከጋዜጠኞች ለሚቀርብላቸው የቃለመጠይቅ ፎርም ወይንም ጥያቄ በቅድሚያ በደብዳቤ ጥያቄዎችን አሳውቀኝ በማለት እውነተኛውን ማንነታቸውን ላለማሳወቅ የሚጠቀሙበት ትልቅ አጀንዳ ነው ። በትክክለኛውም ለሚጠየቁጥ ጥያቄ የሚመልሱትን መልስ ሸምድደው በመምጣት ህብረተሰብን ባልታሰበበት አቅጣጫ ሊያስቱ እና ሊያስደስቱ ይሞክራሉ ፣አሁን ግን ይህ የነጻነት እና የእውነተኛ መረጃ የማቀበያ ዘመን ነው ፣ማንኛውም ጋዜጠኛ በቀጥተኛ መልኩ የሚፈልገውን ፣ያየውን እና የተሰማውን የሚጠይቀበት መድረክ ሊከፈት ይገብዋል እንጂ በደብዳቤ አስገቡ ማለት የሚዲያው መታፈን አባዜ ሁንም አለቀቀውም ማለት ነው።

ዶክተር አብይ ለምን ጋዜጠኞችን ይፈራሉ ?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar