www.maledatimes.com በህወሀት ስልጣን ዘመን ሁለት እግሮቹን እስርቤት ውስጥ ያጣው ከፍያለው ተፈራ የሰበታ ከንቲባ ቤት እና ገንዘብ አበረከቱለት - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Addis Admas  >  Current Article

በህወሀት ስልጣን ዘመን ሁለት እግሮቹን እስርቤት ውስጥ ያጣው ከፍያለው ተፈራ የሰበታ ከንቲባ ቤት እና ገንዘብ አበረከቱለት

By   /   August 18, 2018  /   Comments Off on በህወሀት ስልጣን ዘመን ሁለት እግሮቹን እስርቤት ውስጥ ያጣው ከፍያለው ተፈራ የሰበታ ከንቲባ ቤት እና ገንዘብ አበረከቱለት

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 7 Second

በህወሀት አስተዳደር እስርቤት ገብቶ በድብደባ ብዛት እግሩ አልንቀሳቀስ ብሎት ህክምና በሄደበት ሰአት በዶክተሮች ስህተት ተብሎ መቆረጥ የሚገባው እግሩን በመተው ጤነኛውን ከቆረጡበት በኃላ እንደገና በሽተኛውን ደግመው የቆረጡበት የቀድሞው እስረኛ እና የአሁኑ የአካል ጉዳተኛ አቶ ከፍያለው በደረሰበት የአካል እና የሞራል ጉዳት ማካካሻ ትሆን ዘንድ በማለት የሰበታ ከንቲባ ስጦታ ማበርከታቸው ተገለፀ።

ከንቲባው ስጦታውን ሲያበረክቱ

በህይወቱ ይሄ ይደርስብኛል ብሎ አስቦ የማያውቀው እና በአሁን ሰአት ሙሉ በሙሉ በዊልቸር የሚንቀሳቀሰው የቀድሞ ታራሚው ወጣት ከአከላዊም ሆነ ከሞራላዊ ጉዳት መቼም የሚያገግም እንዳለሆነ ይታወቃል ።ይህ ብቻ አይበቃም በማለት የከተማው ከንቲባ ካላቸው መዋእለ ነዋይ ቀንሰው የሰጡት ፣ከተማዋ ምንም በቂ ገቢ የላትም ሆኖም ለደረሰበት ጉዳት ሞራልን መተካት ባንችልም ፣አካልን መቀጠል ባንችልም መደገፍ ግን ግዴታችን ነው በማለት ስጦታውን አቶ ለገሰ ሰጥተዋል

በእስር ቤት ሁለት እግሮቹ ለተቆረጡበት ወጣት ከፍያለው ተፈራ የሰበታ ከተማ ምክር ቤት 150 ሺህ ብርና መኖርያ ቤት የከተማው ባለሃብቶች ደግሞ 312 ሺህ ብር በጥቅሉ 462 ሺህ ብር ተበርክቶለታል።
ስጦታውን ያስረከቡት ከንቲባ ለገሰ ነገዎ እገዛው ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ህወሃት ለአለፉት ሃያ ሰባት አመታት በወጣት ኢትዮጵያኖች ላይ ያደረገው ግፍ የትየለሌ ከመሆኑም የተነሳ ፣ከስልጣን የወረደ ጊዜ ከተወላጅ ህዝቡ ጋር የመተላለቅ ዘመን ይሆናል እያሉ በፍርሀት ዘመን የተጠመዱ ዜጎች እንደነበሩ ቢታወስም በአዲሱ ጠቅላይ ሚንስትር የመደመር እና የይቅርታ ዘመን ጥያቄ መሰረት እኛ ዝቅ ብለን እንጠይቃለን ባሉት መሰረት ህዝቡ ይቅርታውን ተቀብሎ ህይወቱን ለመቀጠል ቢሞክርም የህወሀት ፅንፈኛ አካላት ግን ህዝብን ከመንግስት ጋር እንዲሁም ዘርን ከዘር ለማጋጨት በመቀሌ መምከር መያዛቸው የማያዋጣ መሆኑን በማስጠንቀቂያጭምር ተነግሯቸዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

♦ “ ትክክለኛ ፍትሕ አይሰጡም” የተባሉት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ከችሎት እንዲነሱ ተጠየቀ !

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar