www.maledatimes.com የመለስን ሌጋሲና ስያሜን በተመለከተ ነፃነት ዘለቀ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የመለስን ሌጋሲና ስያሜን በተመለከተ ነፃነት ዘለቀ

By   /   August 17, 2018  /   Comments Off on የመለስን ሌጋሲና ስያሜን በተመለከተ ነፃነት ዘለቀ

    Print       Email
0 0
Read Time:5 Minute, 13 Second

የመለስን ሌጌሲና ስያሜን በተመለከተ
ነፃነት ዘለቀ (netsanetz28@gmail.com)

የትግራይ መንግሥት የመለስን ስድስተኛ ሙታመት ከምንጊዜውም በበለጠ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር እየተዘጋ

A file picture of the late Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi and his wife Azeb Mesfin arriving in Accra for an AU summit. Mrs Azeb has reportedly stalled on vacating the national palace for new Ethiopian leader Hailemariam Desalegn.

  • ጀ መሆኑን በትግራይ ቲቪ እየተከታተልን ነው፡፡ ሰው በወደደው ይቆርባልና ለአንድ ቀን ብቻም ሣይሆን ለሣምንታትም ማክበር የማንም መብት ነው፡፡ ለምን በደማቁ ለማክበር እየተሰናዱ እንደሆነም ግልጽ ነው፡፡ በሌላ ቦታ ይህ የሙት መንፈስ አከባበር እንደሚቀዘቅዝና ቢከበርም እንኳ ለታይታና ለይምሰል መሆኑን ስለሚገነዘቡ ይመስላል፡፡ “ባለቤቱ ያቀለለውን…” እንዳይባሉም ጭምር፡፡
    አንድ ሰው ሙታመቱ በብሔራዊ ደረጃ ተከብሮም ይሁን ታስቦ የሚውለው ምን ስለሠራ እንደሆነ መታወቅ አለበት፡፡ ለሀገርና ለሕዝብ መልካም ነገር ሠርተው የሚያልፉ ሰዎች በያንዳዱ ዜጋ ልብ ውስጥ ቋሚ ቦታ ስለሚኖቸራው በዓመት አንዴ ብቻ ሣይሆን ሠርክ እንደተከበሩ፣ እንደተወደሱና እንደታወሱ ይኖራሉ፡፡ በክፋት ሥራቸው የሚታወቁ ከሆነ ደግሞ በዚያው ልክ በየቀኑ እንደተወገዙና እንደተወቀሱ፣ ዘር ማንዘራቸውም እንደተረገመ፣ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸውም አንገታቸውን እንደደፉ ይኖራሉ፡፡ ከዚህ አንጻር ይህ የሰንበት ጽንስ መለስ ዜናዊ ለኢትዮጵያ ምን አመጣ? ለሕዝብስ ምን ሠራ? ብሎ መጠየቅ አስፈላጊ ነው፡፡
    የመለስን በረከተ መርገም ዘርዝሮ መጨረስ አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያን እንዲህ ብትንትኗን ከማውጣቱም በተጨማሪ የ100 ሚሊዮኖችን ሀገር ያለ ወደብ ያስቀረ መናጢ ሰው ነበር፡፡ ይህ አፈ ጮሌ የሆነ ሰው የሀገራችንን ታሪካዊ ጠላቶች ተልእኮ አንግቦ ኢትዮጵያን መቅኖ ያሳጣ የመርገምት ፍሬ ነው፡፡ የአንድን ጎሣ የበላይነትና የሥልጣንና የኢኮኖሚ ጠቅላይነትን አረጋግጦ የሞተ ሰው በመሆኑ በአንዱ ወገን እንደመልአክ በሌላውና በተጎጂው ወገን ደግሞ እንደሣጥናኤል የሚቆጠር ክፉ ከሚባል ዐውሬም በበለጠ የክፉ ክፉ ዐውሬ ነበር፡፡ ከዚህ አኳያ ለዚህ ሰው ሐውልት ማቆምም ሆነ በስሙ የሚጠራ ቅርስ መትከል የታሪክ ምፀት ነው፡፡
    ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት አስቸጋሪ ሁኔታ ዳርጓት የሄደን ሰው ከሞተም በኋላ ይህን ያህል ለርሱ ማሽቃበጥና ማሸርገድ ትርጉሙ አይገባኝም፡፡ ደህና ሰው ነበር ብለንም እንኳን ብናስብ ከሞተ ስድስት ዓመታትን ያስቆጠረ የሀገር መሪ ሀገር ለይቶላት መካን የሆነች ይመስል እስከዚህ ማላዘን ተገቢ አይደለም፡፡ ራስን እንደመሳደብም ይቆጠራል፡፡ ሌላው ይቅር ከስድስት ሚሊዮኑ የትግራይ ሕዝብ አንድ መለስን የሚተካ ሰው ጠፍቶ በሞተ ሰው ይህን ያህል – ለማስመሰልና ለፕሮፓጋንዳ መሆኑን ባናጣውም – ጤፍ መቁላት የጤና አይመስለኝም – (ባልጠፋ ቃል “ጤፍ መቁላት” በሚለው “መቅመድመድ” ልል ነበር እግዜር አወጣኝ፡፡)
    መለስ አለማም አጠፋም ወደ ምድር የመጣበትን ዓላማ አከናውኖ ላይመለስ ሄዷል፡፡ ሕይወት ደግሞ ወደፊት እንጂ ወደኋላ አትሄድም፡፡ ትግራይም ሆነች በመለሲስም ፍቅር የናወዙ ትግራውያን በአንድ ከፋፋይ ዘረኛ ሰው ፍቅር ወድቀው እንዲህ ከሚሰቃዩና በርሱ ዕኩይ ተግባር ክፉኛ በተጎዱ ዜጎች ዘንድ ለትዝብት ሳይዳረጉ ሌሎች ከርሱ የተሻሉና ከርሱ ስህተት ሚማሩ መለሶችን በመተካት ወደፊት ምብጋስ ሳይሻላቸው አይቀርም፡፡ ሀዘን ማጥበቅ ሀዘንን ሊያስከትል እንደሚችል መረዳትም ተገቢ ነው፡፡ በቅጡ ያልተያዘ ሀዘን መጥፎ ነው – ይተካል አሉ፡፡ የሰማሁትን ነው፤ ምን አስደበቀኝ፡፡
    በበኩሌ አንድ ሰው ሞተ አልሞተ ክፋቱን ለመግለጽ አልግደረደርም፡፡ በልማድ የሞተ ሰው አይወቀስም ይባላል፡፡ ይህን አልደግፍም፡፡ እናም መለስ ክፉ ሰው ነበር፡፡ ለክፋቱ ደግሞ ወሰን አልነበረውም፡፡ የርሱ ግርፎችና ደቀ መዝሙሮች ናቸው አሁን ድረስ ኢትዮጵያን መቀመቅ ካላወረድን አንተኛም ብለው ሌት ከቀን እያመሱን የሚገኙት፡፡ በፊት ጉልኅ ያልነበረ የዘር ግጭት የሚመስል ሕወሓት ዘራሽ ሁከት አሁን በየቦታው የሚቀሰቀሰውና ንጹሓን ዜጎች ካለአበሳቸው ተዘቅዝቀው የሚሰቀሉት ወያኔ በዘረኝነት ብርብራ ያሰከራቸው ወጣቶች በሚለኩሱት እሳት ወይም ለውጡን ለማክሸፍ ሆን ብለው አሰልጥነው በሚልኳቸው ሥውር የጥፋት ኃይሎች ነው፡፡ “ዓይነታው ያልበጀ ቅራሪው ሰው ፈጀ” ይባላል፡፡ በመላዋ ኢትዮጵያ እንደመዥገር የተጣብቁት የመለስ ልጆች ብልጭ ያለችልንን ለውጥ ለማደናቀፍ የሚራወጡት የሊቀ ሣጥናኤልን የመለስን ዜናዊን ሌጋሲ እውን ለማድረግ ነው – ኢትዮጵያን እስከወዲያኛው የማፈራረስና ታላቋ ትግራይን በአዲስ መልክ የመገንባት ሌጋሲ፡፡
    … ይልቁንስ ፌዴራል የሚባለው መንግሥት አዳዲስ ባለሥልጣናት እንዲህ አድርጉ – ነገ መደረጉ ለማይቀር ዕድሉን እናንተ ብትጠቀሙበት ተወዳጅነትን ታተርፋላችሁ፡፡ በየቢሮው የተሰቀለውን የዚህ እርጉም ሰውዬ ፎቶግራፍ አንሱ፡፡ ፎቶ አስፈላጊ ነው ከተባለም የዐቢይን ስቀሉ – ይሄም ለጊዜው አስፈላጊና ተገቢም አይመስለኝም – ገና በሕዝብ ያልተመረጠ ጊዜያዊ መሪ በመሆኑ “ፍየል ከመድረሷ… “ያስብላልና ለርሱም ደግ አይሆንም፡፡ ቆምኩለት ከሚለው የዲሞክረሲ ዓላማም ጋር ይጋጫል፡፡ ይህ ዓይነቱ ነገር በንጉሣውያንና በአምባገነኖች የሚዘወተር እንጂ በዴሞክራሲያውያን መሪዎች ዘንድ የተለመደ አይመስለኝም፡፡ አምባገነንነትን የሚያበረታታ ይመስለኛልና ሰውን በልብ መውደድ ብቻ ይበቃል፡፡ በዱሮ ስሞች ምትክ የተሰጡ በመለስ የሚጠሩ ስያሜዎችን ወደነበሩበት መልሱ፡፡ ግንቦት 20 እና መለስ የሚባሉ ጉዶች ከታሪክ ድርሣናት ቢጠፉ የአሁኑም ሆነ የወደፊቱ ትውልድ በአእምሮው አይሰቃይም፡፡ በነገራችን ላይ ልጁን መለስ ብሎ የሚጠራ ሰው በጣም ጥቂት እንደሆነ በሥራየ ምክንያት ማወቅ ችያለሁ፡፡ መለስን በማክበርም ይሁን በመፍራት አላውቅም ትግሬዎች ራሳቸው ይህን ስም ለልጆቻቸው ለመስጠት ብዙም የሚደፍሩት አይመስለኝም፡፡ ቤተ አምልኮት እስኪሠራለት በግድ ያለውድ “የተወደደ” ሰው በስሙ ልጅን መጥራት ያልተደፈረበት ምክንያት ሳይገባኝ አለሁ፡፡ የኔ ትዝብት በመሀል አገር ነው ታዲያ፡፡ ትግራይ ውስጥ ያለውን ምስል አላውቅም፡፡ የምታውቁ አሳውቁን፡፡ የደርጉ መንግሥቱ እንኳን ባቅሙ በስሙ ስንቱ መሰላችሁ የሚጠራበት! ህእ፣ “የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ” ይባል የለ?
    በተለይ በዐማራው አካባቢ የዱሮ ስሞች እየተለወጡ በመለስ የሚጠሩ ካሉ በቶሎ ወደፊተኛ መጠሪያቸው እንዲመለሱ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ ይህን የምለው አማራ ላይ የዘር ማጥፋት ዐውጆ፣ ዐማራ የመንግሥት ሥራ እንዳይዝ በውስጥ መመሪያ ከልክሎ፣ ዐማራን ከምድረገጽ ለማጥፋት ቁጥር ስፍር የሌላቸውን ሥልቶች ቀይሶ ሲተገብርና ሲያስተገብር ኖሮ በፈጣሪ ዕርዳታ የሞተን ሰው በስሙ ማስታወሻ ማቆም በራስ ላይ መቀለድ ነው – ሽህ አገር ቢሰጥ ፍቺ የሌለው ዕንቆቅልሽ፡፡ እንዲያውም ቢቻል የዚህ ሰው ዐፅም አይገኝም እንጂ ቢገኝ ኮትና ሱሪ አልብሶ ዘሄግ ላይ ማቆም ነበር፡፡ እንዲህ ብናደርግ ደግሞ የሞተን ሰው በመክሰስ ከራሽያ ቀጥለን ሁለተኛ እንሆን ነበር፡፡ መለስ እኮ ሰይጣን በአካል የመጣብን ገሃነማዊ ውርጅብ ነበር (Devil-incarnate)፡፡
    ስያሜን በተመለከተ አንድ የሞኝ ነገር ትዝ አለኝ፡፡ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲን ፊንፊኔ ዩኒቨርስቲ የሚሉ አሉ፡፡ መስማማት ያስፈልጋል፡፡ በበኩሌ ጃንጀሮ ዩንቨርስቲም ቢባል ግዴለኝም፡፡ ግን የጋራ መስማማት ያስፈልጋል፤ አለዚያ ቂልነት ነው – በትንሹ ሊያውም፡፡ የመለስን የምቃወመው ዕንቆቅልሽ ስለሆነብኝ ነው – የገደለህን ሰው አፍቅረህና ወደህ ለስሙ ማስታወሻ ሐውልት ማቆም ስላልተለመደ፡፡ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ግን ያን ያህል መጥፎ አሰያየም አላየሁበትም፡፡ አንድ ሥፍራ ደግሞ ሁለት ስያሜ የሚኖረው ከሆነ የአጠቃቀም ውዥንብርን ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ ከስሜታዊነት ወጥቶ አቅልን መግዛት ይገባል፡፡ በዚህ ረገድ እኛ ኢትዮጵያውያን ብዙ እየተጃጃልን ነው – ሌሎች በትዝብት እስኪስቁብን ድረስ፡፡ ናዝሬት – አዳማ፤ ደብረ ዘይት – ቢሾፍቱ፤ አሩሲ – አርሲ፤ አዋሣ – ሀዋሳ፤ አለማያ – ሀሮማያ፤ ጂጂጋ – ጂግጂጋ፤ አዲስ አበባ – ፊንፊኔ፤ …. የጅልነታችን መገለጫ ብዙ ነው፡፡ የኛ ጅልነት በስም መለዋወጥ ብቻ ቢያቆም ዕዳው ገብስ በሆነ፡፡ ሰሞኑን ደግሞ ከዐውሬነትም በታች መሆናችንን በኩራት ለዓለም እያሳየን ነው፡፡ ወዴት እየሄድን እንደሆነ ማወቅ እንኳን ሰው የፈጠረን እግዚአብሔር ራሱም ሳይቸገር አይቀርም፡፡ አጃኢብ ነው፡፡ የሞተስ ተገላገለ፡፡ ይብላኝ ይህን ጉዳችንን እያየን ከሞቱት በላይ ካሉት በታች ሆነን ለምንኖር እኛ፡፡ ይህን ሁሉ ትንግርታዊ ተዓምር አስታቅፎን ለሞተ ሰው ነው እንግዲህ በስሙ ብዙ መታሰቢያ እየቆመለት የሚገኘው፡፡ በሰው አምሳል የሚንቀሳቀስ በአስተሳሰብ ደረጃው ከዚያች ሶፊያ ናት ፎዚያ ከምትባል ሰው መሳይ አሻጉሊት ያነሰ ትውልድ ቀፍቅፎልን ለሄደ የዲያብሎስ ውላጅ ነው ይህ ሁሉ ሽርጉድ፡፡ እኔማ – አትታዘቡኝ እንጂ – “ጭራሹን ባልተፈጠርኩ” ወይም “ከተፈጠርኩ – ለምን ሶማሊያና ፊጂ ውስጥ አይሆንም – ከኢትዮጵያ ውጭ በተፈጠርኩ” የሚል ቁጭት ውስጥ ከገባሁ ዓመታት አለፉኝ፡፡ በስመ አብ! ምን ዓይነት አገር እየሆነች መጣች በል! በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ልክ እንደ አንደኛው ድኅረ ልደተ ክርስቶስ መቶ ክፍለ ዘመን ተመልሰን ወደ “ስቅሎ፣ ስቅሎ” የጋርዮሽ የስሜት ፍርድ ቤት እንግባ? ምን ዓይነቱ እርኩስ መንፈስ ገባብን?
    ግን ግን ከዚህ ሁሉ የሚተረማመስ የጳጳሣትና የካህናት መንጋ መካከል በጸሎቱ ሥሙርነትና በምህላው ቅቡልነት የተነሣ ሕዝብን ከፈጣሪ ቁጣ መታደግ የሚችል አንድ ኖኅ እና/ወይም አንድ ሙሤ እንኳን ይጥፋ?

 

የቦስተን የመደመርና ተግባራዊ ርምጃ የመውሰደ ጅምር

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar