www.maledatimes.com የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጎንደር ላይ የጠራው ስብሰባ ተካሄደ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጎንደር ላይ የጠራው ስብሰባ ተካሄደ

By   /   September 18, 2018  /   Comments Off on የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ጎንደር ላይ የጠራው ስብሰባ ተካሄደ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 11 Second

“በአራቱም ማዕዘን መሬት ተቆርሷል፣ ማንነት ተቀምተናል። የሚቀድመውም አስቀደምን ብለን እንጅ ብዙ ጥያቄ አለን። “

በስብሰባው ላይ የታደሙ ሀገር ተረካቢ ወጣቶች ከአነሷቸው ጭብጥ ሃሳቦች የተቀነጫጨበ

ማለዳ ታይምስ 

የወልቃይት ተወላጆች በጎንደር ስብሰባ ላይ http://www.maledatimes.com

” የመጀመርያ ጥያቄ መሆን ያለበት ለአማራነታችን ነው። ማንም ሲመጣ ወጥተን አሸርጋጅ እየሆንን ነው፣ ወደሞቀበት እየሄድን ነው። መጀመርያ አማራነታችን ማስቀደም አለብን”

“ትግርኛ ቋንቋ ትናገራላችሁ ይሉናል። አዎ እንናገራለን። ትግርኛ ብቻ ሳይሆን አረብኛም እንናገራለን። የጎረቤት ቋንቋ ነው። እንግሊዘኛም የሚናገር የወልቃይት ሰው አለ። እንግሊዘኛ አለም አቀፍ ቋንቋ እንጅ የትግራይ ቋንቋ አይደለም። ለአማራ አባይ ግልፅ እንደሆነ ሁሉ ተከዜም ግልፅ ነው” 

” እንበተን የሚል ሰውን እንደ ክልል መሪ አላየውም። አንድ የአማራ ገበሬ ስለ አንድነት ብትጠይቀው እንበታተን አይልህም። አብረን እንኑር ነው የሚለው”

በአንድነት የወልቃይት ጉዳይ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የወልቃይት ተወላጆች በጎንደር ላይ በአደረጉት ስብሰባ ላይ የተነሱትን ነጥቦች ነበር ከላይ ስናስነብባችሁ የነበሩት! ወልቃይት ማለት አማራ ነው እንጂ ትግርኛ ቋንቋነን ስለተናገረ የትግራዋይ ዝርያ አለው ማለት አይደለም ፣ዝርያም አይደለም የዘር ግንዳችን አይገናኝም ያሉት ተሰብሳቢዎቹ በጉርብትናችን ቋንቋቸውን እንደ ግል ቋንቋችን በሚገባ ጠንቅቀን እንናገራለን ሆኖም አማራነታችንን በጉልበት የሚነጠቀን ሀይል  የለም አይኖርም ይህንን ጉዳይ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

በመሬቶቻችን ላይ የደረሰውን ነጠቃ እና በዜጎቻችን ላይ ለደረሰው ጥቃት መንግስት ካሳ ማቅረብ ያለበት ሲሆን ጥቃቱንም ያደረሱትን የትግራይ የቀደሞ ባለስልጣናትን ለፍርድ ማቅረብ አለበት ።

ለሀዝቦቹም በድጋሜ በይቅርታ ጥያቄ እንደ ቀድሞአቸው ሰላማዊ ኑሮአቸውን እንዲመሩ መደረግ አለበት ።በስልጣን ዘመናቸው ሀይላቸውን በመጠቀም በወልቃይት መሬት ላይ የደሃውን ንብረት የነጠቁ እና በደሃው ቦታ ላይ ቦታ ያፈሩ ዜጎች ንብረታቸው በህግ ታግዶ ከወልቃይት መሬት በአስቸኳይ እንዲወጡ የሚል ከአስር ነጥብ በላይ ዋና ዋና ሀሳቦችን አስፍረው ተወያይተዋል።

አንድ የወልቃይት አባት ገልፀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 18, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 18, 2018 @ 8:06 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar