www.maledatimes.com የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው

By   /   September 28, 2018  /   Comments Off on የቦምብ ፍንዳታ ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 2 Second

Maleda Times Media Group 

ታምሩ ጽጌ
ሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች የሽብርተኝነት ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ተረኛ ወንጀል ችሎት ዓርብ መስከረም 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበው ዓቃቤ ሕግ፣ የቦምብ ጥቃቱ የተፈጸመው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ለመግደል መሆኑን በክሱ አስታውቋል፡፡

በቦምብ ጥቃቱ ክስ የተመሠረተባቸው ተጠርጣሪዎች አቶ ጌቱ ግርማ፣ አቶ ብርሃኑ ጃፋር፣ አቶ ጥላሁን ጌታቸው፣ አቶ ባህሩ ቶሎሳና አቶ ደሳለኝ ተስፋዬ ናቸው፡፡

ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ባቀረበው ክስ እንደገለጸው፣ ተከሳሾቹ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ላይ ግድያ ለመፈጸም ያነሳሳቸው በእሳቸው የሚመራ መንግሥት መኖር ስለሌለበት ነው፡፡ የአገሪቱ መንግሥት መመራት ያለበት ቀድሞ በተመሠረተው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ነው የሚል ዓላማ ተከሳሾቹ እንዳላቸው ዓቃቤ ሕግ በመሠረተው ክስ ጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም በማለትም፣ ተጠርጣሪዎቹ ለግድያ መነሳሳታቸውን ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሜሪካ ኮንግረስ የፀደቀውን ኤችአር 128 ለማስፈጸምና በስመ ሕዝበኝነት የራሳቸውን ዓላማ የሚያራምዱ መሆናቸውን፣ በዚህም ምክንያት የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት ስለማያስፈጽሙ ተጠርጣሪዎቹ ጥቃቱን ለመፈጸም መነሳሳታቸቸውን ዓቃቤ ሕግ በክሱ አክሏል፡፡

የሰኔ 16 ቀን 2010 ዓ.ም. የመስቀል አደባባይ የወንጀል ድርጊት ያቀነባበረችው በኬንያ ናይሮቢ የምትገኝ ገነት ታምሩ (ቶለሺ ታምሩ) የምትባል መሆኗን፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አመልክቷል፡፡

በመስቀል አደባባይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ድጋፍና ምሥጋና በተደረገ ሥነ ሥርዓት ላይ በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት ሁለት ግለሰቦች ሲሞቱ፣ ከ150 በላይ ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወሳል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on September 28, 2018
  • By:
  • Last Modified: September 28, 2018 @ 4:05 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar