www.maledatimes.com የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በርካታ መሥሪያ ቤቶች እንዲታጠፉ ወሰነ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በርካታ መሥሪያ ቤቶች እንዲታጠፉ ወሰነ

By   /   November 10, 2018  /   Comments Off on የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በርካታ መሥሪያ ቤቶች እንዲታጠፉ ወሰነ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 39 Second

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በርካታ መሥሪያ ቤቶች  እንዲታጠፉ ወሰነ

ፖለቲካ

7 November 2018ውድነህ ዘነበ

መዋቅሩን በማስተካከል ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ ተደራራቢ ሥራዎችን የሚያከናውኑ በርካታ መሥሪያ ቤቶች እንዲታጠፉ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

ሦስት ወራት ያስቆጠረውና በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከዚህ መሠረታዊ ውሳኔ በተጨማሪ፣ የተቋቋሙለት ዓላማ የጊዜ ገደቡ ቢያልፍም በሕይወት የሚገኙ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቶች እንዲፈርሱና የግለሰቦች መጠቀሚያ የሆኑ የቦርድ መዋቅሮች በድጋሚ እንዲመረመሩ መመርያ ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሥሩ 114 መሥሪያ ቤቶች ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ መሥሪያ ቤቶች መካከል አብዛኞቹ ተመሳሳይነትና የተደጋጋፊነት ባህሪ ያላቸውን ሥራዎች በተናጠል የሚያከናውኑ ናቸው ተብሏል፡፡

ምክትል ከንቲባው ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ በተካሄደ የአመራሮች መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ በከተማው አስተዳደር ሥር ከ100 በላይ እጅግ ግዙፍ የሆኑ የመንግሥት አስፈጻሚ መዋቅሮች አሉ፡፡

‹‹መዋቅሮቹ ለማኔጅመንት በሚያመችና ሥራዎችን በብቃት ማካሄድ በሚያስችል ደረጃ ዝቅ ማለት አለባቸው፤›› በማለት ምክትል ከንቲባው በመድረኩ ላይ ተናግረዋል፡፡

በዚህ መሠረት ማክሰኞ ጥቅምት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ፣ በከተማው ሥር የሚገኙና መሰብሰብ አለባቸው የተባሉ ተቋማት ላይ ያካሄደውን የመጀመርያ ዙር ጥናት አቅርቧል፡፡

አብዛኛዎቹ መሥሪያ ቤቶች በቅርቡ በፌዴራል መንግሥት የተካሄደውን ቅርፅ ይዘው በድጋሚ እንደሚደራጁ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሌሎች ወቅታዊ አጀንዳዎች የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቶችና የቦርድ መዋቅሮች ይሆናሉ ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ለተወሰነ ዓላማ ተቋቁመው፣ ነገር ግን የተቋቋሙለት ዓላማ ቢሳካም ባይሳካም ቆይታቸው ያበቃ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቶች በርካታ ናቸው፡፡

ነገር ግን እነዚህ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቶች መፍረስ ሲገባቸው፣ አሁንም መኖራቸው ታውቋል፡፡ ምክትል ከንቲባው እንዳሉት፣ በርካታ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቶች ጊዜያቸውን የጨረሱ ቢሆንም፣ በአመራሮች በጎ ፈቃድ ዕድሜያቸው ተራዝሟል፡፡

‹‹በዚህ አሠራር በርካታ የሕዝብ ሀብት እየባከነ ነው፤›› ሲሉ ምክትል ከንቲባው የችግሩን ስፋት ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ ከተማ መሥሪያ ቤቶች አብዛኞቹ ከተጠሪ ተቋማት በተጨማሪ በቦርድ ይመራሉ፡፡ ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩት፣ አንድ አመራር እስከ 15 ቦርዶች ውስጥ አባል ነው፡፡ በቦርዶቹ የስብሰባ ወቅትም የማይገኙ አመራሮች በርካታ ናቸው ብለዋል፡፡

ነገር ግን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ያሉ መሥሪያ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ሠራተኞች ለደመወዝ ከሚወጣው ወጪ፣ ሩብ ያህሉ ለሥራ አመራር ቦርድ አባላት ክፍያ ይውላል ሲሉ ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል፡፡

‹‹አንድ አመራር በወር ውስጥ እነዚህን ሁሉ ቦርዶች ሊመራ ቀርቶ በስብሰባ ላይ እንኳን አይገኝም፡፡ በዚህ አሠራር በርካታ የሕዝብ ሀብት እየባከነ ነው፤›› በማለት ምክትል ከንቲባው የችግሩን ስፋት ገልጸው፣ መዋቅሩ በድጋሚ እንደሚፈተሽ አስታውቀዋል፡፡  

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 6 years ago on November 10, 2018
  • By:
  • Last Modified: November 10, 2018 @ 11:54 am
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar