www.maledatimes.com የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ግዥ በመፈጸም ላይ ነኝ አለ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ግዥ በመፈጸም ላይ ነኝ አለ

By   /   January 24, 2019  /   Comments Off on የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ግዥ በመፈጸም ላይ ነኝ አለ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 52 Second

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከስድስት ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ መድኃኒቶችና የሕክምና መሣሪያዎች ግዥ በመፈጸም ላይ ነኝ አለ
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አሚር አማን (ዶ/ር)

የመድኃኒት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ችግር አለ ተብሏል

በአገሪቱ የሚስተዋለውን የመድኃኒትና የሕክምና መሣሪያዎች እጥረት በተወሰነ ደረጃ ለመቅረፍ፣ 6.4 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ግዥ በመፈጸም ሒደት ላይ መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ አሚር አማን (ዶ/ር) ገለጹ።

ሚኒስትሩ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርታቸውን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም. ሲያቀርቡ እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ የመድኃኒት አቅርቦትና ሥርጭት፣ እንዲሁም የተራዘመ የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች የግዥ ሒደት ችግሮች መኖራቸውን ጠቁመዋል።

የአቅርቦትና የሥርጭት ችግሩን ለመቀነስ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን ያስረዱት ሚኒስትሩ፣ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 2.4 ቢሊዮን ብር በማውጣት የመድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ መፈጸሙን ተናግረዋል።

የተፈጸመው የመድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ግዥ ተጠናቆ ምርቶቹ ወደ መጋዘን መግባታቸውንም ጠቁመዋል። በመሆኑም በአዲስ አበባ በሚገኙ ሁሉም ሆስፒታሎች የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ለመቀነስ እንደተቻለ ገልጸዋል።

በቀጣይም የመሠረታዊ መድኃኒትና የሕክምና ግብዓት አቅርቦትን ወደ 88 በመቶ ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅትም 6.4 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው የመድኃኒቶችና የሕክምና መገልገያዎች የግዥ ሒደት መጀመሩን አስታውቀዋል።

 የመድኃኒትና የሕክምና መገልገያዎች አቅርቦት እጥረት ከሚፈጠርባቸው ምክንያቶች ዋነኛው የተጓተተ የግዥ ሒደት መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሩ፣ ግዥዎችን ለመፈጸም ኤልሲ (የክፍያ ሰነድ) ከተከፈተበት ቀን አንስቶ ምርቶቹ ተጓጉዘው ወደብ ላይ እስከሚደርሱበት ያለውን የተጓተተ ሒደት ወደ ዘጠና ቀናት ዝቅ ለማድረግ፣ ዘንድሮ ዕቅድ ተቀምጦ በዚሁ መሠረት ለመፈጸም ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ከጅቡቲ ወደብ ወደ መጋዘኖች የሚደርስበት ሒደትም ከ25 ቀናት በታች እንዲሆን ለማድረግ፣ በተጨማሪም ከመጋዘኖች የአቅርቦት ጥያቄ ለሚያቀርቡ የሕክምና ተቋማት በሁለት ቀናት ውስጥ ለማድረስ ታቅዶ የነበረ መሆኑን፣ ነገር ግን አፈጻጸሙ ሲታይ እስከ 14 ቀናት ሊፈጅ እንደሚችል ገልጸዋል።

 የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ችግር መኖሩን፣ የዚህ ምክንያቱ የተራዘመ የግዥ ሒደት ብቻ ሳይሆን በዘርፉ የሚታየው የመልካም አስተዳደርና መድኃኒቶችን ከመጋዘኖችና ከሕክምና ተቋማት ወደ ገበያ የማውጣት ሌብነት መኖሩን በመጠቆም፣ ሚኒስቴሩ መፍትሔ ሊያበጅ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ይህንን ድርጊት በተመለከተ የፌዴራል ዋና ኦዲተር ከዓመታት በፊት ግዥ በሚፈጽመው ኤጀንሲ ላይ ባደረገው የክዋኔ ኦዲት ለይቶ ሪፖርት ማቅረቡን በመጥቀስ፣ ሚኒስቴሩ ይህንን ሕገወጥ ድርጊት እንዲያርም አሳስበዋል።

የካንሰር በሽታ ምርመራና ሕክምና አገልግሎትን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሚኒስትሩ አሚር (ዶ/ር) ገልጸው፣ ካንሰርን ለማከም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ብቻ የሚሰጠውን የጨረር ሕክምና ማዕከል ለማስፋፋት የማዕከል ግንባታና የመሣሪያ ተከላ ሥራዎች በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲና በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የማስፋፊያ ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን፣ በቅርቡ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቁም አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች የነፃ ሕክምና ካርድ እደላ መጀመሩን፣ በከተማዋ የሚገኙ ሰባት ሆስፒታሎች ለጎዳና ተዳዳሪዎች የሕክምና አገልግሎቱን በነፃ እንዲሰጡ አቅጣጫ መቀመጡንም አብራርተዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on January 24, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 24, 2019 @ 3:04 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar