www.maledatimes.com ይድረስ ለከንቲባ ታከለ ኡማ !! ከዘካርያ መሃመድ - MALEDA TIMES
Loading...
You are here:  Home  >  Ethiopia  >  Current Article

ይድረስ ለከንቲባ ታከለ ኡማ !! ከዘካርያ መሃመድ

By   /   January 29, 2019  /   Comments Off on ይድረስ ለከንቲባ ታከለ ኡማ !! ከዘካርያ መሃመድ

    Print       Email
0 0
Read Time:1 Minute, 34 Second

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ታከለ ዑማ፣ በአዲስ አበባ የጎዳና ላይ ሕይወት የሚገፉ ወገኖች (ሕፃናትና ወጣቶች) “የነገ ህልማቸውን እንዲኖሩ የማድረግ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን” ከሚል ስሜት ተነስተውና፣ በተጨማሪም ልመናን “ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት” በማለም በከፍተኛ የገንዘብ አቅም የሚተገበር የድጋፍ ማዕከል ለመመሥረት “የማኅበራዊ ትረስት ፈንድ” ማቋቋማቸውን በዜና ሰማሁ። 
.
ከንቲባ ታከለ ይህን ዓላማ ለማሳካት፣ ከከተማው አስተዳደር ካዝና ወጪ የሚደረግ ከፍተኛ ገንዘብ ከመመደባቸውም ባሻገር፣ ሕዝቡና ሌሎችም ድርጅቶች በሞባይል የአጭር መልዕክት፣ በመልዕክት ብር 2.00 የሚያዋጡበትን ዘመቻ ይፋ አድርገዋል። 
.
ዜናውን ስሰማ ከንቲባ ታከለ ኡማ ይህን ፕሮጀክት ይፋ ከማድረጋቸው በፊት፣ በተለይ “ወላጅ አጥ እና ተጋላጭ ሕፃናትን ለመታደግ” ባለፉት ጥቂት ዓመታት በPact-Ethiopia አስተባባሪነት አዲስ አበባን ጨምሮ በአምስት ክልሎች እየተተገበረ ስለነበረው “የኮከብ ብርሃን” ሀገር አቀፍ መርኃ-ግብር አልሰሙ ይሆን? የሚል ጥያቄ ነው የመጣብኝ። 
.
“የኮከብ ብርሃን” መርኃ ግብር ማኀበረሰብ አቀፍ የድጋፍና ክብካቤ ጥምረቶችን (Community Care Coalitions) በማቋቋም፣ የአካባቢ ማኅበረሰብን የጋራ አቅም በማስተባበር ለተጋላጭ ሕፃናት ሁለንተናዊ ድጋፍና ክብካቤ ለመስጠት የሚያስችል፣ በጣም ዉጤታማ መርኃ ግብር እንደሆነ አዉቃለሁ። Pact-Ethiopia መርኃ ግብሩን በአምስት ክልሎች ላይ ለማስተዋወቅ ትልቅ ሥራ እንደሠራ ብቻ ሳይሆን፣ በመርኃ ግብሩ የሰለጠኑ አካላት ዉጤታማ ሥራዎች ሲሠሩበትም እንደነበር በተግባር አይቼ በሸገር የ”ስንክሳር” መሰናዶ ላይ የራዲዮ ዶክመንተሪ ሠርቼበታለሁ። 
.
USAID “የኮከብ ብርሃን” መርኃ ግብር ሲጠናቀቅ ያስሰራው ግምገማ፣ “Yekokeb Berhan Program for Highly Vulnerable Children in Ethiopia -Endline Evaluation Report” በሚል ርዕስ google ላይ ስለሚገኝ፣ ከንቲባ ታከለ ወይም አማካሪዎቻቸው እርሱን አውርደው እንዲያነብቡት፣ በዚያ መርኃ ግብር ላይ የሠሩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ፣ እንዲሁም ማኅበረሰብ አቀፍ ድርጅቶችን ጠርተው እንዲያናግሩ በአክብሮት እመክራቸዋለሁ። 
.
የክብካቤ ማዕከል ለአረጋውያን ይሆን እንደሁ እንጂ ለሕፃናት ፈፅሞ የሚመከርም አይደለም። አሁን ከንቲባ ታከለ የጀመሩት የማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ሕፃናትን በማዕከል ለመንከባከብ የሚያልም ከሆነ፣ አዲስ አበባን ከየክልሉ በሚመጡ እርዳታ ፈላጊ ሕፃናት ያጥለቀልቃት እንደሁ እንጂ ለችግሩ ዘላቂ መፍትኄ የሚያመጣ አይመስለኝም። 

በተረፈ በፕሮጀክቱ ፍፃሜ ማግስት ልመናን እና ለለማኝ መመፅወትን በሕግ የመከልከል (Banning/Criminalizing Poverty & Benevolence?!) ሐሳብዎን ስሰማ፣ በኢትዮጵያ ምድር ድህነትን እና ደሀን መርዳትን “ወንጀል” የማድረግ “ህልምዎ” እንዳስደነቀኝ፣ አልደብቅዎትም። ነገር ግን፣ በፍፁም ይህን መሰሉ ህልምዎ የሚሳካ አይመስለኝም። በአጭሩ ልመና በጣም ዉስብስብ ነገር ነው። በጣም ዉስብስብ!!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %
    Print       Email
  • Published: 5 years ago on January 29, 2019
  • By:
  • Last Modified: January 29, 2019 @ 4:05 pm
  • Filed Under: Ethiopia

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%
<"Without the support of our readers, the Maleda Times website would not exist in its present form">

You might also like...

በሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ መከላከያ ከአማራው ማህበረሰብ እና ከፋኖ ጋር ጦርነት ገጥሟል

Read More →

This site is protected by wp-copyrightpro.com

%d bloggers like this:
Skip to toolbar